ቫሩን ሳይኪያ የተባለው የ 15 ዓመት ታዲጊ በውቅያኖሶች ፣ በጅረቶች እና በወንዞች ወለል ላይ ቆሻሻን በሚያጸዳ ተንሳፋፊ መሣሪያ ‹‹ፍሊፐር››በመስራት በአሁን ወቅት አለምን እያነጋገረ ይገኛል።ፈጠራውም ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ ሲሆን፣ ከርቀት መቆጥጠር የሚያስችል መሆኑ ታውቃል።
እየጨመረ የሚሄደው የፕላኔቷ የውሃ ብክለት፣ ታሳቢ ያደረጉም የታዳጊው ፈጠራ በአሁኑ ወቅት ዓለም ላይ በጣም የሚፈልገውን የፈጠራ ዓይነት እንደሆነ መስክረዋል። ታዳጊው መሣሪያውን ሲፈጥር ገና የ 12 ዓመት ልጅ ነበር ።
ታዳጊው በአሁኑ ጊዜ ዓለም ለገጠማት ብቸኛ ትልቁ ተግዳሮት መፍትሔ ለማምጣት ያግዝ ዘንድ ያፈለቀው ድነቅ ፈጠራም ሽልማቶችን እየተቀዳጀ ይገኛል።የሕንዳዊው ተማሪ በቅርቡም Initiative for Research and Innovation in STEM (IRIS) National Fair የ 2021 አሸናፊ ሆናል።
ሽልማቱም ማሳቹሴትስ በአሜሪካ የሜትሮሎጂ ማህበር ኤ.ኤም.ኤስ በከባቢ አየር እና በተዛማጅ ሳይንስ የላቀ ውጤት በማምጣት የሚሰጥ ነው። ኤ.ኤም.ኤስ ስለ ውቅያኖስ ፣ በከባቢ አየር እና በሃይድሮሎጂካል ሳይንስ መረጃዎችን የሚያስተዋውቅ እና የሚያሰራጭ ሙያዊ ድርጅት ነው ።
በሕንድ ጉጅራት ግዛት ሳማ ናቫራቻና ትምህርት ቤት የሚማረው ቫሩን አሸናፊ ለመሆን የበቃው፣ለሽልማት ከተወዳደሩ አንድ ሺ የመጨረሻ ዙር ተወዳዳሪዎች ተመርጦ መሆኑም ታውቃል።
እርሱም፣ሽልማቱን ማግኘቱ እንዳስደሰተው በመግለፅ፣‹‹ዓላማዬ ፈጣን የውሃ አካላትን በፍጥነት ሊያፀዳ የሚችል ቴክኖሎጂ ማምጣት ነው ›› ሲል ተናግራል። ምንጫችን ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ነው።
አዲስ ዘመን የካቲት 09/2013