ያኔና 2013
እያጠናቀቅን ያለው 2013 የልጅነት ዘመኔን ያስታውሰኛል። በብዙ መልኮቹ ወደ ኋላ ወስዶኝ እያለፈም ነው። ከአገሬ ሰላምና ደህንነት ጋር የተያያዝነውን ብቻ ላንሳ። ’’ሁሉም በአገር ነው’’ እንዲሉ።
ያኔ ሶማሊያ የአገራችንን መሬት ለመውሰድ ወረረችን። በምሥራቅ እስከ አዋሽ 700 ኪሎ ሜትር ድረስ ዘልቃ ‘’የታላቋን ሶማሊያ’’ ህልም ለማሳካት ሞከረች።
አሁን ከአንዱ የአገራችን ክፍል ሌሎቹን የአገሩን ሕዝብ የሚወጋ አካል ጦር ሰብቆብናል። ወገን በወገኑ ላይ ዘምቶ አንድ ለ11 የሚባል ዓይነት ጦርነት ውስጥ ገብተናል።‘’ላታመልጪኝ አታሩጪኝ’’ ዓይነት ይመስላል ጦርነቱ።
ኢትዮጵያ ለማስተዳደር አጋጣሚ የፈቀደለትን ዕድል ያበላሸ ቡድን በሚገርም ሁኔታ ዳግም ሥልጣን፣ የአገር ሀብትና ጥቅም ለመንጠቅ በጦርነት አዲስ አበባ ገብቶ ሊያስተዳድረን እየሞከረ ነው። ያኔ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት በህቡዕ ለመታገል ውጋት የሆኑበት ሁኔታም እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ። ዛሬም ማንነትን ለማስከበር ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ያልተመቻቸው ወገኖች ሽብር ሲፈጥሩ ይታያሉ።
ሁሌም ሰላምና መረጋጋት የሚናፍቀውን የአፍሪካ ቀንድ ጂኦ ፖለቲክስ ለማቃወስ በእሳት ላይ ነዳጅ ለመጨመር ያኔም ተሠርቷል። ዛሬም ጦርነቱን ወደ ጎረቤት አገሮች ለማስፋፋት ሲሞከርም ይታያል። አልሆነም እንጂ። ኢትዮጵያውያን ያኔም አሁንም አንድ ሆነን የወጣንበት ታሪክ ገጥሞናል። ከሃዲዎችና ባንዳዎችን ቀንሰን። ያኔም ኢትዮጵያን የማዳን ዘመቻ ተካሂዷል። ዛሬም ይህቺን ታሪካዊ ጥንታዊ አገር ለማዳን እየተዘመተ ነው።
ዘመቻ + ድጋፍ
የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ባቀረቡት የእናት አገር 300ሺህ ሕዝባዊ ሠራዊት(ሚሊሺያ)አዘመቱ። ዛሬ ደግሞ መከላከያ ሠራዊትን ብቻ የተቀላቀሉትን ወጣቶች ብቻ መመልከት በቂ ይመስለኛል።
የአገሩን ሉዓላዊነትና አንድነት ለማስከበር እናቶቻችን ገብስ ፈትገው በሶ አዘጋጅተዋል። ዳቦ ቆሎና ጭኮ አሰናድተዋል። አርሶ አደሮች በሬዎቻቸውን ለግሰዋል። የገንዘብ አስተዋጽኦም በገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ተደርጓል። ዛሬ በተመሳሳይ ሁኔታ ስንቅ ተዘጋጅቷል። በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የታሸገ ውሃ መጨመሩ ብቻ ለየት ያደርገዋል እንጂ፤ለሠራዊቱ ምን የማይደረግ ነገር አለ!! ያኔም ሆነ ዛሬም ራሱን፣ገንዘብና የዓይነት ድጋፍ የሚያደርግ ሕዝብ ያላጣች ድንቅ አገር እንዳለችው በተግባር መስክሯል።
እውነተኛ ኢትዮጵያዊ በአገሩ ጉዳይ የማይደራደር ሕዝብ መሆኑን ለዓለም እያሳየ ነው።
‘’ወተቱን እንጂ…..ላሚቱን ‘’
ኢትዮጵያዊነት በከረረ ማንነትና ብሄርተኝነት በሽታ ታሞ ከሩብ ምዕተ ዓመታት በላይ በሥልጣን ላይ በነበረው አስተዳደር አልጋ ላይ ቆይቷል። ለዜግነት ወይም ለይለፍ ብቻ የተዘጋጀ እስኪመስል። አስተዳዳሪዎቻችን የማይወዷትን አገር ይመሩ ነበር።
ይህንንም አመለካከታቸውን ለማወቅ ሩቅ መሄድ አያስፈልግም። በሐምሌ 2013 መግቢያ ላይ አሳይተውናል። መንግሥት የትግራይ ክልልን ለቅቆ ከወጣ በኋላ የጥሞና ጊዜ ሰጥቶ ነበር። አንድ በጀት ዓመት ተጠናቅቆ ወደ ሌላ በጀት በተሸጋገርንበት ወቅት የፌዴራል መንግሥት ለክልሉ 12 ቢሊዮን ብር በጀት መመደቡን ስለሚያውቅ ‘’በጀቴን አሁኑኑ ቁጭ’’ የሚሉት ጥያቄ ማቅረብ ጀመረ።
የፌዴራሉ መንግሥት በ2013 በጀት ዓመት ለክልሉ 8 ቢሊዮን ብር በጀት ተመድቦ 100 ቢሊዮን ብር ለመልሶ ማቋቋም እንዳወጣ የሚያውቀው ቡድን ድጎማው እንዳልተላከለት እያወቀ፤ የአዲሱን በጀት ዓመት አምጡ የሚለው ሊዋጋበት እንደሆነ ልቡ እያወቀ ‘’የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን አባል እንደመሆኔ’’ ማለቱን ባንጠላበትም፤ሰላም ባልወረደበትና መግባባት ባልተፈጠረበት ‘’አምጡ’’ማለቱ ያስተዛዝባል። በፍቅርና በሰላም ሁሉም አለ።‘’አራዳ’’ነት ሲያስነቃ ግን ምንም የለም።
ዱሮውንም ኢትዮጵያዊነትን የማይወደው ቡድን በስሟ ተጠቀመ። መዘበረ። ዘረፈ። ሕዝብ ተፍቶት ከሥልጣን ሲወርድ፤መቀሌን መሸሻና መጠጊያው አድርጎ ሲመቸው ኢትዮጵያዊ መስሎ፤ካልተመቸውም ደግሞወደ የገንጣይ አስገንጣይ ጨዋታውን ካርታ መዝዞ ይጫወታል። እናም ‘’ውሳኔ ሕዝብ’’ ናፈቀኝ ይለናል። በአጭርና ግልጽ ቋንቋ ሲቀመጥ ለእነሱ ኢትዮጵያ ላም ነች። ወተቷና የወተት ተዋጽኦዋ ይፈለጋል። ላሚቱ ግን አትፈለግም።
ጠዋት ኢትዮጵያዊ የሆነው ቡድን፣ሲመሻሽ ‘’ራስን በራስ የማስተዳደር መብታችን ለማስከበር መብት ያለን ክልል በመሆናችን ሕዝበ ውሳኔ ልንጠይቅ እንችላለን’’ ሲል ታገኙታላችሁ ‘’የኢትዮጵያ ማንነት፣ታሪክ፣ባህልና ቅርስ መሠረት የሆነውን ክልልና ሕዝብ ለመነጠል ይሞክራል-ፖለቲካና ማንነትን ለማገናኘት ይሞክራል።
ነገር ግን በየአጋጣሚው ሰልፍ የወጡት ወገኖቼ ’’የትግራይ ሕዝብ አካላችን፤ህወሓት ጠላታችን!’’ በአንድነትና በአብሮነት መኖርን የሚመኘው ኩሩው ሕዝባችን ሕዝቡን ከፈላጭ ቆራጩ ኮሙኒስታዊው ህወሓት መለየት የቻለ ሕዝብ ነው። በዚህም እንኮራለን።
ያልደበዘዘው ቀለም
በ1970ዎቹ የማውቃት ኢትዮጵያ በጠባብ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ ተውጣ እንዳልቀረችና ደማቁ ቀለሟ እንዳልፈዘዘ በ2013 አሳይታኛለች። ይህ ደግሞ ዳግም በኢትዮጵያዊነቴ እንደ ሌሎቹ ወገኖቼ እንድኮራ፣ ከአንገቴ ቀና ብዬ ለመራመድ አስችሎኛል።
ያኔ ከመሪው በተደረገለት የእናት አገር ጥሪ ተምሞ ወደ ታጠቅ ጦር ሠፈር ገብቶ ለድል የበቃው ሚሊሺያ ፤ዛሬ ደግሞ መከላከያ ሠራዊትን የተቀላቀሉት ወጣቶች በወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት ገብተው አገር ለማዳን ሥልጠና ሲወስዱ ማየት በራሱ ያኮራል። ጠላትንም ያርበደብዳል።
ዛሬም ዜጎች ለአገር ለህልውና ለመዋደቅ ዝግጁነታቸውን በተግባር አሳይተዋል። ከአካባቢ ሚሊሺያነት እስከ መከላከያ ሠራዊት አባልነት አገርና ሕዝባቸውን ለመታደግ ሥልጠና ወስደው ውጊያውን ተቀላቅለዋል። በህልውና ለመጣ መልሱ ህልውናን ማስጠበቅ በመሆኑ።
ዛሬ የገጠመን የአንድን ክልል ሕዝብ ‘’ወራሪ’’ አድርጎና አስደርጎ ሁለት ክልሎችን ወርሮ ብሄር ተኮር ጥቃት በመፈጸም ሰዎችንና የቀንድ ከብቶችን ገድሏል፣ንብረት አጥፍቷል፣ ሀብት ዘርፏል፣ታሪክና ቅርሶችን አጥፍቷል፤ባህል አበላሽቷል።
የያኔው ወራሪ ጎረቤት አገር የውስጥ ችግሮችን አይቶ ሁኔታዎች ተመችቶኛል ሲል ወረራ ፈፀመ።
የዛሬው የውስጥ የፖለቲካ ችግሮችን በውይይት ባለመፍታት የአገር መከላከያ ሠራዊትን የጦር መሣሪያዎች ተማምኖ መንፈቅለ መንግሥት ለማካሄድ ሞከረ።‘’ሕዝባዊ ኃይል’’ን ተጠቅሞ ወረራን ከነግሳንሱ ተጠቅሞ ጥፋት አደረሰ። በያኔውና በአሁኑ መካከል ያለው ልዩነት በአብዛኛው የጊዜ ብቻ መሆኑ ይደንቃል።
ዓለም የገጠሟትን ችግሮችን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገዶች ለመፍታት ቅድሚያ በምትሰጥበት ዘመን የ”እኔን ብቻ’’ ካልሆነ ብሎ ወደ ጦርነት መግባት ‘’መተላለቅ’’ ካልሆነ ማንን እንደጠቀመ 2013 አሳይቶናል። ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መነጋገርን የመሰለ ምርጥና ተተኪ የማይገኝለት መፍትሔ ባለበት አገር 30 ዓመታት ወደኋላ መጓዝ ‘’ተገትሮ መቅረት’’እንጂ ሌላ ስያሜ ያለው አይመስለኝም።
በእኔ ግምት በክፍለ ዘመኑ ‘’አሳፋሪ’’ የተባለው ጦርነት በ2013 ገጥሞናል። የአንድ ብሄር ፖለቲካ ድርጅት የበላይነቱን ለማንገስ ሕዝብን ጋሻ አድርጎ ሌሎች የአገሩን ዜጎች መውጋት የሚያኮራም የሚያስደስትም ታሪክ አይደለም። ባይሆን አንገት የሚያስደፋ እንጂ።
ዳግም ወደ ጦርነት ‘’መሥመራችን ኃይላችን’’ ብሎ ሕዝቡን ተዋጊ አድርጎ ለ50 ዓመታት ያህል ያልተለወጠው፣ ቋሚና የማይለዋወጥ የትግል መሥመር ይዞ በተለወጠች ዓለም ያልተለወጠ ኮሙኒስታዊ ርዕዮተ ዓለም አንግቦ ሕዝብን አግቶ ወደ ጎረቤት ክልሎች መዝመት በተስፋፊነትና በወራሪነት መግባት ማንን ለመጥቀም እንደሆነ የሚያውቁት ራሳቸው ብቻ ናቸው። መነጠልና መገንጠል ምን ይዞ ጉዞ እንደሚሆን ራሱም በአግባቡ ያወቀው አይመስልም።
አካሄዱ የኢትዮጵያዊ ሳይሆን፤ የውጭ ጠላቶች የሚመስል አንጃ ገጥሞናል።‘’አገር ተከፋፈለች፣አንድነቷ የላላ፣ሕዝቧ ተለያየ ብሎ ሁኔታዎችን የሚገመግምና ለውጭ ጠላቶች አሳልፎ መስጠት ከሃዲነትም ነው። ኢትዮጵያውያን እንዲህ አይደለንም።
ድህነት፣ኮቪድ 19፣ የኑሮ ውድነትን፣የአንበጣ ወረራን ተቋቁሞ መኖር በከበደበት ዘመን ጦርነትን እንደ አንድ አማራጭ ወስዶ ይዋጣል ማለት ማንን ለመጥቀም?
ይበታተናሉ ተብለው የሚሰባሰቡት፣አለቀላቸው ብለው ሲያሟርቱ በአዲስ መልክ አድገውና ተመንድገው ብቅ የሚሉት፣ተስፋ የላቸውም ብለው ተስፋ ሊያሳጡን ሲሞክሩ ዛሬም ተስፋ እንዳላቸው በአንድነት ቆመው በተግባር የሚያሳዩ አገር ዜጎች መሆን ያኮራል።
በውጭ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን አንዷንና መለዋወጫ የሌላትን አገራቸውን ‘’አትንኩብን’’፣የእኛን ጉዳይ ለእኛው ተውት’’ ብለው የአውሮፓና የአሜሪካን አደባባዮች ሲያጥለቅልቁ የከረሙት ‘’አንድ ነን’’ ብለው ነው በተቃራኒው የሽብር፣ የመጠፋፋትና የሽቆልቁሎሽ ጉዞ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ወገኖችም ሰልፍ ወጥተዋል። ይህንን አንድነቱን ከልዩነቱ ጋር አክብሮና አስከብሮ የኖረ ሕዝብ የሚጠቅመው የቱ እንደሆነ ጊዜ ያሳየናል።
የሚያዋጣውማ
የጦርነቶች ማብቂያ የሰላም ድርድሮች ናቸው። የዓለምን ታሪክ መዛግብት ያመለከቱትም ያስተማሩትም ይህንን ነው። በቅርብም በሩቅም ምናልባት ወታደራዊ መንግሥታት አገር መርተው፣ሕዝብ ገዝተው ይሆናል ግን የሕዝብን ልብ አልገዙም፤ በጉልበት አገር ገዝተው ይሆናል፤ ግን መርጧቸው አላስተዳደሩትም።
