በኃይሉ አበራ
እስራኤል ቀድሞውኑ ከጆ ባይደን የውጭ ፖሊሲ ፊርማዎች አንዱ የሆነውን ከኢራን ጋር የኒውክሌር ስምምነት ዳግም የማደስ ዕቅድን ለማስቀረት ፍላጎት እንዳላት ብሉምበርግ ዘግቧል።
በዘገባው መሰረት የእስራል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢንያሚን ኔታንያሁ በኦባማ አስተዳደር ወቅት እ.ኤ.አ የ2015 ከኢራን ጋር የኑክሌር ስምምነት የተደረገበትን ውል የማገድ ከፍተኛ ዘመቻ አልተሳካም።
ባለስልጣናት አሁን ላይ ከባይደን ጋር ከመድረክ በስተጀርባ የሚደረጉ እንዲህ ዓይነቱ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ውጤታማ ስትራቴጂ ይሆናል በሚል እየመዘኑ ነው ሲሉ አንድ ከፍተኛ የእስራኤል ባለሥልጣን ገልፀዋል። ምንም ዓይነት ውሳኔ እንዳልተደረገም አፅንዖት ሰጥተዋል።
በግል ውይይቶች ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት ኃላፊው እስራኤል በዋሽንግተን ጉብኝት ላይ በርካታ መልዕክተኞችን በመላክ ትጀምራለች ሲሉ ገልጸዋል።
አሜሪካ አዲስ ስምምነት ሳይደረግ በእስላማዊ ሪፐብሊክ ላይ ማዕቀቦችን እንድታስቀር እንደማይፈለግ እና በኑክሊየር ፕሮጀክት፣ በባላስቲክ ሚሳይል መርሃግብር እና በቀጠናዊ ተኪ ኃይሎች ዙሪያ ጠንካራ አቋም መወሰድ እንዳለበት በይፋ ተገልጿል።
ይህ ስትራቴጂ የባይደንን ቡድን እንደገና ወደስምምነት የመግባት እና ከዚያ ውሎቹን ለማስፋት በሚደረገው መነጋገር ላይ ካለው ፍላጎት ጋር ይቃረናል። ዶናልድ ትራምፕ እ.ኤ.አ በ2018 አሜሪካን ከስምምነቱ ካስወጡ በኋላ ኢራን ገደብ የጣሰችበት ስምምነት ላይ የምትመለስበትን ቅድመ ሁኔታ ይወስናል።
በእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር የፖለቲካና ወታደራዊ ቢሮ ሃላፊ ዞሃር ፓልቲ ከአንድ ወር በፊት በፓናል ውይይት ላይ እንደተናገሩት “ድርድሩን ከመጀመራችን በፊት ማዕቀቡን ላለማቆም የተወሰኑ የአምስት ደቂቃ ትምህርቶችን መማር ያለብን ይመስለኛል።” ብለዋል።
ኢራን የአሜሪካን ወደ ስምምነቱ መመለስ እንደምትቀበል ትናገራለች፤ ነገር ግን ድርድር አታደርግም።
እንዲሁም በአሜሪካ ማዕቀብ ምክንያት ለጠፋው የ70 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ዘይት ገቢ ካሳ ትጠይቃለች። እስራኤል ደግሞ በኢራን ላይ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን የመቀየር ስውር እንቅስቃሴ አቅም ያለውና የሚያስጠነቅቅ የአደጋ ካርድ አላት።
ቴህራን እ.ኤ.አ በጥቅምት ወር ለተፈጸመው አንድ ከፍተኛ የኢራን የኑክሌር ሳይንቲስት ግድያ እስራኤልን ትወቅሳለች፤ እንዲሁም የኔታንያሁ መንግስት በዚህ ወር በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል የባይዴን ስምምነቱን የማደስ ጥረት ለማደናቀፍ በመሞከር አሜሪካን ለጦርነት የማነሳሳት ሙከራ አድርጋለች ብለው ይከሳሉ።
ኔታንያሁ ስምምነቱን በማደስ በኩል ያለውን የአሜሪካ ተሳትፎ ለማስቆም ስላላቸው ፍላጎት በግልጽ አሳይተዋል። “ኢራን እ.ኤ.አ ወደ 2015ቱ የኑክሌር ስምምነት መመለስ የለባትም፤ ከመሠረቱም የተሳሳተ ስምምነት ነው” ብለዋል።
እስራኤል ባልተለመደ ህዝባዊ ክፍፍል ውስጥ በመሆንም በተወካዩ በርኡል በኩል ስምምነቱን የማስቆም ሃሳባቸውን በጀርመን ለሚገኙ ዲፕሎማቶቿ በማስረዳት የበርሊንን ግፊት ለማግኘት እየሰራች ነው።
በየካቲት ወር ምርጫ የሚጠብቃቸው ቤንጃሚን ኔታኒያሁ በውጭ ፖሊሲና ደህንነት ዘመቻዎች ላይ የሚገኙ ሲሆን የኢራንን ስምምነት በመቃወም በእስራኤል የተቃውሞ ድምጽ በማሳየት ላይ ይገኛሉ።
እ.ኤ.አ. በ2015 ናታንያሁ የፓርላማ አባላት የኦባማን የኢራን ፖሊሲዎች እንዲቃወሙ ለማሳመን የሞከረበትን ለአሜሪካ ኮንግረስ አከራካሪ ንግግርን አካትቷል።
ንግግሩ የተደረገው እንደ ስድብ ተደርጎ የሚታየውን በወቅቱ የነበረው ፕሬዝዳንት ለኋይት ሀውስ ሳያሳውቅ የዲፕሎማሲ ፕሮቶኮልን በመጣስ ነው።
በወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ባይደን ከኔታንያሁ ጋር ጥሩ ግንኙነት በመፈለግ የህዝብ አለመግባባቶችን ለማስወገድ እንደሚሞክሩ በቅርቡ ከባይደን ቡድን ጋር የተገናኙ የቀድሞ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን ተናግረዋል። ነገር ግን አጠቃላይ ፖሊሲው ለክርክር አይሆንም፤ ብሏል ግለሰቡ።
በአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ስር በኢራን ፖሊሲ ላይ የሚደረጉ ፈጣን ለውጦች የሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦትን ማቃለል እና ከአውሮፓ ጋር ያለው የንግድ አሠራር በተሻለ እንዲሠራ ማድረግን ሊያካትቱ ይችላሉ ሲሉ የቀድሞው ባለሥልጣን ለተመረጡት ፕሬዝዳንት የመናገር ስልጣን ስላልተሰጠ ስማቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀዋል። .
በካርኒጊ ኢንዶውመንት የቀድሞ ዓለም አቀፍ ሰላም ከፍተኛ የሥራ ባልደረባ፣ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞው የመካከለኛው ምስራቅ ባለስልጣን የሆኑት አሮን ዴቪድ ሚለር “በባይደን እና በኔታንያሁ መካከል የጫጉላ ሽርሽር አይኖርም፤ ነገር ግን በኦባማ ዘመን የነበረውን ዓይነት ግንኙነት የሚያንፀባርቅ የሳሙና ኦፔራ አያስፈልግም” ብለዋል።
አዲስ ዘመን ጥር 6/2013