የአሜሪካው የጠፈር እና የህዋ ምርምር ተቃም ናሳ የመጀመሪያውን ሂሊኮፕተር ማርስ ላይ ሊያሳርፍ ነው።
ሂሊኮፕተራም በዚህ ሳምንት ቀያ ፕላኔት ላይ ታርፋለች እንደምታርፍ ሲኤን ቢ ሲ አስነብባል። ቆይታዋ ሁለት አመት እንደሚወስድና ተልእኮም ቀደም ሲል ማርስ ላይ የነበረው ህይወት ምን ይመስላል የሰው ልጅን ወደ ፓላኔታ እንዲያቀናስ ምን ምቹ ሁኔታ አለ ፣የሚለውን ለመቃኘት ነው ተብላል።
በታሪክ ከመሬት ውጭ ሌላ ፕላኔት ላይ በመብረር የመጀመሪያ የሆነችው ሂሊኮፕተርም፣ ሰማንያ ሳንቲ ሜትር ቁመት፣ እንዲሁም አንድ ነጥብ ስምንት ኪሎግራም ክብደት እንዳላት ታውቃል።ባትሪዋም 273 ግራም ይመዝናል፣ የሚያስፈልጋት ሃይልም 350 ዋት ነው ተብላል።
የፕሮጀክቱ ተመራማሪዎችም፣ሂሊኮፕተራ ማርስ ላይ ለሚኖራት ቆይታና ፕላኔታ ላይ እንዴት መንቀሳቀስ እንደምትችል ለማግገጥ አስፈላጊው ምርመራና እንደተደረገላት ተናግረዋል። ምርምሩና ስኬቱም ከምድር ባሻገር ያለው አለም ምን ይመስላል የሚለው ለማረጋገጥ በቀጣይ ለሚኖሩ እርምጃዎች ወሳኝ መሆን አስታውቀዋል።
ናሳ ወደ ማርስ የምትቀናውን ሂሊኮፕተር ለመስራት ሰማንያ ሚሊየን ዶላር ፈሰስ አድርጋል።ሂሊኮፕተራ ወደ ስራ ለማስገባትም አምስት ሚሊየን ዶላር ወጪ አድርጋል።
ናሳ ማርስ ላይ ሕይወት መኖሩን ለማረጋገጥ እና የሰው ልጅ ወደዚያ መጓዝ የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እ.አ.አ ከ2012 ጀምሮ ወደ ፕላኔቷ የምርምር ጉዞ ሲካሔድ መቆየቱ ይታወሳል።
አዲስ ዘመን የካቲት 09/2013