በአረር፣ በወረራ፣በዝርፊያና በስርቆት የተገነባ አገር የለም። የፖለቲካ ልዩነቶችን በንግግር/በድርድር እንጂ፤በጦርነት ያለቀባቸው አገሮች በዓለም ታሪክ አሉ ማለት ያስቸግራል። አቧራው ከጨሰ በኋላ መነጋገር ስለማይቀር። ‘’ሰላም ከክብ ጠረጴዛ ዙሪያ እንጂ፤ሁሌም ከጦር ሜዳ አትገኝም’’የተባለውም አለ ነገር አይደለም። እኛ ዛሬ ባለንበር ሁኔታ የንግግር በሮች ሁሉ ተጠርቅመዋል። ሰላምና ዕድገት ናፋቂው ወገን ወደ ጦርነት እንዳይገባ ልዩነቶችን ለመፍታት ሞክሯል። የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በዚያኛው ወገን ስላልተፈለጉ ነገሮች ሁሉ ተበላሹ እንጂ።
‘’ቀድሞ ነበር እንጂ፤
መጥኖ መደቆስ
አሁን ምን ያደርጋል፤
ድስት ጥዶ ማልቀስ።’’ እንደተባለው ማለት ነው።
አማራጮቻችን
አማራጮቹ በቁጥር ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ። ሲጠቃለሉ ግን አንድ ይሆናሉ። ከምንም በላይ ለሰላም መቆምና ቅድሚያ ሰጥቶ መሥራትን ይጠይቃል። ካለ ሰላም ምንም ማምጣት ስለማይቻል። የውጭና የሩቅ ኃይሎች እንኳን መዋጋት በማይፈልጉበት በዚህ ዘመን የትሮይ ፈረስ መሆን አያስፈልግም። ይሁንና ለሠላ ሲባል ግን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አሳልፎ የሚሰጥ መንግሥትም ሆነ ህዝብ እንደሌለ ሊሰመርበት ይገባል። ኢትዮጵያዊነትን አምኖ መቀበልና ያንንም መተግበር ያስፈልጋል። የስም ኢትዮጵያዊነት ከ30 ዓመታት በኋላ ማክተም አለበት። የትናንት ኢትዮጵያዊነት ቢያበቃ መልካም ነው። አያዋጣምና።
በተረፈ በዚህች በችግሮች በተሞላች ዓለም ከድህነት፣ ከኋላ ቀርነትና ከረሃብ የምውጣው ተደጋግፈን ነው። በአንድ በኩል ዓለም ወደ አንድ መንደር መጥታለች። ይህንንም በበጎ መልኩ ወስዶ ችግሮችን ለማቃለል መጠቀም ያሻናል። ታዲያ ኢትዮጵያውያን ሰላምና ዴሞክራሲን ከወደድን፣ ዕድገት የምንፈልግና የተሻለ ሕይወት ለመምራት ካሻን፤ የሚቸግረን ነገር የለም።
በዓለም ተምሳሌት የሚያደርጉን በርካታ ነገሮች ያሉን፣በተፈጥሮ ሀብት የታደልን፣አኩሪ ታሪክ፣ባህልና ቅርሶች ያለን ሕዝብ ነንና አንድነታችንን አስከብረን፣ ብዝኃነታችንን አስጠብቀን ከቀጠልን እንደ እኛ ማንም የለም። ታሪክ ሠሪ እንጂ፤ የጎደፈ ታሪክ ባለቤት መሆን የለብንም።
በምንቀይረው ዘመን
ዘመን አያመጣው የለ። ጥቁር ጠባሳ ያረፈበትን አንድ ዓመት በመቀየር ላይ ነን። ነገን ከዛሬ ብሎም ከትናንት የተሻለ ለማድረግ መትጋት እንጂ፤የቆሸሸና ያደፈ ታሪክ ይዘን መሻገር የለብንም።
ከምንም በላይ ሰላም ያስፈልገናል። የወደመውንና የፈረሰውን መልሶ ማቋቋም ሌላው የቤት ሥራችን ነው። በምግብ ራስን መቻልና በሽታዎች መከላከልም ቢሆን ካልተባበርን አይፈቱም። ከምንም በላይ አንድነትና ተደጋግፎ መቆምን ይጠይቃሉ።
እናም ከዘመነ መሳፍትን የተማርን ኢትዮጵያውያን፣ የአንድነትን ጥቅም የምናውቅ የአንዲት አገር ልጆች ዳግም ከፋፋዮች
ኢትዮጵያዊነት-ያኔና ዛሬ
ያኔና 2013
እያጠናቀቅን ያለው 2013 የልጅነት ዘመኔን ያስታውሰኛል። በብዙ መልኮቹ ወደ ኋላ ወስዶኝ እያለፈም ነው። ከአገሬ ሰላምና ደህንነት ጋር የተያያዝነውን ብቻ ላንሳ። ’’ሁሉም በአገር ነው’’ እንዲሉ።
ያኔ ሶማሊያ የአገራችንን መሬት ለመውሰድ ወረረችን። በምሥራቅ እስከ አዋሽ 700 ኪሎ ሜትር ድረስ ዘልቃ ‘’የታላቋን ሶማሊያ’’ ህልም ለማሳካት ሞከረች።
አሁን ከአንዱ የአገራችን ክፍል ሌሎቹን የአገሩን ሕዝብ የሚወጋ አካል ጦር ሰብቆብናል። ወገን በወገኑ ላይ ዘምቶ አንድ ለ11 የሚባል ዓይነት ጦርነት ውስጥ ገብተናል።‘’ላታመልጪኝ አታሩጪኝ’’ ዓይነት ይመስላል ጦርነቱ።
ኢትዮጵያ ለማስተዳደር አጋጣሚ የፈቀደለትን ዕድል ያበላሸ ቡድን በሚገርም ሁኔታ ዳግም ሥልጣን፣ የአገር ሀብትና ጥቅም ለመንጠቅ በጦርነት አዲስ አበባ ገብቶ ሊያስተዳድረን እየሞከረ ነው። ያኔ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት በህቡዕ ለመታገል ውጋት የሆኑበት ሁኔታም እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ። ዛሬም ማንነትን ለማስከበር ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ያልተመቻቸው ወገኖች ሽብር ሲፈጥሩ ይታያሉ።
ሁሌም ሰላምና መረጋጋት የሚናፍቀውን የአፍሪካ ቀንድ ጂኦ ፖለቲክስ ለማቃወስ በእሳት ላይ ነዳጅ ለመጨመር ያኔም ተሠርቷል። ዛሬም ጦርነቱን ወደ ጎረቤት አገሮች ለማስፋፋት ሲሞከርም ይታያል። አልሆነም እንጂ። ኢትዮጵያውያን ያኔም አሁንም አንድ ሆነን የወጣንበት ታሪክ ገጥሞናል። ከሃዲዎችና ባንዳዎችን ቀንሰን። ያኔም ኢትዮጵያን የማዳን ዘመቻ ተካሂዷል። ዛሬም ይህቺን ታሪካዊ ጥንታዊ አገር ለማዳን እየተዘመተ ነው።
ዘመቻ + ድጋፍ
የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ባቀረቡት የእናት አገር 300ሺህ ሕዝባዊ ሠራዊት(ሚሊሺያ)አዘመቱ። ዛሬ ደግሞ መከላከያ ሠራዊትን ብቻ የተቀላቀሉትን ወጣቶች ብቻ መመልከት በቂ ይመስለኛል።
የአገሩን ሉዓላዊነትና አንድነት ለማስከበር እናቶቻችን ገብስ ፈትገው በሶ አዘጋጅተዋል። ዳቦ ቆሎና ጭኮ አሰናድተዋል። አርሶ አደሮች በሬዎቻቸውን ለግሰዋል። የገንዘብ አስተዋጽኦም በገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ተደርጓል። ዛሬ በተመሳሳይ ሁኔታ ስንቅ ተዘጋጅቷል። በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የታሸገ ውሃ መጨመሩ ብቻ ለየት ያደርገዋል እንጂ፤ለሠራዊቱ ምን የማይደረግ ነገር አለ!! ያኔም ሆነ ዛሬም ራሱን፣ገንዘብና የዓይነት ድጋፍ የሚያደርግ ሕዝብ ያላጣች ድንቅ አገር እንዳለችው በተግባር መስክሯል።
እውነተኛ ኢትዮጵያዊ በአገሩ ጉዳይ የማይደራደር ሕዝብ መሆኑን ለዓለም እያሳየ ነው።
‘’ወተቱን እንጂ…..ላሚቱን ‘’
ኢትዮጵያዊነት በከረረ ማንነትና ብሄርተኝነት በሽታ ታሞ ከሩብ ምዕተ ዓመታት በላይ በሥልጣን ላይ በነበረው አስተዳደር አልጋ ላይ ቆይቷል። ለዜግነት ወይም ለይለፍ ብቻ የተዘጋጀ እስኪመስል። አስተዳዳሪዎቻችን የማይወዷትን አገር ይመሩ ነበር።
ይህንንም አመለካከታቸውን ለማወቅ ሩቅ መሄድ አያስፈልግም። በሐምሌ 2013 መግቢያ ላይ አሳይተውናል። መንግሥት የትግራይ ክልልን ለቅቆ ከወጣ በኋላ የጥሞና ጊዜ ሰጥቶ ነበር። አንድ በጀት ዓመት ተጠናቅቆ ወደ ሌላ በጀት በተሸጋገርንበት ወቅት የፌዴራል መንግሥት ለክልሉ 12 ቢሊዮን ብር በጀት መመደቡን ስለሚያውቅ ‘’በጀቴን አሁኑኑ ቁጭ’’ የሚሉት ጥያቄ ማቅረብ ጀመረ።
የፌዴራሉ መንግሥት በ2013 በጀት ዓመት ለክልሉ 8 ቢሊዮን ብር በጀት ተመድቦ 100 ቢሊዮን ብር ለመልሶ ማቋቋም እንዳወጣ የሚያውቀው ቡድን ድጎማው እንዳልተላከለት እያወቀ፤ የአዲሱን በጀት ዓመት አምጡ የሚለው ሊዋጋበት እንደሆነ ልቡ እያወቀ ‘’የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን አባል እንደመሆኔ’’ ማለቱን ባንጠላበትም፤ሰላም ባልወረደበትና መግባባት ባልተፈጠረበት ‘’አምጡ’’ማለቱ ያስተዛዝባል። በፍቅርና በሰላም ሁሉም አለ።‘’አራዳ’’ነት ሲያስነቃ ግን ምንም የለም።
ዱሮውንም ኢትዮጵያዊነትን የማይወደው ቡድን በስሟ ተጠቀመ። መዘበረ። ዘረፈ። ሕዝብ ተፍቶት ከሥልጣን ሲወርድ፤መቀሌን መሸሻና መጠጊያው አድርጎ ሲመቸው ኢትዮጵያዊ መስሎ፤ካልተመቸውም ደግሞ
ወደ የገንጣይ አስገንጣይ ጨዋታውን ካርታ መዝዞ ይጫወታል። እናም ‘’ውሳኔ ሕዝብ’’ ናፈቀኝ ይለናል። በአጭርና ግልጽ ቋንቋ ሲቀመጥ ለእነሱ ኢትዮጵያ ላም ነች። ወተቷና የወተት ተዋጽኦዋ ይፈለጋል። ላሚቱ ግን አትፈለግም።
ጠዋት ኢትዮጵያዊ የሆነው ቡድን፣ሲመሻሽ ‘’ራስን በራስ የማስተዳደር መብታችን ለማስከበር መብት ያለን ክልል በመሆናችን ሕዝበ ውሳኔ ልንጠይቅ እንችላለን’’ ሲል ታገኙታላችሁ ‘’የኢትዮጵያ ማንነት፣ታሪክ፣ባህልና ቅርስ መሠረት የሆነውን ክልልና ሕዝብ ለመነጠል ይሞክራል-ፖለቲካና ማንነትን ለማገናኘት ይሞክራል።
ነገር ግን በየአጋጣሚው ሰልፍ የወጡት ወገኖቼ ’’የትግራይ ሕዝብ አካላችን፤ህወሓት ጠላታችን!’’ በአንድነትና በአብሮነት መኖርን የሚመኘው ኩሩው ሕዝባችን ሕዝቡን ከፈላጭ ቆራጩ ኮሙኒስታዊው ህወሓት መለየት የቻለ ሕዝብ ነው። በዚህም እንኮራለን።
ያልደበዘዘው ቀለም
በ1970ዎቹ የማውቃት ኢትዮጵያ በጠባብ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ ተውጣ እንዳልቀረችና ደማቁ ቀለሟ እንዳልፈዘዘ በ2013 አሳይታኛለች። ይህ ደግሞ ዳግም በኢትዮጵያዊነቴ እንደ ሌሎቹ ወገኖቼ እንድኮራ፣ ከአንገቴ ቀና ብዬ ለመራመድ አስችሎኛል።
ያኔ ከመሪው በተደረገለት የእናት አገር ጥሪ ተምሞ ወደ ታጠቅ ጦር ሠፈር ገብቶ ለድል የበቃው ሚሊሺያ ፤ዛሬ ደግሞ መከላከያ ሠራዊትን የተቀላቀሉት ወጣቶች በወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት ገብተው አገር ለማዳን ሥልጠና ሲወስዱ ማየት በራሱ ያኮራል። ጠላትንም ያርበደብዳል።
ዛሬም ዜጎች ለአገር ለህልውና ለመዋደቅ ዝግጁነታቸውን በተግባር አሳይተዋል። ከአካባቢ ሚሊሺያነት እስከ መከላከያ ሠራዊት አባልነት አገርና ሕዝባቸውን ለመታደግ ሥልጠና ወስደው ውጊያውን ተቀላቅለዋል። በህልውና ለመጣ መልሱ ህልውናን ማስጠበቅ በመሆኑ።
ዛሬ የገጠመን የአንድን ክልል ሕዝብ ‘’ወራሪ’’ አድርጎና አስደርጎ ሁለት ክልሎችን ወርሮ ብሄር ተኮር ጥቃት በመፈጸም ሰዎችንና የቀንድ ከብቶችን ገድሏል፣ንብረት አጥፍቷል፣ ሀብት ዘርፏል፣ታሪክና ቅርሶችን አጥፍቷል፤ባህል አበላሽቷል።
የያኔው ወራሪ ጎረቤት አገር የውስጥ ችግሮችን አይቶ ሁኔታዎች ተመችቶኛል ሲል ወረራ ፈፀመ።
የዛሬው የውስጥ የፖለቲካ ችግሮችን በውይይት ባለመፍታት የአገር መከላከያ ሠራዊትን የጦር መሣሪያዎች ተማምኖ መንፈቅለ መንግሥት ለማካሄድ ሞከረ።‘’ሕዝባዊ ኃይል’’ን ተጠቅሞ ወረራን ከነግሳንሱ ተጠቅሞ ጥፋት አደረሰ። በያኔውና በአሁኑ መካከል ያለው ልዩነት በአብዛኛው የጊዜ ብቻ መሆኑ ይደንቃል።
