የህፃናት የተሟላ እድገት መኖር ሰው በመሆን ሂደት ውስጥ ጤናማ ለመሆን መሠረት ነው። ህፃናት ደስተኛና ጤናማ ሆነው እንዲያድጉ ከሚያስፈልጓቸው ነገሮች አንዱና ዋነኛው ምግብ ነው፤ ለጤናማ ዕድገት ጤናማ ምግብ እጅግ ወሣኝ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ለዛሬም ዶክተር ፋሲል መንበረ ስለ ጤናማ አመጋገብ ለህፃናት በተለይም ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ላሉት ይህን ብለዋል። ህፃናት ስድስት ወር ከሞላቸው በኋላ የእናት ጡት ወተት ለብቻው የምግብ ፍላጎታቸውን ስለማያሟላ ተጨማሪ ሌሎች ምግቦችን መጀመር ይኖርባቸዋል። በዚህ የዕድሜ ክልል ህፃናት እድገታቸው ፈጣን ስለሚሆን በቂ የሆነ ምግብ ካላገኙ ለሰውነታቸው የሚሆን በቂ ኃይል አያገኙም፤ በመቀጠልም ሰውነታቸው ለመቀጨጭ እና መቀንጨር ይዳረጋል:: በተጨማሪም የበሽታ የመከላከያ ሀይላቸው (Immunity) ዝቅተኛ ስለሚሆን ለተለያዩ ኢንፌክሽኖች ተጋላጭ ይሆናሉ:: ከስድስት ወር በፊት ሌሎች ምግቦችን መጀመር ለተቅማጥ እና ትውከት፣ የጡት ወተት መቀነስ እና የመሳሰሉት ችግሮችን ያመጣል::
ተጨማሪ ምግቦችን ዘግይቶ መጀመር የሚያስከትለው ጉዳት ህፃኑ በቂ የሆነ ክብደት እንዳይጨምር እና የተለያዩ ንጥረ ነገሮች እጥረት እንዲከሰት ያደርጋል። ከስድስት ወር – ሁለት ዓመት ያሉትን ህፃናት ምን እንመግባቸው? በየትኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ህፃናትም ሆኑ አዋቂዎች የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ይኖርባቸዋል:: የተመጣጠነ ምግብ ማለት መሰረታዊ የሆኑ የምግብ ክፍሎችን የሚያካትት ነው:: እነሱም የእህል ዘር፣ ጥርጣሬ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ወተት እና የወተት ምርቶች እንዲሁም እንቁላል እና ስጋ ናቸው:: ከላይ የተጠቀሱትን የምግብ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በቁጥር አድገው በጥራት ወርደው ዛሬ ላይ ቆመዋል።
በሀገራችን ባለፉት 20 ዓመታት መንግሥት የትምህርት ተደራሽነቱ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ መጓዙን የትምህርት ባለሙያዎች እንደ ስህተት ያነሱታል። ጥራትን መሠረት አድርገው የሚጓዙ ተቋማት እንዳይፈጠሩም ማድረጉን ይገልጻሉ። በአብዛኛዎቹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የሚታየው እንዝህላልነት እየጨመረ በመሄዱ ለተማሪ እውቀትን ለመሸጥ መቋቋማቸውን እስከመዘንጋት አድርሷቸዋል ይላሉ። ስለዚህ በጥራት የማይደራደሩ፣ በትምህርት ጥራታቸው ሊመሠገኑ የሚገባቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለመፍጠር ከታሰበ ራሱን የቻለ ገለልተኛ ተቋም መመሥረት ያስፈልጋል። በተገቢው መንገድ የሚጓዙትን አንጽሮ፣ የሚያወጣ በትምህርት ጥራታቸው ለውጥ ያላመጡትን ተከታትሎ ርምጃ መውሰድ የሚያስችል ማዕቀፍ መዘርጋት ያስችላል። በመንግሥትም በሀገሪቱ በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት መጓደል እንቅልፍ የነሳው ችግር መሆኑን በማመን ለመፍትሄው እንደሚሰራ በተደጋጋሚ ሲናገር ይሰማል። በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የተለያዩ ማሻሻያዎች የተደረጉ ሲሆን፤ ከሰሞኑ ደግሞ የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ምክር ቤትን እንዲመሠረት መደረጉ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ እንደሚሆን ታምኗል።
የትምህርት ጥራት ችግርን ለመፍታት የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ምክር ቤት ማቋቋም አስገዳጅ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ምክር ቤቱ በሀገሪቱ የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲያረጋግጡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ምሩቃንን ለማፍራት ፋይዳ የሚኖረው ገለልተኛ ምክር ቤት መሆኑ ተነግሯል። በሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ በአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ምክር ቤት ምሥረታ ላይ የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሣሙኤል ኡርቃቶ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ይህንኑ አረጋግጠዋል።
