የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ዛሬ የፈረንሳይ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑትን ማርየሌ ሳርነዝ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው የሁለቱን አገሮቸ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባችው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
ወ/ሮ ሂሩት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ረጅም ዘመን ያሰቆጠረ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው ትብብሩም በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በማህበራዊ መስኮች ላይ ያተኮረና ሁሉን አቀፍ ነውም ብለዋል። አሁን ያለውን ታሪካዊ ግነኙነት የሁለቱን አገሮች ህዘቦቸ ጥቀም ባስጠበቀ መልኩ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በአየር ንብረትና በህዝበ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ይሰራልም ብለዋል። ፈረንሳይ ለኢትየጵያ ልማት እያደረገች ያለውን ድጋፍ ኢትዮጵያ ታደንቃለች ብለዋል።
በተለይም በኢትዮጵያ የሚገኘውን የላሊበላ ውቅር አብየተ ክርስቲያናት አድሳት እና የብሄራዊ ቤተመንግስትን በማደስ ለህዝብ እይታ ክፍት ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ የፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ ለማደረግ ላሳየው ተነሳሽነት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ይህም የህዝበብ ለህዝብ ግንኙነቱን ይበለጥ ያሳድገዋል ብለዋል።
ሊቀመንበር ማርየሌ ሳርነዝ በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቅፍ ለውጥ ፈረንሳይ ታደንቃለች ብለዋል። ለውጡ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣ የህግ የበላይነትና የሚዲያ ነፃነትን በማረጋገጥ የአገሪቱን ልማት እንደሚያፋጥን እምናታቸው መሆኑንም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተደረሰረው የሰላም ሰምምነት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ጸጥታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ገልጸዋል።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ፅ/ቤት እንዳስታወቀው የሁለቱን አገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩም ክብርት ማርየሌ ሳርነዝ ገልጸዋል።