ዓለም የገጠሟትን ችግሮችን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገዶች ለመፍታት ቅድሚያ በምትሰጥበት ዘመን የ”እኔን ብቻ’’ ካልሆነ ብሎ ወደ ጦርነት መግባት ‘’መተላለቅ’’ ካልሆነ ማንን እንደጠቀመ 2013 አሳይቶናል። ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መነጋገርን የመሰለ ምርጥና ተተኪ የማይገኝለት መፍትሔ ባለበት አገር 30 ዓመታት ወደኋላ መጓዝ ‘’ተገትሮ መቅረት’’እንጂ ሌላ ስያሜ ያለው አይመስለኝም።
በእኔ ግምት በክፍለ ዘመኑ ‘’አሳፋሪ’’ የተባለው ጦርነት በ2013 ገጥሞናል። የአንድ ብሄር ፖለቲካ ድርጅት የበላይነቱን ለማንገስ ሕዝብን ጋሻ አድርጎ ሌሎች የአገሩን ዜጎች መውጋት የሚያኮራም የሚያስደስትም ታሪክ አይደለም። ባይሆን አንገት የሚያስደፋ እንጂ።
ዳግም ወደ ጦርነት ‘’መሥመራችን ኃይላችን’’ ብሎ ሕዝቡን ተዋጊ አድርጎ ለ50 ዓመታት ያህል ያልተለወጠው፣ ቋሚና የማይለዋወጥ የትግል መሥመር ይዞ በተለወጠች ዓለም ያልተለወጠ ኮሙኒስታዊ ርዕዮተ ዓለም አንግቦ ሕዝብን አግቶ ወደ ጎረቤት ክልሎች መዝመት በተስፋፊነትና በወራሪነት መግባት ማንን ለመጥቀም እንደሆነ የሚያውቁት ራሳቸው ብቻ ናቸው። መነጠልና መገንጠል ምን ይዞ ጉዞ እንደሚሆን ራሱም በአግባቡ ያወቀው አይመስልም።
አካሄዱ የኢትዮጵያዊ ሳይሆን፤ የውጭ ጠላቶች የሚመስል አንጃ ገጥሞናል።‘’አገር ተከፋፈለች፣አንድነቷ የላላ፣ሕዝቧ ተለያየ ብሎ ሁኔታዎችን የሚገመግምና ለውጭ ጠላቶች አሳልፎ መስጠት ከሃዲነትም ነው። ኢትዮጵያውያን እንዲህ አይደለንም።
ድህነት፣ኮቪድ 19፣ የኑሮ ውድነትን፣የአንበጣ ወረራን ተቋቁሞ መኖር በከበደበት ዘመን ጦርነትን እንደ አንድ አማራጭ ወስዶ ይዋጣል ማለት ማንን ለመጥቀም?
ይበታተናሉ ተብለው የሚሰባሰቡት፣አለቀላቸው ብለው ሲያሟርቱ በአዲስ መልክ አድገውና ተመንድገው ብቅ የሚሉት፣ተስፋ የላቸውም ብለው ተስፋ ሊያሳጡን ሲሞክሩ ዛሬም ተስፋ እንዳላቸው በአንድነት ቆመው በተግባር የሚያሳዩ አገር ዜጎች መሆን ያኮራል።
በውጭ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን አንዷንና መለዋወጫ የሌላትን አገራቸውን ‘’አትንኩብን’’፣የእኛን ጉዳይ ለእኛው ተውት’’ ብለው የአውሮፓና የአሜሪካን አደባባዮች ሲያጥለቅልቁ የከረሙት ‘’አንድ ነን’’ ብለው ነው በተቃራኒው የሽብር፣ የመጠፋፋትና የሽቆልቁሎሽ ጉዞ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ወገኖችም ሰልፍ ወጥተዋል። ይህንን አንድነቱን ከልዩነቱ ጋር አክብሮና አስከብሮ የኖረ ሕዝብ የሚጠቅመው የቱ እንደሆነ ጊዜ ያሳየናል።
የሚያዋጣውማ
የጦርነቶች ማብቂያ የሰላም ድርድሮች ናቸው። የዓለምን ታሪክ መዛግብት ያመለከቱትም ያስተማሩትም ይህንን ነው። በቅርብም በሩቅም ምናልባት ወታደራዊ መንግሥታት አገር መርተው፣ሕዝብ ገዝተው ይሆናል ግን የሕዝብን ልብ አልገዙም፤ በጉልበት አገር ገዝተው ይሆናል፤ ግን መርጧቸው አላስተዳደሩትም።
