ከህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሌሎች አባል አገራት የቀረበ ከንግድ ጋር የተገናኘ የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብቶች /ትሪፕስ/ክልከላ ጽንሰ ሀሳብ
በብራጃንድራ ናቭኒት የህንድ የአለም የንግድ ድርጅት አምባሳደር እና ቋሚ ተወካይ
በህንድ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በሌሎች 8 ሀገራት፤ አንዳንድ የባለቤትነት ፍቃዶችን እና ከአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብቶች ጋር የተያያዙ እና ትሪፕስ ተብለው የሚጠሩ ከንግድ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች ላይ በተደረገው የድርጅት ስምምነት ስር ባሉት ሌሎች አእምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብቶች ላይ ለተወሰነ ጊዜ በአባል ሀገራት ላይ ተግባራዊ እንዳይደረጉ ለአለም የንግድ ድርጅት ጥሪ የቀረበበት ምክረ ሀሳብ።
ይህም የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብቶች የኮቪድ-19 ክትባቶች እንዲመረቱ እና ህክምናው በፍጥነት እንዲከናወን እንዳይገደብ ያረጋግጣል፣ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አባላት ስለ ምክረ ሀሳቡ ያላቸውን ስጋት ቢገልፁም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአለም ንግድ ድርጅት አባላት ግን ምክረ ሀሳቡን ደግፈዋል። እንዲሁም የተለያዩ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በርካታ ኤጀንሲዎች እና አለም አቀፍ የሲቪክ ማህበራት ድጋፍ ተቀብለዋል።
ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ጊዜዎች ያልተ ለመዱ እርምጃዎችን ይጠይቃሉ። ይህንን ለተወሰነ ጊዜ በተደረገው ሙሉ በሙሉ ክልከላ ውጤት ማምጣቱን ተመልክተናል። እንደ ፖሊሲ ጣልቃ ገብነት የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት ችሏል። የዓለም አቀፍ የገንዘብ ፈንድ በኦክቶበር 2020 እትሙ በአለም የኢኮኖሚ ምልከታ ይህንን ተናግረዋል። “ይሁን እንጂ ከታሰበው በላይ እየከፋ ያለው የስርጭቱ እድገት ስጋት ማቆም አልተቻለም።
ቫይረሱ በድጋሚ የሚያገረሽ ከሆነ የህክምናዎቹ እና የክትባቶቹ ሂደት ከተገመተው በላይ ከቀዘቀዘ ወይም የሚያገኙአቸው ሀገራት እኩል ሳይሆኑ ከቀሩ፣ የኢኮኖሚ ስራው ከተጠበቀው በታች ሊሆን ይችላል። እንዲሁም አዲስ የአካል መራራቅ እና ጥብቅ ክልከላ ሊያስከትል ይችላል”። ሁኔታው ከተገመተው በላይ የከፋ መስሎ ይታያል። በ2019 ከተገመተው ትንተና የመሰረት መስመር 7 በመቶ የኢኮኖሚ ውጤቱን አጥተናል።
ይህም ሲተረጐም ከአለም ጂዲፒ ከ10 ትሪሊየን ዩኤስ ዶላር በላይ ኪሣራ ደርሷል። በአለም አቀፍ ጂዲፒ ውስጥ ። ማሻሻል እንኳን በአለም አቀፍ ውጤት ላይ ከ800 ቢሊዮን ዩኤስ ዶላር በላይ ውጤት የሚጨምር ሲሆን በክልከላው ሁኔታ በጣም ዝቅተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ኪሣራ እንደሚኖር ማረጋገጥ ይቻላል።
ክትባቶቹን እና ህክምናዎቹን በጊዜ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት የሚቻል መሆኑን የማረጋገጫ ቀላል ምልክት በኢኮኖሚ ውስጥ ለሚኖር የፍላጐት ማነቃቂያ ከፍተኛ በራስ መተማመን ማሣደጊያ ሆኖ ይሰራል።
