በዓለም መድረክ ላይ ስማቸው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ገኖ ከተሰማው ውስጥ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳራ መንክር ትገኝበታለች። ታዋቂው “የታይምስ” መፅሄት በያዝነው ዓመት በቴክኖሎጂ ዘርፍ እጅግ ውጤታማ ስራን በመስራት “የዓለማችን ተፅእኖ ፈጣሪ” ሰዎች መካከል አንዷ አድርጎ እንደመረጣት የቢቢሲ የዜና ማሰራጫ በዘገባው አስነብቦናል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳራ መንክር በታይም መጽሔት ከዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ የዓለማችን 100 ሰዎች መካከል አንዷ በመሆን ተመርጣለች። ኢትዮጵያዊቷ ሥራ ፈጣሪ እና የምግብ ፖሊሲ ስፔሻሊስቷ ሳራ ከተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካትታለች። “የግሮ ኢንተለጀንስ” መስራችና የበላይ ኃላፊ የሆነችው ሳራ፣ የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተተችው በምግብ ዋስትና እና በአየር ንብረት ላይ በሰራችው ስራ ነው።
ታይም መጽሔት በ2021 ተጽዕኖ ፈጣሪ ብሎ የመረጣቸው በአካዳሚ፣ በሳይንስ፣ በአክቲቪዝም እና ምጣኔ ሀብት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ነው። በዚህም ሳራ መንክር በዓለም ዙሪያ ካሉ የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል አንዷ ሆና ለመመረጥ በቅታለች። ሳራ አዲስ አበባ ውስጥ ተወልዳ ያደገች ሲሆን ወደ አሜሪካ ያመራችው በ1970ዎቹ ነበር። በኋላም ሴቶች በሚማሩበት ማውንት ሆዮኬ ኮሌጅ እንዲሁም በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪዋን በኢኮኖሚክስ እና በአፍሪካ ጥናቶች እንዲሁም ከኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ኤም ቢኤ ማግኘቷን ትናገራለች።
በወቅቱ በጣም አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን የዓለም አቀፍ ተማሪዎች ከሚቀጥሩ ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው ዎል ስትሪት የሥራ ላይ ልምምድ አገኘች። በዚያ ወቅትም በነዳጅ እና ጋዝ ሽያጭ ላይ ለተሰማራ ኩባንያ ነበር ትሰራ የነበረው። በ29 ዓመቷ በዎል ስትሪት ያላትን ሥራ በመተው ‘ግሮ ኢንተለጀንስ’ የተሰኘ ኩባንያ መሰረተች። በወቅቱ የምግብ ዋስትና ላይ ለመስራት በመወሰን ሥራዋን ስታቆም “ከኢትዮጵያ ጋር የሚያስተሳስራት ሥራ” እንደሚሆን ተናግራ ነበር።
በአፍሪካ የምግብ ዋስትና አለመረጋገጥ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን የተረዳችው ሳራ፣ በዋናነት ከገበሬው ጋር በመስራት ችግሮችን ከስር መሠረታቸው ለመቅረፍ ማለሟን ታስረዳለች። ሳራ ከዎል ስትሪት ለቃ ‘ግሎ ኢንተለጀንስን’ እስክትመሰርት ድረስ ሁለት ዓመት ያህል የማሰላሰያ እና የማሰቢያ ጊዜ ወስዳለች። እኤአ በ2014 ‘ግሎ ኢንተለጀንስ’ ስትመሰርት በዓለም የተለያዩ አካባቢዎች በመጓዝ እና ከገበሬዎች ጋር በመገናኘት እንዲሁም የእርሻ ስፍራዎችን በመጎብኘት የሚያስፈልጋትን መረጃዎች ሰበሰበች። በዚህ ወቅት በግብርናው ዘርፍ የሚያስፈልገው አዲስ እውቀት ነው ወይስ ያለውን እውቀት ማደራጀት የሚለውን ካጠናች በኋላ ችግሩ ተቋማዊ መሆኑን መረዳቷን ትናገራለች።
ከዚህ በፊት በኢነርጂ ገበያ ውስጥ በምትሰራበት ወቅት ያላትን ልምድ እንደ ግብዓት በመጠቀም ግብርናውን እንዴት ማሸጋገር እንደሚቻል ትናገራለች። ግሮ ኢንተለጀንስ ከዓለም ላይ ከሳተላይት፣ ከሜትዎሮሎጂ፣ ከመንግሥት ተቋማት፣ ከሸቀጦች ዝውውር፣ ከአነስተኛ ንግድ ተቋማት፣ መረጃዎችን በመሰብሰብ የማደራጀት እና የመቀመር ሥራ እንደያከናውን ትናገራለች። ግሮ ኢንተለጀንስ አርሶ አደሮች እና መንግሥታት የተሻለ ውሳኔ እንዲወስኑ ለማገዝ ይሰራል።
ያለ ንብ ማር፣ ያለ ላም ወተት ማምረት ይቻላል? ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት አርሶ አደሮችን በሳተላይት የምታግዘው ኡጋንዳዊቷ የናሳ ሳይንቲስት በአፍሪካ የምግብ ዋስትና አለመረጋገጥ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን የተረዳችው ሳራ፣ በዋናነት ከገበሬው ጋር በመስራት ችግሮችን ከስር መሠረታቸው ለመቅረፍ ማለሟን ታስረዳለች። በግብርናው ዘርፍ የሚያስፈልገው አዲስ እውቀት ነው ወይስ ያለውን እውቀት ማደራጀት የሚለውን ካጠናች በኋላ ችግሩ ተቋማዊ መሆኑን መረዳቷን ትናገራለች።
ከዚህ በፊት በኢነርጂ ገበያ ውስጥ በምትሰራበት ወቅት ያላትን ልምድ እንደ ግብዓት በመጠቀም ግብርናውን እንዴት ማሸጋገር እንደሚቻል አስተዋውቃለች። ግሮ ኢንተለጀንስ ከዓለም ላይ ከሳተላይት፣ ከሜትዎሮሎጂ፣ ከመንግሥት ተቋማት፣ ከሸቀጦች ዝውውር፣ ከአነስተኛ ንግድ ተቋማት፣ መረጃዎችን በመሰብሰብ የማደራጀት እና የመቀመር ሥራ እንደሚያከናውንም መረጃዎች ይጠቁማሉ። ዘገባውን ስናሰናዳ በተጨማሪ ዋቢነት- ቢቢሲንና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ተጠቅመናል
አዲስ ዘመን መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም