አዲስ አበባ፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ለብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን እና ለአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የቀረቡ ዕጩዎችን ሹመት ውይይት ካደረገ በኋላ አፀደቀ፡፡
ምክር ቤቱ ትናንት ባካሄደው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባ ለብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን እና የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የቀረቡ ዕጩ አባላትን ሹመት ያጸደቀ ሲሆን፤ ለአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የቀረቡ ዕጩ አባላትን በ22 ተቃውሞና በ4 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡
የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ከሃይማኖት ተቋማት ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብፅዕ አቡነ አብርሃም፣ ከካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ፣ ከእስልምና ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ኡመር ኢድሪስ፣ ከወንጌላዊያን ዶክተር ቤተ መንግስቱ፣ ከወንጌላዊያን ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ፣ ከእስልምና ወጣት ምሁራን ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ወጣት ምሁራን አቶ ታምሩ ለጋ፤ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ ከሃሳብ መሪዎች ዶክተር ምህረት ደበበ እና መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ።
ከምሁራን ደግሞ ፕሮፌሰር አህመድ ዘከርያ፣ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነ ብርሃን፣ ፕሮፌሰር በየነ ዼጥሮስ፣ ዶክተር አበራ ዴሬሳ፣ ዶክተር ኡባህ አደም፣ ፕሮፌሰር ደስታ ሓምቶ፣ ፕሮፌሰር አሰፋ ኃይለማርያም፣ ዶ/ር ደረጀ ገረፋ፤ ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ደራሲ አያልነህ ሙላቱ፣ አርቲስት ደበበ እሸቱ እና ዶክተር ሙሴ ያእቆብ፤ ከታዋቂ የሕግ ባለሙያ ወይዘሮ ብሌን ሳሕሉ እና አቶ ታምራት ኪዳነማርያም።
ከአገር ሽማግሌዎች ሡልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ፣ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ፣ አቶ አባተ ኪሾ እና ካኦ ደምሴ፤ ከፖለቲከኞች ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ፣ ዶ/ር ግደይ ዘርዓጽዮን፤ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ከአትሌቶች አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም፤ ከታዋቂ ሰዎች ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ እና ልዑል በዕደ ማርያም መኮንን፤ ከበጎ አድራጎት ትርሐስ መዝገበ እና ዶክተር ቦጋለች ገብሬ፤ በተጨማሪም አቶ ዳሮታ ደጃሞ፣ አባ ገዳ ጎበና ሆላ፣ ዶክተር ኃይለማርያም ካሕሳይ፣ ዶክተር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ፣ ዶክተር ሰሎሞን አየለ ደርሶ እና ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ ተካትተዋል፡፡
በአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ውስጥ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ ፕሮፌሰር ጥላሁን እንግዳ፣ ዶክተር ያእቆብ አርሳኖ፣ዶክተር ደመቀ አጭሶ፣ ዶክተር ካሳሁን ብርሃኑ፣ ፕሮፌሰር ፍሥሃ ጽዮን መንግሥቱ፣ ዶክተር ጣሰው ገብሬ፣ ወይዘሮ መዓዛ ብሩ፣ ዶክተር ኦባንግ ሜቶ፣ ዶክተር መስፍን አርአያ፣ ወይዘሮ አማረች አግደው፣ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ፣ ፕሮፌሰር ወልደ አምላክ በእውቀት፣ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ወይዘሮ ራሔል መኩሪያ፣ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ፣ ዶክተር ያዕቆብ ኃይለማርያም፣ ዶክተር በቀለ ቡላዶ፣ አቶ ሌንጮ ለታ፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ አቶ ጉደታ ገለልቻ፣ አቶ አበበ እሸቱ፣ ዶክተር ጳውሎስ ሊቃ፣ አቶ ብርሃኑ ተስፋዬ፣ ዶክተር አበራ ደገፉ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ውብሸት ሙላት፣ ወይዘሮ ወርቅነሽ ዳባ እና አቶ ዘገየ አስፋው ተካትተዋል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ ውይይት ካደረገ በኋላ ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ፣ ዶክተር ዳዊት መኮንን፣ አቶ ባዩ በዛብህ፣ አቶ በለጠ ሞላ፣ አቶ ዮናስ ዘውዴ፣ አብዱልባሲጥ ምንዳዳ፣ አብዱራሂም መሐመድ እና ዶክተር በላይ ንጉሴ ላይ በኮሚሽን ውስጥ ተካትተው እንዲሠሩ አባላት አድርጎ አፅድቋል፡፡
አዲስ ዘመን ጥር 29/2011
በመርድ ክፍሉ