ተመራማሪዎች በስነ-ፈለክ ምርምር ውስጥ የመጀመሪያ የሆነ ጁፒተርን የሚመስል ደመና አልባ ፕላኔት ማግኘታቸውን አስታወቁ። ግኝቱ በዚህ ወር አስትሮ ፊዚካል ጆርናል Astrophysical Journal Letters ላይ የታተመ መሆኑም The Harvard Gazette አስነብቧል። ስለ ፕላኔቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍንጭ የተገኘው በ2012 ቢሆንም ከባቢ አየሩ ግን እስካሁን ድረስ ሳይታወቅ ቆይቷል።
ፕላኔቱ ‹‹ሞቃቱ ጁፒተር›› የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው በሳይንሳዊ መጠሪያው WASP-62b የሚባል ሲሆን በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ ከሚገኘው ጁፒተር ግማሽ ያክል መጠን ሲኖረው በ575 የብርሃን ዓመት ርቀት ላይ እንደሚገኝም ተመላካታል። ፕላኔቱ ፀሐይን ለመዞር 12 ዓመት ከሚወስድበት ከጁፒተር በተቃራኒው የራሱን ኮከብ ዞሮ ለመጨረስ አራት ቀን ተኩል ብቻ ይፈጅበታል ተብሏል። ለኮከቡ ባለው ቅርበት የተነሳ ከፍተኛ ሙቀት አለው።
ለምርምሩ ሃብል የተባለው የህዋ ቴሌስኮፕ ጥቅም ላይ ውላል። በውስጡ የሚገኙ ንጥረ ነገሮችን ለመለየት ስፔስትሮስኮፒ የተባለ ስልትን እንደተጠቀመች ምርምሩን ያደረገችው ሙንዛ አላም ተናግራለች። ምንም እንኳን ፖታሺየም መኖርን የሚያመለክት ፍንጭ ባይኖርም ሶዲየም የተባለው ንጥረ ነገር ግን በግልጽ ይታያል ስትል ታስረ
‹‹መጀመሪያም ስለ ፕላኔቷ ባገኘሁት መረጃ ብዙም አልተደነቅኩም፣ይሁንና መረጃውን በጥልቀት በመቃኘትና በመመርመር ባገኘሁት ውጤት እጅግ በጣም ደስተኛ ሆኛለሁም› ›ብለላች። ደመና አልባ ፕላኔቶችን የማግኘት እድል እጅግ ዝቅተኛ እንደሆነ ጠቁማለች።
እስካሁን ባለው ምርምር ግልጽ የሆነ ከባቢ አየር ያለው ኤግዞ ፕላኔት ሞቃቱ ሳተርን የተሰኘውና በ2018 የተገኘው WASP-96b ፕላኔት መሆኑን ታውቋል። የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች እንዲህ አይነት ግልጽ የሆነ ከባቢ አየር ያላቸውን ደመና አልባ ፕላኔቶች ማጥናት በፕላኔቶች አፈጣጠር ዙሪያ ለሚደረገው ምርምር አጋዥ እንደሚሆን አመላክተዋል። ዳለች።
አዲስ ዘመን ጥር 18/2013