ይበል ካሳ
አንድ በመቶ የሚሆኑት ከሁለት መቶ የማይበልጡት ጥቂት የዓለማችን ቱጃሮች ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆነውን የዓለማችንን ሃብት እንደያዙት ሁሉም አውቆትና ተቀብሎት አድሯል። እናም ድህነት ዋነኛው የሰው ልጆች ችግር፣ ዓለማችንም የድሆች ሆነው እንደቀጠሉ ነው። ይህ መሆኑ የገባት ዓለማችን ታዲያ በተናጠል ስታደርግ የነበረውን ጥረት ወደ ጋራ ትግል ቀይራ በድህነት ላይ ይፋዊ ዘመቻ ከጀመረች ሁለት ድፍን አስርታትን ጨርሳ ወደ ሦስተኛው አስር ከገባች ሁለት ወራት አስቆጥራለች።
ድህነትን ለመዋጋት ባደረገችው ቆራጥ ተጋድሎም በጎርጎሬሳውያኑ አቆጣጠር በ2000 መሪዎቿን ሰብስባ ድህነትን ለመቀነስና ብሎም ለማጥፋት ያስችላል ያለችውን “የሚሊኒየሙ የልማት ግቦች” በሚል በሰየመችው የአስራ አምስት ዓመት የድህነት ቅነሳ ስትራቴጅ 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሰዎችን ከድህነት አረንቋ ማውጣት ችላለች።
የድሆችን ቁጥር በመቀነስ ረገድ ዓለም አቀፋዊ የድህነት ትግሉ አበረታች ውጤት ያስመዘገበ ቢሆንም የተገኘው ድል ጣፋጭ እንዳይሆን ያደረጉ መሰረታዊ ችግሮች ያጋጠሙት መሆኑን በ2015 የመንግስታቱ ድርጅት የሚሊኒየሙን የልማት ግቦች አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት መግለጹ የሚታወስ ነው።
ይህም በድህነት ቅነሳ ትግሉ የተገኘው ስኬት በከፍተኛ ደረጃ አለመመጣጠን የሚታይበትና ፍትሃዊነት የጎደለው መሆኑ ነው። እናም የዓለም ሃገራት በ2015 የሚሊኒየሙን የልማት ግቦች አፈጻጸም ቁጭ ብለው ከገመገሙ በኋላ “ዘላቂ የልማት ግቦች” በሚል እስከ 2030 ድረስ ለቀጣይ አስር አምስት ዓመታት የሚቆይ ሌላ የድህነት መዋጊያ ስትራቴጅ አስቀምጠው ለሁለተኛው ዙር ፍልሚያ ወደ ሥራ ገብተዋል።
በዚህኛው ስትራቴጅ ቀዳሚ ግብ ሆኖ የተቀመጠውና ሁሉም የዓለም ሃገራት የተስማሙበት የመጀመሪያው ግብ “በ2030 አስከፊ ድህነትን ከሁሉም ዓለማችን አካባቢዎች ማስወገድ” የሚል ነው። እነሆ ስትራቴጅው ተቀርጾ ጥቅም ላይ መዋል ከጀመረ አምስት ዓመታት ከሦስት ወራት ተቆጥሮለታል።
በቀጣዮቹ ዘጠኝ ዓመታት ከዘጠኝ ወራት እንዳሰሰብነው ተሳክቶልን አስከፊ ድህነትን ከሁሉም የዓለማችን አካባቢወች ልናስወግደው እንችል እንደሆነ አብረን የምናየው ይሆናል።
እኛና ኑሯችንስ?
ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣም ድህነትን በመቀነስ ረገድ ባለፉት አስራ አምስት ዓመታት ከፍተኛ መሻሻል መታየቱን የመንግስት ብቻ ሳይሆን ተዓማኒነት ባላቸው ዓለም አቀፍ ገለልተኛ ተቋማት የተሰሩ መረጃዎችም ያመለክታሉ።
በዚህም በሃገሪቱ ያለው አጠቃላይ የድህነት መጠን እ.ኤ.አ በ2000 ከነበረበት የ45 ነጥብ 5 በመቶ በ2016 23 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ) ጥናት ያመለክታል። ይሁን እንጅ አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ከ22 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ከድህነት ወለል በታች የሚኖር ህዝብ ይገኛል።
በዚህ ረገድ አሁንም ድረስ የሃገራችን ዋነኛ ጠላት ሆነው ከቀጠሉ ችግሮቻችን መካከል ድህነት ግንባር ቀደሙን ቦታ ይዞ እየተዋጋን ነው። “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ በተለይም ደግሞ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በየጊዜው እየተበባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት ከድህነት ወለል በታች የሚኖረውን ህዝብ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዲገባና የሰቀቀን ኑሮ እንዲ ንመራ አስገድዶናል።
በሃገሪቱ ውስጥ በሁሉም አካባቢዎች በተለይም በዋና በከተሞች አካባቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ የኑሮ ውድነቱ እየተባባሰ መጥቷል። አሁን ላይ ያልጨመረ ነገር የለም፣ ሁሉም ከምግብ እስከ መድሃኒት፣ ከትንሽዋ መርፌ እስከ ትልልቅ ማሽነሪዎች ያልጨመረ የለም። ክብሪት እንኳን በአቅሟ ብር ከሃምሳ ገብታለች። መቶ ሃምሳ ግራም
የማይሞላ ዳቦ ሦስት ነው ። በተዓምር ካልሆነ በስተቀር ከምጣዱ ላይ እንዴት እንደተላቀቀ ለማወቅ የሚያዳግት፣ እፍ ቢሉት አርባ ክንድ የሚበር፣ ህጻን ልጅ የማያጠግብ አንድ እንጀራ ሰባት ብር ከገባ ሰነባብቷል። የሥጋ ዋጋው የማይቀመስ ከመሆኑ የተነሳ ለብዙሃኑ ኢትዮጵያውያን የቅንጦት ምግብ ሆኗል ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
ከእነዚህ መካከል አቶ ጋሹ መርከቡ የተባሉ አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ እንዳሉት፤ “ከአስራ ለሚልቁ ዓመታት በሚኒባስ ታክሲ ሾፌርነት ቤተሰቡን ሲያስተዳድር ኖሬያለሁ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን የኑሮ መወደድ ከአቅሜ በላይ ሆኖ እያንገዳደገደኝ ነው። በእኔ ህይወት እንኳን ታክሲ ሠርቼ ብሩን ይዤ ብገባም ምንም የሚገዛው ነገር የለም።የልጆች ትምህርት ቤት፣ ሌላውም ተዳምሮ ተስፋ ወደማስቆረጥ ደረጃ እየደረሰኩ ነው” ይላሉ ።