በአረር፣ በወረራ፣በዝርፊያና በስርቆት የተገነባ አገር የለም። የፖለቲካ ልዩነቶችን በንግግር/በድርድር እንጂ፤በጦርነት ያለቀባቸው አገሮች በዓለም ታሪክ አሉ ማለት ያስቸግራል። አቧራው ከጨሰ በኋላ መነጋገር ስለማይቀር። ‘’ሰላም ከክብ ጠረጴዛ ዙሪያ እንጂ፤ሁሌም ከጦር ሜዳ አትገኝም’’የተባለውም አለ ነገር አይደለም። እኛ ዛሬ ባለንበር ሁኔታ የንግግር በሮች ሁሉ ተጠርቅመዋል። ሰላምና ዕድገት ናፋቂው ወገን ወደ ጦርነት እንዳይገባ ልዩነቶችን ለመፍታት ሞክሯል። የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በዚያኛው ወገን ስላልተፈለጉ ነገሮች ሁሉ ተበላሹ እንጂ።
‘’ቀድሞ ነበር እንጂ፤
መጥኖ መደቆስ
አሁን ምን ያደርጋል፤
ድስት ጥዶ ማልቀስ።’’ እንደተባለው ማለት ነው።
አማራጮቻችን
አማራጮቹ በቁጥር ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ። ሲጠቃለሉ ግን አንድ ይሆናሉ። ከምንም በላይ ለሰላም መቆምና ቅድሚያ ሰጥቶ መሥራትን ይጠይቃል። ካለ ሰላም ምንም ማምጣት ስለማይቻል። የውጭና የሩቅ ኃይሎች እንኳን መዋጋት በማይፈልጉበት በዚህ ዘመን የትሮይ ፈረስ መሆን አያስፈልግም። ይሁንና ለሠላ ሲባል ግን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አሳልፎ የሚሰጥ መንግሥትም ሆነ ህዝብ እንደሌለ ሊሰመርበት ይገባል። ኢትዮጵያዊነትን አምኖ መቀበልና ያንንም መተግበር ያስፈልጋል። የስም ኢትዮጵያዊነት ከ30 ዓመታት በኋላ ማክተም አለበት። የትናንት ኢትዮጵያዊነት ቢያበቃ መልካም ነው። አያዋጣምና።
በተረፈ በዚህች በችግሮች በተሞላች ዓለም ከድህነት፣ ከኋላ ቀርነትና ከረሃብ የምውጣው ተደጋግፈን ነው። በአንድ በኩል ዓለም ወደ አንድ መንደር መጥታለች። ይህንንም በበጎ መልኩ ወስዶ ችግሮችን ለማቃለል መጠቀም ያሻናል። ታዲያ ኢትዮጵያውያን ሰላምና ዴሞክራሲን ከወደድን፣ ዕድገት የምንፈልግና የተሻለ ሕይወት ለመምራት ካሻን፤ የሚቸግረን ነገር የለም።
በዓለም ተምሳሌት የሚያደርጉን በርካታ ነገሮች ያሉን፣በተፈጥሮ ሀብት የታደልን፣አኩሪ ታሪክ፣ባህልና ቅርሶች ያለን ሕዝብ ነንና አንድነታችንን አስከብረን፣ ብዝኃነታችንን አስጠብቀን ከቀጠልን እንደ እኛ ማንም የለም። ታሪክ ሠሪ እንጂ፤ የጎደፈ ታሪክ ባለቤት መሆን የለብንም።
በምንቀይረው ዘመን
ዘመን አያመጣው የለ። ጥቁር ጠባሳ ያረፈበትን አንድ ዓመት በመቀየር ላይ ነን። ነገን ከዛሬ ብሎም ከትናንት የተሻለ ለማድረግ መትጋት እንጂ፤የቆሸሸና ያደፈ ታሪክ ይዘን መሻገር የለብንም።
ከምንም በላይ ሰላም ያስፈልገናል። የወደመውንና የፈረሰውን መልሶ ማቋቋም ሌላው የቤት ሥራችን ነው። በምግብ ራስን መቻልና በሽታዎች መከላከልም ቢሆን ካልተባበርን አይፈቱም። ከምንም በላይ አንድነትና ተደጋግፎ መቆምን ይጠይቃሉ።
እናም ከዘመነ መሳፍትን የተማርን ኢትዮጵያውያን፣ የአንድነትን ጥቅም የምናውቅ የአንዲት አገር ልጆች ዳግም ከፋፋዮችን መታገስ የለብንም። ይሄኛው ዘመን ስንሰናበት ብሩህ ዘመን እንደምናመጣ በተስፋ ነው። ደግሞም ተፈጻሚ እንደሚሆንም በመተማመን።
አንድ ሆነን የሚያስደምም ታሪክ እንሠራለን!!!
ከብርሃኑ ተሰማ
አዲስ ዘመን መስከረም 3/2014
ን መታገስ የለብንም። ይሄኛው ዘመን ስንሰናበት ብሩህ ዘመን እንደምናመጣ በተስፋ ነው። ደግሞም ተፈጻሚ እንደሚሆንም በመተማመን።
አንድ ሆነን የሚያስደምም ታሪክ እንሠራለን!!!
ከብርሃኑ ተሰማ
አዲስ ዘመን መስከረም 3/2014