መላኩ ኤሮሴ
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበችው የኢኮኖሚ እድገት፣ የሕዝብ ቁጥር መጨመር እና የግሉ ዘርፍ መነቃቃት የፈጠረው ነው። ባለፉት ዓመታት እመርታ ከተመዘገበባቸው ዘርፎች የከተሞች እድገት አንዱ ተጠቃሽ ነው ።ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚነሱ አንዳንድ ውስንነቶች እንደተጠበቁ ሆነውም ቢሆን በሀገሪቱ ከፍተኛ የከተሞች መስፋፋት እና ዕድገቶች መመዝገባቸው አሌ የሚባል አይደለም።
የከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሰው የሕዝብ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል ።በሀገሪቱ በከተሞች የሚኖር ሕዝብ ቁጥር ከ20 በመቶ በላይ የደረሰ ሲሆን፤ የከተሞች መስፋፋት ምጣኔ ደግሞ 4 ነጥብ 9 በመቶ መሆኑን በአፍሪካ ሀገራት በቤቶች ፋይናንስ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናት የሚያካሂደው የአፍሪካ ተመጣጣኝ የቤቶች ልማት ፋይናንስ ማዕከል(ሲ ኤ ኤች ኤፍ) የተሰኘ ተቋም አረጋግጧል ።ከዚህ ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዘው ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡
ፈጣን የከተሞች መስፋፋት፣የከተማ ኢንቨ ስትመንት ፍላጎቶች እና የመሰረተ ልማት ግንባታ እንዲፋጠን ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት የተቋሙ ጥናት አመላክቷል ።በከተሞች አካባቢ ኢንቨስትመንት፣ መሰረተ ልማት እና አገልግሎት አሰጣጥ መስፋፋት በርካቶች ወደ ከተሞች እንዲፈልሱ አንዱ ሳቢ ምክንያት መሆኑን ጥናቱ ጠቅሷል ።
ይህ በአዲስ አበባም የሚታይ እውነታ ነው ።በከተማዋና በዙሪያው ኢንቨስትመንት፣ መሰረተ ልማት እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት መስፋፋትን ተከትሎ በርካቶች ኑሯቸውን በከተማዋና ዙሪያዋ እንዲያደርጉ ሆኗል ።በከተማዋ የቤት አቅርቦት እና ፍላጎት መካከል ያለው ልዩነት እንዲሰፋም ምክንያት ሆኗል ፡፡
ይህን ተከትሎም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የቤት ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል፡፡በአንድ በኩል የተከማቸ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ሲኖር በሌላ በኩል ደግሞ አነስተኛ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ይስተዋላል ።ይህም በአዲስ አበባ የቤቶች ዋጋ የማይቀመስ እንዲሆን አድርጓል፡፡
የቤቶችን ፍላጎት ለማሟላት መንግስት የተለያዩ ጥረቶችን አድርጓል ።በከተማዋ የተቀናጀ የቤቶች ልማት ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ በርካታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች(የኮንዶሚኒየም)ግንባታ አካሂዷል።
አንዳንድ የሚነሱ ቅሬታዎች እንደተጠበቁ ሆኖ በ100 ሺህዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች የቤት ባለቤት ማድረግ ችሏል ።መንግስት ከሚገነባቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ባሻገር ከግል የቤት አልሚ ዎች(ሪል ስቴት)ጋር በመተባበር በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ቤቶችን ለመገንባት ግብ አስቀምጦ ነበር። ይሁን እንጂ በከተማዋ ከሚስተዋለው የቤቶች ፍላጎት አንጻር እዚህ ግባ የሚባል ሥራ አልተሰራም።
የተገነቡ ቤቶች ከፍላጎት አንጻር እጅግ አነስተኛ መሆን፣ የቤቶች ግንባታ መጓተት እና ተገንብተው ያለቁ ቤቶች በሕገ ወጥ መንገድ መያዛቸው በከተማዋ የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤቶች ችግርን ለመቅረፍ የተሰሩ ስራዎች የሚፈለገውን ውጤት እንዳያስመዘግብ አድርጓል፡፡
በዚህም ዛሬም በርካቶች የከተማዋ ቤተሰቦች ከባድ የመኖሪያ ቤት ችግርን እየተጋፈጡ ይገኛሉ ።ዛሬም የከተማዋ ነዋሪዎች ከሚያገኙት ገቢ አብዛኛውን ለቤት ኪራይ ለመክፈል ይገደዳሉ ።
ሰሞኑን ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ስለከተማዋ ችግሮች መግለጫ የሰጡት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በከተማዋ ውስጥ የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የከተማ አስተዳደሩ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን አብራርተዋል ።የቤት እጥረት ችግርን ለመቅረፍ አንድም በሕገ ወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶችን ከሕገ ወጦች በመውሰድ ለሚገባቸው አካላት ለማስተላለፍ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም መሰረት ባለቤቶቻቸው ያልታወቁ ቤቶች፣ ባለቤቶች መጥተው እንዲያመለክቱ እና የማያመለክቱ ከሆነ ግን ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ለቆጠቡ ሰዎች እንዲተላለፍ መወሰኑን ያብራሩት አቶ ጃንጥራር ይህንንም ውሳኔ ለመተግበር ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል ።
እንደ አቶ ጃንጥራር ማብራሪያ ከዚህ ቀደም ለቤት የቁጠባ ሂሳብ ከፍተው ሲቆጥቡ ለቆዩ የከተማዋ ነዋሪዎች ቤቶቹን ሰርቶ ለማስረከብ እየተሰራ ነው ።ለቤት ቆጥበው የቤት ባለቤት ያልሆኑ ከ600 ሺህ በላይ ቆጣቢዎች በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ ።እነዚህ ቆጣቢዎች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ጥረት እየተደረገ ነው ።
ስለዚህ የተጀመሩትን አጠናቅቆ ለባለቤቶች ለማስተላለፍ ከተማ አስተዳደሩ ጥረት እያደረገ ነው ።የተጀመሩትን የማጠናቀቅ ስራው በትኩረት እየተሰራ ነው ።ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ቤቶችን በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል ።የተጀመሩ ቤቶችን ለማጠናቀቅ የሚያስችል ገንዘብ ከባንክ በብድር መገኘቱንም አስረድተዋል፡፡
ያልተጠናቀቁ ቤቶችን ለማጠናቀቅ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁለት ነገሮች ሊዘነጉ አይገባም። በአንድ በኩል በከተማዋ ያለውን የቤት ችግር ለማቃለል ግንባታዎች በፍጥነት መካሄድ አለባቸው ።በሌላ በኩል በፍጥነት ቤቶቹን ለማጠናቀቅ በሚደረግ ርብርብ የጥራት ጉድለት እንዳይከሰት ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል የሚለው ነው፡፡
ከዚህ ቀደም ግንባታቸው ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ ቤቶችን አጠናቆ ከማስተላለፍ ጎን ለጎን ዜጎች በራሳቸው የቤት ግንባታ የሚያከናውኑበት ሁኔታዎች የማመቻቸት ስራ እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ጃንጥራር፤ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገነቡት የመኖሪያ ቤቶች ባሻገር ለቤት ፈላጊዎች ተጨማሪ አማራጮችን ለመፍጠር የከተማዋ ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው ቤት የሚገነቡበት እድል የሚሰጥ መመሪያ ተዘጋጅቷል ብለዋል ።