ይህ እንግዲህ የአቶ ጋሹ ብቻ ሳይሆን የብዙሃኑን አዲስ አበቤ ብሎም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ያለበትን የኑሮ ሁኔታ የሚያመላክት ነው። እናም በየጊዜው እየተባባሰ የመጣው የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት ኑሮን ፈታኝ አድርጎታል።
ከእነ አቶ ጋሻውም በባሰ የቀን ገቢና በአስከፊ ድህነት ውስጥም ሆነው ጎጆ ቀልሰው ኑሮን የሚመሩ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ እማወራዎችና አባወራዎች ብዙዎች ናቸው።
ሊታመን በማይችል ሁኔታ ውስጥ ሆነው ጎጆ ቀልሰው፣ አስቤዛ ሸምተው፣ የዕለት ጉሮሯቸውን ዘግተው፣ የዓመት ልብሳቸውን ገዝተው አልፈው ተርፈው ልጅ እያስተማሩ ሦስት አራት ቤተሰብ እያስተዳደሩ፣ ኑሯቸውን ከሚመሩ እናትና አባቶች መካከል ወይዘሮ አብሪሐ ገሰሰው አንዷ ናቸው። ከእንደነዚህ ዓይነት ዜጎች አንድም የሰውነት ጽናትን፣ አንድም ህይወትን የሚመሩበትን ጥበብን እንማራለንና እኛም ለዛሬው የእኒህን እናት ጎጆ ልናስቃኛችሁ ወደድን።
“ መቐለ ቤቴን በግፍ ተቀማሁ”
ወይዘሮ አብሪሃ ገሰሰው ይባላሉ። ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ የሚሄደውን መንገድ ተከትለው ሲሄዱ ራስ መኮንን ድልድይ ስር የእግረኛ መንገዱ ላይ በተለምዶ “ቴራስ” ተብሎ ወደሚታወቀው መዝናኛ ቤት መውጫ ደረጃ ስር በአሮጌ ላስቲክ ላይ አንዳንድ ነገሮች አስቀምጠው ፀሐይ ላይ ተቀምጠው ያገኟቸዋል።
የተለያየ ቀለም ያላቸው ቁርጥራጭ ደረቅ እንጨቶች በመደብ በመደብ ተቀምጠዋል(እርሳቸው እንደነገሩኝ እንጨቶቹ ቀበርቾ፣ ቀረጥ…የሚባሉ ለጭስ የሚያገለግሉ የዕፅዋት ዝርያወች ናቸው)። ማስቲካና ሲጋራም ይሸጣሉ። ከማውቃቸው ሰዎች በደረሰኝ ጥቆማ መሰረት ቦታው ድረስ ሄጀ አገኘኋቸው።
ራሴን አስተዋውቄ፣ ፈቃደኝነታቸውን ጠይቄ “አሁን እዚህ ምንድነው የሚሸጡት?” በሚል ጥያቄ ቃለ ምልልሴን ጀመርኩላቸው። “ቀበርቾ፣ ግዛዋ፤ ማስቲካና ሲጋራም እሸጣለሁ” አሉኝ።
አሁን ላይ እኮ ኑሮው ተወዷል፣ እነዚህን ሽጠው ምን ያህል ያገኛሉ፣ ደግሞስ ይበቃወታል? ቀለል አድርጌ በወግ መልክ ቀጣዩን ጥያቄ አቀረብኩላቸው። “ባይበቃስ የት እንሄዳለን፣ ብናገኝ እንበላለን፣ ብናጣ ጦማችንን እናድራለን” አሉኝ። እንዴ ብቻዎትን የሚኖሩ መስሎኝ ነው፤ ቤተሰብም አለዎት፣ ከማን ጋር የሚኖሩት? ሌላ ጥያቄ አስከተልኩ። “ልጆች አሉኝ፣ ከልጆቸ ጋር ነው የምኖረው”።
ስንት ልጆች አለዎት? አሁን አንድ ላይ ስንት ሆናችሁ ነው የምትኖሩት? “ሦስት ልጆች አሉኝ፣ አንዱ ጥሎኝ ሄዷል። አሁን አብረውኝ ያሉት ሁለቱ ናቸው፣ አንደኛዋ ወልዳለች። አጠቃላይ አራት ሆነን ነው የምንኖረው”።