ዶክተር ሣሙኤል እንደተናገሩት በእውቀትና በክሂሎት የዳበሩ ተማሪዎችና ተፈላጊነት ያላቸው ባለሙያዎችን ማፍራት ይጠበቅብናል። የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመፍታት የሙያ ማህበራትን ያሣተፈ የትምህርት ጥራት ምክር ቤት ተቋቁሟል። በምክር ቤቱም የሙያ ማህበራት የትምህርት ጥራትን በየጊዜው እንዲፈትሹ፣ ጥናት እንዲያካሄዱና ስታንዳርድ እንዲያወጡ የሚያደርግ ይሆናል። የትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች የሀገሪቱን ፍላጎትና ገበያ ማዕከል ያደረጉ እንዲሆኑ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርትና ሥልጠና ጥራትና አግባብነትን ለማስጠበቅ እንዲቻል የሚኖረው ሚና ወሣኝ ነው። ከዚህ ባሻገር የሀገሪቱ የትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲመዘኑ እና ተቀባይነት እንዲኖራቸው የሚያግዝ ይሆናል።
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምሩቃን በአገር ውስጥና በውጭ ተፈላጊነታቸው እንዲጨምር የትምህርት ጥራት ችግርን ለመፍታት እየተሰራ ስለመሆኑ ዶክተር ሣሙኤል ገልፀዋል። የተቋቋመው ምክር ቤት የትምህርት ጥራት ችግርን በመፍታት ከተቋማቱ የሚመረቁ ተማሪዎች በአገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊነታቸው እንዲጨምር በማድረግና ሌሎች ትላልቅ ሥራዎች ይሰራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ የሚገኙ የሙያ ማህበራት የትምህርት ጥራት ምክር ቤት ማቋቋማቸውን ያመላከቱት ደግሞ
አይነቶችን ያካተት የተመጣጠነ ምግብ ለልጅዎ በተለያየ መንገድ ማዘጋጀት ይቻላል:: በሀገራችን የተለመደው አሰራር የምጥን ዱቄት ይባላል:: ይኼም በውስጡ የተለያዩ የእህል ዘሮችን ማካተት ይቻላል። ለምሳሌ ሦስት እጁ ከእህል ዘሮች ማለትም የተፈተገ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ጤፍ፣ አጃ እና የመሳሰሉትን አድርጎ አንድ እጁን ደግሞ ከጥራጥሬ ዓይነቶች ባቄላ፣ ሽምብራ፣ አተር፣ ምሥርንና ኦቾሎኒ ማካተት ይኖርበታል::
ለልጅ ምግብ መስራት ስንጀመር ምን ያህል ነው? ተብሎ ለሚነሳ ጥያቄ ከስድስት ወር እስከ ስምንት ወር – በቀን ከሁለት እስከ ሦስት የቡና ሲኒ፤ ከዘጠኝ ወር እስከ አንድ ዓመት ድረስ – ከአራት እስከ አምስት የቡና ሲኒ፤ ከአንድ ዓመት በላይ ግን በሲኒ መለካት አስፈላጊ አይደለም። ሆኖም ግን ሦስት ዋና ዋና የምግብ ሰዓቶችን ጠብቆ በመስጠት በተጨማሪ ደግሞ በመሃል በመሃል ሁለት መክሰሶችን መስጠት ይገባል:: የቡና ሲኒው ቢያንስ 70 ሲሲ (ሚሊ ሊትር) የሚይዝ መሆን አለበት። እድሜያቸው ከስድስት እሰከ ስምንት ወር ላሉ ህፃናት ከአጥሚት ትንሽ ወፈር ያሉ ምግቦች ይመከራሉ:: እድሜያቸው ከስምንት እስከ 12 ወር ለሆናቸው ደግሞ በከፊል ጠጣር (semi solid) ወይም ለስለስ ያለ ገንፎ በቀን ከአራት እስከ አምስት ጊዜ መመገብ ይኖርባቸዋል።
ለልጅዎ የምጥን ገንፎ ሲያዘጋጁ ከውሃ ይልቅ በወተት ቢያዘጋጁት የበለጠ ገንቢ እና በቂ ካሎሪ ያለው ምግብ ማድረግ ይቻላል። በዚህ የዕድሜ ክልል ላሉ ህፃናት ምግብ ስንጀምር የታሸጉ ምግቦች (Processed food)ን ትተን በተፈጥሮ ከእህል ዘሮች ከተዘጋጁ እና በተለመዶ ምጥን ከሚባሉ ምግቦች ብንጀምር መልካም ነው:: እነዚህ ምግቦች በቀላሉ የሚፈጩ እና በውስጣቸው ከፍ ያለ የብረት ማዕድን ስለሚይዙ የደም ማነስን ይከላከላሉ። በተጨማሪም ኃይል ሰጪ (carbohydrate) እና ገንቢ (protein) የሆኑ ምግቦች ናቸው::
ህጻናት ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ከሆኑ 350 ሚሊ ሊትር እንዲሁም ከሦስት እስከ አራት ዓመት ከሆኑ 475 ሚሊ ሊትር የላም ወተት መውሰድ ይችላሉ። ነገር ግን ከአንድ ዓመት በፊት የላም ወተት ማስጀመር ለሚከተሉት የጤና ችግሮች የሚያጋልጥ ሲሆን፤ ዝቅተኛ የአይረን (ብረት) ማዕድን መጠን ስላለው ለደም ማነስ ችግር ያጋልጣል። ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ስላለው ለዓይነት አንድ የስኳር ህመም ያጋልጣቸዋል። የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ ያስከትላል፤ የወተት አለርጂ የአንጀት መቆጣት ላክቶዝ ንጥረ ነገር በሰውነት ውስጥ አለመኖር በወተት ውስጥ ለሚገኘው የላክቶዝ ንጥረ ነገር መብላላት አለመቻል ያጋልጣቸዋል።
ከሁሉም የምግብ ዓይነት ሣይበዛም ሣያንስም አመጣጥኖ ህፃናትን መመገብ ጠቀሜታው የላቀ ነው። ከምግብም በሻገር ንፅህናው የተጠበቀ ውሃን ማጠጣትም ጠቃሚ ነው። ልጆች በተገቢ መልኩ እንዲያድጉ ወላጆች በአቅራቢያቸው የሚገኘውን ምግብ አመጣጥነው መመገብ ይኖርባቸዋል።
አስመረት ብስራት
አዲስ ዘመን ሰኔ 7/2013