በመንግስት ጥረት ብቻ የከተማዋን የቤት ችግር መቅረፍ አዳጋች በመሆኑ ሌሎች አማራጮች ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል ።አቶ ጃንጥራር እንደሚሉት፤ በግንባታ ላይ የሚገኙ ቤቶች ሲጠናቀቁ ከዚህ ቀደም ከነበሩ አማራጮች በተጨማሪ የሚጀመሩ አዳዲስ የቤት ግንባታ መኖራቸውን አመልክተዋል ።ለዚህም በውጭ ሀገራት ካሉ ኩባንያዎች ጋር የመነጋገር እና የተሻለውን አማራጭ የመፈለግ ስራ ባለፉት ወራት ተሰርቷል ።
በመዲናዋ ዘላቂ ችግር ሆኖ ለቀጠለው የመኖሪያ ቤት እጥረት ችግሮች ቀላል መፍትሔዎች የሉም ፣ ምክንያቱም በቂ መጠለያ አለመኖር የአጠቃላይ የሀገሪቱ ድህነት አንዱ መገለጫ ነው ።የተስፋፋ ድህነት እስካለ ድረስ ለሁሉም መጠነኛ መጠለያ በቀላሉ ማቅረብ ከባድ ተግባር ነው ።
ሆኖም በቁርጠኝነት ከተሰራበት የማይፈታ ችግር የለም፡፡ በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች እንደ ሚያመላክቱት፤ ጥሩ ፖሊሲዎች የመጠለያ ችግሮችን ለማቃለል ይረዳሉ ።መንግስት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን የቤት ባለቤት ሊያደርጉ የሚችሉ ፖሊሲዎችን መቅረጽና መተግበር ትኩረት ሊያደርግ ይገባል ።
በከተማዋ የተጀመሩ ቤቶች በታቀደለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ የግንባታ ቁሳቁሶች ዋጋ መናር መሆኑን የተለያዩ አካላት በተለያዩ ጊዜያት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡መንግስት የግንባታ ቁሳቁሶች ዋጋ እንዳይንር አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ።በተቻለ አቅም በአነስተኛ ዋጋ የግንባታ እቃዎችን ለማቅረብ የሚያስችሉ አማራጮች ሊዘረጉ ይገባል፡፡
አዳዲስ ግንባታዎች ይካሄዳል በሚል ያረጁ ሰፈሮችን ያለ ቅድመ ዝግጅት በገፍ የማፍረስ አካሄድ በከተማዋ ለሚስተዋለው የቤት እጥረት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ከሚገኙ ምክንያቶች አንዱ ነው ።በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች ለቤቶች ልማት ተብሎ ቤት ፈርሰው አንዳች ልማት ሳይካሄድ ዓመታት ተቆጥረዋል ።መሰል አሰራር እያስከተለ ካለው ማህበራዊ ቀውስ ባሻገር የቤት ፈላጊዎችን ቁጥር የበለጠ ከፍ ሊያደርግ ይችላል ።
ምክንያቱም በቂ መጠለያ አለመኖር የአጠቃላይ የሀገሪቱ ድህነት አንዱ መገለጫ ነው ።የተስፋፋ ድህነት እስካለ ድረስ ለሁሉም መጠነኛ መጠለያ በቀላሉ ማቅረብ ከባድ ተግባር ነው ።
ሆኖም በቁርጠኝነት ከተሰራበት የማይፈታ ችግር የለም፡፡ በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች እንደ ሚያመላክቱት፤ ጥሩ ፖሊሲዎች የመጠለያ ችግሮችን ለማቃለል ይረዳሉ ።መንግስት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን የቤት ባለቤት ሊያደርጉ የሚችሉ ፖሊሲዎችን መቅረጽና መተግበር ትኩረት ሊያደርግ ይገባል ።
በከተማዋ የተጀመሩ ቤቶች በታቀደለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ የግንባታ ቁሳቁሶች ዋጋ መናር መሆኑን የተለያዩ አካላት በተለያዩ ጊዜያት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡መንግስት የግንባታ ቁሳቁሶች ዋጋ እንዳይንር አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ።በተቻለ አቅም በአነስተኛ ዋጋ የግንባታ እቃዎችን ለማቅረብ የሚያስችሉ አማራጮች ሊዘረጉ ይገባል፡፡
አዳዲስ ግንባታዎች ይካሄዳል በሚል ያረጁ ሰፈሮችን ያለ ቅድመ ዝግጅት በገፍ የማፍረስ አካሄድ በከተማዋ ለሚስተዋለው የቤት እጥረት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ከሚገኙ ምክንያቶች አንዱ ነው ።በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች ለቤቶች ልማት ተብሎ ቤት ፈርሰው አንዳች ልማት ሳይካሄድ ዓመታት ተቆጥረዋል ።መሰል አሰራር እያስከተለ ካለው ማህበራዊ ቀውስ ባሻገር የቤት ፈላጊዎችን ቁጥር የበለጠ ከፍ ሊያደርግ ይችላል ።
ያረጁ የከተማ አካባቢዎችን ማፍረስ ቢያስፈልግ እንኳ በቦታው ሌላ ግንባታ ለማካሄድ ሙሉ ዝግጅት ከተደረገ በኋላ ነው መፍረስ ያለበት ።በቦታው ግንባታ ለማካሄድ ምንም አይነት ዝግጅት ሳይደረግ ቤቶችን ማፍረስ መቆም እንዳለበት ገልጸዋል።
በመንግስት ፖሊሲ ውስጥ አድሏዊነትን ማስወገድ አስፈላጊ ነው፤ በቀጣይ ጊዜያት የቤቶች እጥረት ችግሮችን ለመቅረፍ የሚሰሩ ስራዎች ከዚህ ቀደም የነበሩ ድክመቶች እዳይደገሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ።ከዛሬ ነገ የቤት ባለቤት እሆናለሁ ብሎ የሚጠብቅ የከተማ ነዋሪ እያለ ሰበቦችን እንደምክንያት በመጠቀም ላልቆጠቡት ቤት አሳልፎ የመስጠት ሕገ ወጥነት ሊቆም ይገባል፡፡
በተጨማሪም ዝቅተኛ ኑሮ የሚኖሩ ቤተሰቦች ለራሳቸው የመኖሪያ ቤት መፍትሔዎች አስተዋፅዖ የማድረግ ዕድላቸውን ለማሻሻል ብዙ መሰራት አለበት ።መንግስት በራሱ ጥረት ብቻ ችግሩን መቅረፍ አይችልም ።ድሆች በራሳቸው ችግራቸውን የሚፈቱበትን እድሎች የማመቻቸት ስራ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
በመዲናዋ ሌላኛው የቤቶች እጥረት ምክንያት እየሆነ ያለው የቤት መስሪያ መሬት ዋጋ መናር ነው ።አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ መጠነኛ ገንዘብ ያላቸው ሰዎች የራሳቸውን ቤት ለመገንባት እጅግ አዳጋች ነው ።ይህንን ችግር ለመቅረፍ የቤት መሥሪያ የሚሆን መሬት መንግስት ለዜጎች ተደራሽ የሚያደርግበትን ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት፡፡
በቅርቡ የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን አስመልክቶ ያደረገው ጥናት እንደሚያመላክተው በቤቶች ግንባታ ዙሪያ ይስተዋሉ የነበሩ ሕገ ወጥነትና የአመራር ችግሮች የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዙሪያ ለተፈጠሩ ችግሮች አንዱ ምክንያት መሆኑን አመላክቷል ።
በዚህም ምክንያት ፕሮጀክቶቹ ከፍተኛ የሀገሪቱ ሀብት የፈሰሰባቸው ቢሆኑም በሕግና ስርዓት አለመመራታቸውን አመላክቷል ።አሁንም መሰል ችግሮች እንዳይፈጠሩ ለህገ ወጥነት በር ከፋች የሆኑ ክፍተቶችን የመሙላት እና የአመራር ክፍተቶችን የመድፈን ስራ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
በአጠቃላይ በከተማዋ የሚስተዋለውን የቤቶች ችግርን ለመቅረፍ የቤት ፍላጎት እና አቅርቦትን ለማጣጣም ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ።ይህንን ለማድረግ ደግሞ ተቋማዊ አሰራርን ማጠናከር እንዲሁም መንግስት፣ ለጋሽ አካላትና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተቀናጅተው መንቀሳቀስ ወሳኝ ነው፡፡
አዲስ ዘመን የካቲት 13/2013