እና አሁን በዚች በሚሸጧት ነገር አራት ሆናችሁ እንዴት ነው የሚኖሩት፤ ለመሆኑ ሙሉ ቀን ውለው ስንት ያገኛሉ? “ምን ያህል እንደምሸጥ አላውቀውም፤ በቃ በምሸጣት ነገር ለዕለት የምንበላት ነገር ለመግዛት የሚበቃኝ ከሆነ በዚያች ቀምሰን እናድራለን፤ ካልበቃ ወይም ካልሸጥኩ ደግሞ እንደሚሆነው እንሆናለን። ቅድም እንደነገርኩህ ምንም ከሌለ ጦማችንን እናድራለን፣ ለቆሎ የሚሆን ካገኘን ደግሞ ቆሎ ቆርጥመን እናድራለን”። ጭራሽ የማይሸጡበት ቀንም አለ? ለምሳሌ ዛሬ አሁን እስካሁን
ከእነዚህ መካከል አቶ ጋሹ መርከቡ የተባሉ አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ እንዳሉት፤ “ከአስራ ለሚልቁ ዓመታት በሚኒባስ ታክሲ ሾፌርነት ቤተሰቡን ሲያስተዳድር ኖሬያለሁ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን የኑሮ መወደድ ከአቅሜ በላይ ሆኖ እያንገዳደገደኝ ነው። በእኔ ህይወት እንኳን ታክሲ ሠርቼ ብሩን ይዤ ብገባም ምንም የሚገዛው ነገር የለም።የልጆች ትምህርት ቤት፣ ሌላውም ተዳምሮ ተስፋ ወደማስቆረጥ ደረጃ እየደረሰኩ ነው” ይላሉ ።
ይህ እንግዲህ የአቶ ጋሹ ብቻ ሳይሆን የብዙሃኑን አዲስ አበቤ ብሎም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ያለበትን የኑሮ ሁኔታ የሚያመላክት ነው። እናም በየጊዜው እየተባባሰ የመጣው የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት ኑሮን ፈታኝ አድርጎታል። ከእነ አቶ ጋሻውም በባሰ የቀን ገቢና በአስከፊ ድህነት ውስጥም ሆነው ጎጆ ቀልሰው ኑሮን የሚመሩ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ እማወራዎችና አባወራዎች ብዙዎች ናቸው።
ሊታመን በማይችል ሁኔታ ውስጥ ሆነው ጎጆ ቀልሰው፣ አስቤዛ ሸምተው፣ የዕለት ጉሮሯቸውን ዘግተው፣ የዓመት ልብሳቸውን ገዝተው አልፈው ተርፈው ልጅ እያስተማሩ ሦስት አራት ቤተሰብ እያስተዳደሩ፣ ኑሯቸውን ከሚመሩ እናትና አባቶች መካከል ወይዘሮ አብሪሐ ገሰሰው አንዷ ናቸው። ከእንደነዚህ ዓይነት ዜጎች አንድም የሰውነት ጽናትን፣ አንድም ህይወትን የሚመሩበትን ጥበብን እንማራለንና እኛም ለዛሬው የእኒህን እናት ጎጆ ልናስቃኛችሁ ወደድን።
“ መቐለ ቤቴን በግፍ ተቀማሁ”
ወይዘሮ አብሪሃ ገሰሰው ይባላሉ። ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ የሚሄደውን መንገድ ተከትለው ሲሄዱ ራስ መኮንን ድልድይ ስር የእግረኛ መንገዱ ላይ በተለምዶ “ቴራስ” ተብሎ ወደሚታወቀው መዝናኛ ቤት መውጫ ደረጃ ስር በአሮጌ ላስቲክ ላይ አንዳንድ ነገሮች አስቀምጠው ፀሐይ ላይ ተቀምጠው ያገኟቸዋል።
የተለያየ ቀለም ያላቸው ቁርጥራጭ ደረቅ እንጨቶች በመደብ በመደብ ተቀምጠዋል(እርሳቸው እንደነገሩኝ እንጨቶቹ ቀበርቾ፣ ቀረጥ…የሚባሉ ለጭስ የሚያገለግሉ የዕፅዋት ዝርያወች ናቸው)። ማስቲካና ሲጋራም ይሸጣሉ። ከማውቃቸው ሰዎች በደረሰኝ ጥቆማ መሰረት ቦታው ድረስ ሄጀ አገኘኋቸው።
ራሴን አስተዋውቄ፣ ፈቃደኝነታቸውን ጠይቄ “አሁን እዚህ ምንድነው የሚሸጡት?” በሚል ጥያቄ ቃለ ምልልሴን ጀመርኩላቸው። “ቀበርቾ፣ ግዛዋ፤ ማስቲካና ሲጋራም እሸጣለሁ” አሉኝ። አሁን ላይ እኮ ኑሮው ተወዷል፣ እነዚህን ሽጠው ምን ያህል ያገኛሉ፣ ደግሞስ ይበቃወታል? ቀለል አድርጌ በወግ መልክ ቀጣዩን ጥያቄ አቀረብኩላቸው። “ባይበቃስ የት እንሄዳለን፣ ብናገኝ እንበላለን፣ ብናጣ ጦማችንን እናድራለን” አሉኝ። እንዴ ብቻዎትን የሚኖሩ መስሎኝ ነው፤ ቤተሰብም አለዎት፣ ከማን ጋር የሚኖሩት? ሌላ ጥያቄ አስከተልኩ። “ልጆች አሉኝ፣ ከልጆቸ ጋር ነው የምኖረው”።
ስንት ልጆች አለዎት? አሁን አንድ ላይ ስንት ሆናችሁ ነው የምትኖሩት? “ሦስት ልጆች አሉኝ፣ አንዱ ጥሎኝ ሄዷል። አሁን አብረውኝ ያሉት ሁለቱ ናቸው፣ አንደኛዋ ወልዳለች። አጠቃላይ አራት ሆነን ነው የምንኖረው”።
እና አሁን በዚች በሚሸጧት ነገር አራት ሆናችሁ እንዴት ነው የሚኖሩት፤ ለመሆኑ ሙሉ ቀን ውለው ስንት ያገኛሉ? “ምን ያህል እንደምሸጥ አላውቀውም፤ በቃ በምሸጣት ነገር ለዕለት የምንበላት ነገር ለመግዛት የሚበቃኝ ከሆነ በዚያች ቀምሰን እናድራለን፤ ካልበቃ ወይም ካልሸጥኩ ደግሞ እንደሚሆነው እንሆናለን። ቅድም እንደነገርኩህ ምንም ከሌለ ጦማችንን እናድራለን፣ ለቆሎ የሚሆን ካገኘን ደግሞ ቆሎ ቆርጥመን እናድራለን”። ጭራሽ የማይሸጡበት ቀንም አለ? ለምሳሌ ዛሬ አሁን እስካሁን
ስንት ሸጠዋል?(ሰዓቱ ዘጠኝ ተኩል አካባቢ ነበረ)። “አዎ፤ አንዳንዴ ምንም ሳልሸጥ የምውልበት ቀን አለ። ዛሬ አሁን እስካሁን ምንም የሸጥኩት ነገር የለም”። ግን ወደዚህ ህይወት እንዴት ሊገቡ ቻሉ?” ሌላ ጥያቄ ጠየኳቸው። “መንግስት ቤቴን ቀማኝ፤ በላቤ ሰርቼ መሬት ገዝቼ የሰራሁትን ቤት በአምስት ሽ ብር ጉቦ መንግስት ቀምቶኝ ለሃብታም ሰጠብኝ”።
በድሃ ጉልበታቸው ለፍትው ተንገላተው፣ ላባቸውን ጠብ አድርገው በመቀሌ ከተማ መሬት ገዝተው አንዲት ክፍል ቤት ሠርተው ይኖሩ የነበሩት ወይዘሮ አብሪሃ ከላይ በገለጹት መንገድ በ1994 ዓ.ም መንግስት ቤታቸውን በግፍ ቀምቶ ለሌላ ሰው ከሰጠባቸው በኋላ ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ይናገራሉ።
የመጡት ግን “አዲስ አበባማ አዲስ አበባማ፣ ሽር ነው በጫማ” የሚለውን ዘፈን ሰምተው በዝና የሰሟትን እምዬ አዲስ አበባን ለማየትና ለመዝናናት፣ አለያም ባለጠጋዎች እንደሚያደርጉት ደልቷቸው ሞልቷቸው የነበሩበትን ኑሮ ትተው ቪላ ቤት ገንብተው ሸገር ላይ ለመኖር አልነበረም። የክልሉ መንግስት በግፍ ቀምቶ ለሃብታም የሰጠባቸውን ጎጇቸውን ተሟግተው ለማስመለስና ፍትህ ለማግኘት የፌደራሉን ፍርድ ቤት አቤት ለማለት ነበር።
“በዚያ ባለው የመቀሌው ፍርድ ቤት ሦስት ጊዜ ተመላልሸ ብሟገትም ያው ጉዳዩ መንግስት ራሱ ያለበት ስለሆነ ለእርሱ ወሰነለት። ከዚያም እኛ ወስነናል ከፈለግሽ ወደ ፌደራሉ ፍርድ ቤት አዲስ አበባ መሄድ ትችያለሽ ስላሉኝ መጣሁ። በድህነት ለፍቸ የሰራሁት ቤቴ በጉልበታም መቀማቴ ውስጤን እያመመው አላስቀምጥ ስላለኝ እንደምንም ብየ ክሱን ይዤ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ።
