የኦሮሚያ ክልል የመሬት አስተዳደር አጠቃቀም በተገቢው መልኩ እንዲተገበር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
የቢሮው ሃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው በክልሉ በ25 ከተሞች ባለፈው አመት የተጀመረው የማስተካከል ስራ በዚህ አመትም ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።
በለገጣፎ 347 ቤቶች እና በአጥር የተከለሉ ይዞታዎች ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑንም የቢሮ ሃላፊው ተናግረዋል።
በተደረገው ቅድመ ማጣራትም ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ ቦታዎችና ይዞታዎች ከከተማዋ ማስተር ፕላን የማይጋጩ በመሆናቸው፥ በህጋዊ ይዞታዎች ውስጥ እንዲካተቱ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ህግን የማስከበርና ከተሞችን በታለመላቸው ፕላን እና የእድገት መስመር መሰረት እንዲያድጉና የህዝቦች ፍትሃዊ የሃብት ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የሚሰራው ስራ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም በአሰራር ሂደት የሚያጋጥሙ ግድፈቶች ካሉ ለማጣራትና መፍትሄ ለመስጠት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ትዕዛዝ የተዋቀረ ግብረ ሃይል ወደ ስራ መግባቱንም አስታውቀዋል።
ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው ተዋቀረው ግብረ ሃይል አጣርቶ በሚያቀርበው ሪፖርት መሰረትም የእርምት እርምጃ እንደሚሰወድም ጠቅሰዋል።
አየተዋቀረውለፈ ግን በህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃና ህግን የማስከበር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት።