ታምራት ተስፋዬ
ስመጥርና ግዙፉ ማህበራዊ አውታር መረብ ‹‹ፌስቡክ››በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ማደሪያ ትንሽ ክፍል ውስጥ እኤአ2004 ማርክ ዙከርበርግ በተባለ አሜሪካዊ ይፋ ከሆነ ጊዜ አንስቶ የግለሰቦችን ማህበራዊ ግንኙነት በማስፋፋትና በማጎልበት ረገድም ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጠቃሚው ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።ሰዎች ጎደኛ የሚያፈሩበት፤ ስሜት፤ ሃሳብና እውቀታቸው የሚለዋወጡበት፤ የሚያሰራጩበት እና የሚስተላልፉበት ይሕ መገናኛ፣ የተጠቃሚዎቹን ስሜትና ወቅታዊ ሁኔታዎች በማገናዘብም የተለያዩ አማራጮች ሲያቀርብ ቆይታል።
ኩባንያው በተለይ እኤአ በ2016 ሰዎች እርስ በእርስ ከመተዋወቅን እና የተለያዩ መረጃዎችን ከመለዋወጥ ባሻገር በፌስቡክ ገንዘብ መስራትና ማግኘት የሚችሉበት መንገድ አመቻችቷል። በፌስቡክ ገጽ አማካኝነት የሚሰራ ምርቶችን መሸጥ እና መግዛት የሚያስችል አዲስ መገበያያ መተግበሪያ አስተዋውቋል።
የገበያ ስፍራውም ሰዎች እና የንግድ ባለቤቶች ምርቶቻቸውን የሚዘረዝሩበት ክፍት የልውውጥ ቦታ ያለው ሲሆን ተጠቃሚዎች በቅርብ ርቀት ከሚገኙ የመገናኛ ዘዴው ማህበርተኞች ጋር የፈለጉትን፣የተጠቀሙትን ወይም አዳዲስ እቃዎችን በቀጥታ መግዛትና መሸጥ ይችሉበታል።
ምርቶችን መሸጥ እና መግዛት የሚያስችል አዲስ መገበበያ መተግበሪያ በአለም አቀፍ ደረጃ በርካቶች እየተጠቀሙበት ይገኛል። በተለይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የሰዎች እንቅስቃሴ መስተጋጎል ብሎም በቤት ውስጥ መታጠርና ማህበራዊ ርቀቶችን እንዲጠብቁ መገደድ በርካታ የአለማችን አገራትና ዜጎቻቸው አገልግሎቶችን ለመጠቀምና ለማስፈፀም ከሁሉ በላይ ወረርሽኙን ከሚያስፋፋው ንክኪ ለመቆጠብ የዲጂታል ፋይናንስ ቴክኖሎጂዎች ይበልጥ ምርጫቸው እንዲያደርጉ ማድረጉን ተከትሎ፣ የፌስ ቡክ ገበያ ተመራጭ ለመሆን በቅታል።
በርካታ አፍሪካውያንም በተለይ የንግድ ልውውጦችን ለመፈፀም ከቤት ሳይወጡ፣አካላዊ ንኪኪና ንፅህናን በጠበቀ መልኩ ከጥሬ ገንዘብ ይልቅ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ትስስርን በመጠቀም ላይ ናቸው። የፌስ ቡክ ገበያም በዚህ ሂደት ተጨማሪ አማራጭን ሰጥታቸዋል። ተጠቃሚዎቹም ከእለት እለት እያጨመሩ መጥተዋል።
ይሕን ያስተዋለው የፌስ ቡክ ካምፓኒም፣በተለያዩ የአፍሪካ አገራት የምርቶችን መሸጥ እና መግዛት የሚያስችል አዲስ መገበያያ መተግበሪያን ይፋ አጓል።ከዚህ ቀደም በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያና በኬንያ መሰል የገበያ ስፍራን ከፍቷል።ከቀናት በፊት ደግሞ ለአፍሪካ አራተኛ የሆነውን ናይጂሪያ መክፈቱን አስታውቋል። ውሳኔው በናይጄሪያ ምድር የኢ ኮሜርስ ግብይትን ለማሳለጥ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን Nigeria Abroad አስነብባል።
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በናይጄሪያ የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር ባለፉት ሶስት አመታት 35 በመቶ እድገት አሳይታል።እኤአ በ2017 17 ነጥብ 87 ሚሊየን ተጠቃሚዎች የነበሩ ሲሆን ይሕ አሃዝ በ2020 ወደ 27 ነጥብ 46 ሚሊየን ከፍ ብሏል። እኤአ በ2025 ወደ 43 ነጥብ 53 ሚሊየን ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።
በአፍሪካ አንግሎፎን /እንግሊዘኛ ተናጋሪ /አገራት የፌስ ቡክ የፐብሊክ ፖሊሲ ሃላፊው የሆኑት አዶራ ሊኪንዜ፣ በተለይ ባለፉት አስር ወራት በፌስ ቡክ በኩል የሚፈፀሙ ግዚና ሽያጮች መጨመራቸውን ጠቁመው፣የካምፓኒው የግብይት ጠረፔዛው ፣የናይጄሪያዊያን የግዚ እና ሽያጭ መስተግባር ይበልጥ ለሚያሳልጥና ለሚያጎለብት››ያግዛል ብለዋል። ሰዎች አዳዲስ ምርቶችን በቀላሉ ለመመልከት፣ ባሉበት ሆነው በቀላል መንገድ የፈለጉትን ለመግዛትም ሆነ ለመሸጥ እንደሚያስችላቸው አስረድተዋል።
ካምፓኒው መሰል የግብይት ጠረቤዛን ሲያመቻች፣ ተጠቃሚዎቹ ሊከተሉት የሚገባ ግልፅ፣መስፈርትና ፖሊሲ፣ህግና የደህንነት እርምጃዎችንም አስቀምጣል።ገዚም ሆነ ሻጮች በማእከሉ በሚኖራቸው ተሳትፎ 100 በመቶ ሃላፊነት አለባቸው።
በዚህ መድረክም ተሳታፊ ለመሆን ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ላይ መቆየትን ይጠይቃል።ከዚህ ባሻገር የእድሜ ገደብ የተቀመጠ ሲሆን ከ18 አመት በላይ መሆንም የግድ ነው ተብላል።
የመግዛትም ሆነ የመሸጥ ሂደቱም የራሱ ሃላፊነትን ግዴት ተቀምጦለታል። እስታንዳርድና የግብይት ፖሊሲ አለው። ማንኛውም የግዚ እና ሻጭም ህግና ደንቦችን ማክበርና መጠበቅ ግድ ይላቸዋል።
መግዛትና መሸጥ የሚፈልጉትን ምርት ፎቶ በማንሳት መለጠፍ ይችላሉ።በዚህ ሂደትም ሃቀኝነትም የግድ ነው። የምርቱን እውነተኛ ስም፣ዋጋና ሌሎችም መገለጫ ማስቀመጥ የግድ ይላቸዋል።ምርቶቹ የሚገኙበትን ስፍራ መግለፅም ይጠበቅባቸዋል።
በህግና ደንቡ መሰረትም ሁሉም ምርትና አገልግሎት ፌስቡክ ላይ አይሸጥም አይለወጥም።አንዳንድ ምርቶችም በገበያ ስፍራው ላይ አይቀመጡም። በተለይም ቁሳዊ ያልሆኑ ምርቶች ለአብንትም፣ ምግብ፣ ቀልዶች እንዲሁም ዜናዎችን ለሽያጭም ሆነ ለግዚ ማስቀመጥን ይከለክላል።
እንስሳትን እንገዛለን አሊያም እንሸጣለን ማለት እና የእንስሳትን ምስል መለጠፍ፣ፎቶና መግለጫው የማይገጣጠም ምርት ማቅረብ ፈፅሞ የማይቻል ነው።አገልግሎት በመሸጥ ረገድ ለአብነትም የቤት ፅዳት አገልግሎት እንሰጣለን አሊያም እንፈልጋለን የሚል መልክእት መጫንም አይፈቅድም።
የመጀመሪያ እርዳታ ኪቶችና የሙቀት መለኪያዎችን ጨምሮ አንዳንድ የጤና መጠበቂያ ግብአቶች ለገበያ ማቅረብም የማይሞከር ነው።ክብደት ለመቀነስ የሚያችሉ ምርቶችን በማስተዋወቅ ሰዎች ምርቱን ሲጠቀሙ ቀደም ሲል የነበራቸውን ገፅታና አሁናዊ ልዩነቶችን በማነፃፀር ማቅረብ አይቻልም።
አዲስ ዘመን የካቲት 09/2013