ግን ምን ያደርጋል እዚህም ያለው መንግስት የእነርሱ ስለሆነ የመቀሌው ፍርድ ቤት የወሰነው ይጸናል ብሎ ፈረደ። በሆነብኝ ነገር ሰው ሆኘ መፈጠሬን ጠላሁ…ሰማይ መሬቱ ዞረብኝ….ቀኑ ጨለመብኝ…የመኖር ህልሜ ተበለሻሸ ድጋሜ ወደ አገሬ መመለስ አስጠላኝና እዚሁ ቀረሁ።
ይኸው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አስራ ዘጠኝ ዓመት ሆነኝ እስካሁን ድረስ እንደነገርኩህ ሆኘ እኖራለሁ” በማለት ወደ አዲስ አበባ የመጡበትንና ጎጆ አልባ ህይወት የጀመሩበትን ክፉ ገጠመኝና እየኖሩት ያሉትን አሳዛኙን ህይወታቸውን እንባ እየተናነቃቸው ተረኩልኝ።
የአዲስ አበባው “ጎጆ ”
የመተዳደሪያውን ነገር ቅድም አጫወቱኝ፣ ከሁለት ልጆችውና ከአንድ የልጅ ልጅዎ ጋር አራት ሆናችሁ እንደምትኖሩም ነግረውኛል። እና ቤትስ እንዴት ሆነው የሚኖሩት? የመጨረሻውን ጥያቄ በሃዘን ስሜት ሆኘ ጠየኳቸው። “ያኔ እንደነገርኩህ ሰማይ መሬቱ ተደፍቶብኝ፣ የምይዘው የምጨብጠው አጥቼ ከስድስት ኪሎ ከፍርድ ቤቱ ወጥቼ እያለቀስኩ ወደ ፒያሳ እየሄድኩ እያለሁ አንዲት መነኩሲት አገኘሁ።
ከዚያም የሆንኩትን ጠይቀውኝ ወደ ቤት ይዘውኝ ከሄዱ በኋላ ከእርቸው ጋር ለተወሰነ ቀናት ካቆዩኝ በኋላ ራስ መኮንን ድልድይ ተብሎ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ጨርቅ እየሰፉ የሚኖሩ ሽማግሌ ሰውየ አስተዋወቁኝና፤ አብረን እንድንኖር አስማሙን፤ ቆርቆሮ በቆርቆሮ የሆነች ትንሽየ መጠለያ ውስጥ ነው የምንኖረው። በሁለተኛው ዓመት በ1996 ዓ.ም ከእርሳቸው አንዲት ሴት ልጅ ወለድኩኝ፤ ሆኖም ሰውየው(ባለቤቴ) ያማቸው ስለነበረ በ2000 ዓ.ም ሞቱ።
“ ውሃ የሚያጠጣኝ ጎረቤት ነው፣ መብራትም እንዲሁ ትንሸዋን አምፖል ቀጥለውልኝ ነው የምጠቀመው። እርሷንም እራት ልንበላ ስንል አንድ አፍታ አብርተን እናጠፋታለን እንጅ ሁሌ አናበራትም ።” አሉኝ።
እንዴያው መንግስት ወይም ደግሞ ሌሎችች ረጂዎች ሊያግዝዎት ቢፈልግ ግን ምን እንዲያግዝዎት ነው የሚፈልጉት”፤ “ከመጠለያ ቢያወጣን መንግስት የተሻለ ቀበሌ ቤት እንኳን ቢሰጠኝ ፤ ሌላው ደግሞ አንደኛዋ ልጄ ደግሞ ትማራለች አስረኛ ከፍል ናት እርሷንም ትምህርቷን ጨርሳ ራሷን እንድትችልልኝ ፣ እግዚአብሔር ካቆየኝ እኔንም እንድታግዘኝ መብራት እንኳን እንደ ልቧ አግኝታ የምታጠናበት መብራት ያላት ትንሽ ቤት ብናገኝ ነው የምመኘው”። በማለት ነው ሀሳባቸውን ያካፈሉን።
ከላይ በመግቢያችን ላይ እንዳየነው ሃገራችንና ዓለማችን ድህነትን ለመዋጋት እያደረጉት ያለው ከፍተኛ ጥረት ጣፋጭ እንዳይሆን እያደረገባቸው ያለውን ያልተመጣጠነ ኑሮና ኢፍተሐዊነት መቀነስና ምናልባትም እንደተመኘነው በቀሩት ዘጠኝ ዓመታትና ዘጠኝ ወራት ውስጥ አስከፊ ድህነትን ከሁሉም አካባቢዎች አስወግደን የ2030ውን ዘላቂ የልማት ግቦች ማሳካት እንችላለን።
አዲስ ዘመን ጥር 29/2013