አስመረት ብስራት
መልካም የልጅ አስተዳደግ መርሆዎች የሚመነጨው በወላጆችና በልጆች መካከል ባለ የጠነከረ፣ በመተማመንና በተሳሰረ ግንኙነት ነው፡፡ ከልጆች ጋር ያለው የፍቅር፣ የመከባበርና የመተዛዘን ሁኔታ የቤተሰብ ትስስሩን ሲያጠናክረው የመጨካከን ግንኙነቱ ግን የቤተሰብን ትስስር ያዳክማል፡፡
የልጅ አስተዳደግ የመጨረሻ ግቡ ልጆች ሲያድጉ የተስተካከሉ ጎልማሶች እንዲሆኑ ማስቻል ነው፤ ይህም ማለት ባህሪያቸውን የሚቆጣጠሩና በራሳቸው ጤንነት እንዲሰማቸው ማስቻል መሆኑን ወላጆች መዘንጋት የለባቸውም፡፡
ለልጆች ስለሚችሉት ነገር እንጂ ስለማይችሉት ነገር አይንገሯቸው፤
• ዘወትር አሉታዊ ንግግርን የሚሰሙ ልጆች ይህንን አሉታዊውን ንግግር ይላመዱታል፡፡
• በጣም አንገብጋቢ ሁኔታ ላይ ከባድ አሉታዊ ቃላትን ከመናገር ከተቆጠቡ ልጆች የሚጠቀሙበትን ቃላት ይሰማሉም፤ ያከብራሉም፡፡
• ልጆችዎ እንዲይዙ የሚፈልጉትን ባህሪ ለማየት ለልጅዎችዎ አስተማሪ ቃላትን ይናገሩ፡፡
ልጆች የመወደድና ብቁ የመሆን ስሜት እንዲሰማቸው አድርጎ ማሳደግና መጠበቅ፤
• ልጆች መሆን የሚፈልጉት ጎልማሶች እንዲሆኑላቸው የሚመኙትን ነው፡፡ ልጆቻችን ተወዳጅና ብቁ እንዲሆኑ ጠብቀን ካሳደግናቸው እንደፈለግነው ለመሆን ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ልጆች የመወደድና ብቁ የመሆን ስሜት ካደረባቸው በራስ የመተማመን ስሜትም ይኖራቸዋል፡፡
በቤተሰብ ደረጃ ማራኪ ምግብ ማዘጋጀት ልጆቹ የባለቤትነት ስሜት እንዲያዳብሩና ለቤተሰብ አስተዋጽኦ የማድረግ ስሜት ያዳብራሉ፤
1. በቤተሰብ ደረጃ አብሮ መመገብ በቤተሰብ ደረጃ ማህበራዊ ግንኙነት እንዲያደርጉ ጊዜ ይኖራቸዋል። ይህም ጊዜ ስለቤተሰቡ ሁኔታና ስለልጆች የቀለም ትምህርት ብቃትና የትምህርት ቤት ሁኔታ ለመወያየት ጊዜ ይሰጣል፡፡
2. ዘወትር ከቤተሰብ ጋር ማዕድ የሚቀርቡ ልጆች የቋንቋ ችሎታቸውም ሆነ የትምህርት ብቃታቸው ከሌሎች አዘውትረው ማዕድ ከማይቀርቡት ልጆች የተሻለ ነው፡፡
ለልጆች ምርጫዎችን ማቅረብ ያለብዎት የልጆችን የምርጫ ውሳኔ ለመቀበል ፈቃደኛ ሲሆኑ ብቻ ነው፤
1. ለልጆች በርካታ ወይም ምቹ ያልሆኑ ምርጫዎችን ሁልጊዜ እናቀርባለን፡፡ ተስማሚ ምርጫዎችን ለልጆች ስናቀርብላቸው ከቁም ነገር አይቆጥሩትም፡፡
2. ወላጆች፣ ያስታውሱ፣ “ማለት ያለብዎትንና ምን ማለትዎ እንደሆነ” መግለጽ አስፈላጊ ነው፡፡ ከልጆች ጋር ተስማምተው ይስሩ፤ ልጆች ለመስራት የሚሞክሩትን ያጢኑና ከዚያም ለመስራት የሞከረውን
ወይም የሞከረችውን ለመስራት ሌላ አማራጭ ያስቡ።
3. አስፈላጊ ከሆነ ያግዙዋቸው ወይም ከሱ ወይም ከርሷ ጋር አብረው ይሁኑ፡፡
ልጆች በአካል ንቁ እንዲሆኑ ቤተሰቦች የልጆችን የመስኮት ዕይታ ጊዜያቸውን መቀነስን ማበረታታትና የአካል ማጎልመሻ ጤና ማጠናከር ነው፤
1. የልጆችን የመስኮት ምልከታ ጊዜን መወሰን (ቴሌቪዥን፣ ኮምፒተርና ቪዲዮ)
2. ወላጆች የልጆችን የስራ ተሳትፎአቸውን ለመጨመር ጥሩ አርአያ መሆን ይገባቸዋል፡፡
ሊገባቸው የሚችለውን ጥብቅ ወሰን ለልጆች ይስጡ።
1. ልጆች እንዲይዙት የምትፈልጉትን ባህሪ ልጆች ማወቃቸውንና መገንዘባቸውን እርግጠኛ መሆን ይገባል፡፡
2. የደንብና የጥንቃቄ እርምጃዎችን በተመለከተ ለልጆች በግልጽና ቀላል በሆነ መልኩ መግለጽ ይገባል።
ምንጭ፡- የህጻናት አስተዳደግ ምርምር
ማህበር ድረገፅ
አዲስ ዘመን ጥር 30/2013