የተሳካ ክትባቶች መፈጠር በከፍተኛ ደረጃ የተወሰነ ተስፋ ያጭራል። ነገር ግን ይህ ምን ያህል የአለም ህዝብ ተደራሽ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል። መሰረታዊ ጥያቄ የሚሆነው የኮቪድ 19 ክትባቶች በቂ ይሆናሉ ወይ የሚለው ነው። ነገሮች እንደሚታዩት ከሆነ የተሻለ ተስፋ አድራጊዎች እንኳን ሳይቀር በዚህ ዘመን የኮቪድ 19 ክትባቶችን እና የቴራፒዩትክስ ህክምናዎችን ለአብዛኛው ህዝብ ማለትም በሀብታም እና በደሀ ሀገራት ሁሉ ላሉት እስከ 2021 መጨረሻ ድረስ ማዳረስ እንደሚቻል አላረጋገጡም። ሁሉም የዓለም የንግድ ድርጅት አባላት እጅግ በጣም ብዙ የሆነውን የአለም ፍላጐቶቹን
ለመድረስ የክትባቶቹን እና የቴራፒዩቲክስ የማምረት አቅምን በከፍተኛ ደረጃ በአስቸኳይ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ተስማምተውበታል። ከንግዱ ጋር የተያያዙ የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብቶች ክልከላ ምክረ ሀሳብ የአእምሯዊ ንብረት ክፍተቶች የማምረት አቅምን ለመጨመር ተግዳሮት እንዳይሆኑ በማረጋገጥ ይህንን ፍላጐት ማሟላት የሚፈልግ ምክረሀሳብ ነው።
በንግድ ተያያዥ የአእምሯዊ ንብረት ባለቤ ትነቶች ስምምነት ስር ያሉ ተለዋዋጭነቶች ለምን በቂ አልሆኑም በንግድ ተያያዥ የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነቶች ስምምነት ስር ያሉ ተለዋዋጭነቶች በቂ ያልሆኑበት ምክንያት እነዚህ ነገሮች ወረርሽኝን በማሰብ የተሰሩ ነገሮች አይደሉም። የአስገዳጅ ፍቃዶች ሀገር በሀገር፣ ጉዳይ በጉዳይ፣ ምርት በምርት ላይ በመመስረት የተሰጡ ሲሆን ይህም የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነቱ የተለየ አስገዳጅ ፈቃዶችን ለመስጠት ስልጣን በሚኖራቸው በእያንዳንዱ ቦታ በተለይም በጣም አስቸጋሪ እና አድካሚ በሆኑ ሀገራት መካከል ትብብርን በተጨባጭ ለማድረግ የተሰጡ ናቸው።
ከንግድ ጋር የተገናኙ የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነት ተለዋዋጭ አሰራሮችን እንዲጠቀሙ ስናበረታታ በዛው ልክ ጊዜን የሚያባክኑ እና ለመተግበር የሚያዳግት ጉዳይ ናቸው። ስለዚህ መጠቀማቸው ብቻ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ክትባቶች እና ህክምናዎች በወቅቱ ስለመቅረባቸው ሊያረጋግጥ አይችልም።
በተመሣሣይ ሁኔታ በዓለም የጤና ድርጅት የኮቪድ 19 የቴክኖሎጂ አክሰስ ፑል ወይም ሲ-ቲኤፒ ኢንሼቲቭ የአእምሯዊ ንብረትን፣ ቴክኖሎጂን እና ንብረትን በፍቃደኝነት አስተ ዋጽኦ እንዲያደርጉ እና የዓለም መጋራትን እንዲደግፉ እንዲሁም የኮቪድ 19 የህክምና ምርቶችን ማምረቻ ከፍ እንዲያደርጉ የሚያበ ረታታው ስራ በጣም የሚያበረታታ ሂደት ላይ ሆኖ አላገኘነውም ። በፍቃደኝነት የሚሰጡ ፍቃዶች ባሉበት ቦታ እንኳን እጥረት ያለባቸው ናቸው።
ህጐቻቸው እና ሁኔታዎቻቸው ግልጽ አይደሉም። ይዘታቸውም ለተወሰነ መጠን ብቻ የተገደበ ወይም ለተወሰኑት ሀገራት ብቻ የተገደቡ ሲሆን ከአለም አቀፉ የትብብር ሁኔታ ይልቅ ሀገራዊነትን የሚያበረታቱ ናቸው።
ከአሉት የዓለም አቀፍ ትብብር ማበረታ ቻዎች በላይ መሄድ የሚያስፈልገው ለም ንድን ነው። የዓለም አቀፉ የትብብር ማበረታቻ እንደ ኮቫክስ መካኒዚም እና የአክት አክስሌረተር የመሳሰሉት በዓለም አቀፍ ያለውን የ7.8 ቢሊዮን ሰዎች ከፍተኛ ፍላጐት ለመድረስ በቂ አይደሉም።
አክት-ኤ ኢንሼቲቭ በሚቀጥሉት ዓመታት መጨረሻ ላይ ሁለት ቢሊዮን የክትባቶች ደርዘኖችን ለመግዛት እና ፍትሐዊ በሆነ ሁኔታ በዓለም ዙሪያ ለማሰራጨት አላማ ይዘዋል። በሁለት ዙር አሰራር ለመፈፀም ያሰበ ሲሆን ነገር ግን ይህ 1 ቢሊዮን ሰዎችን ብቻ መሸፈን የሚችል ነው። ይህም ማለት አሁን ባለው ሁኔታ ማድረግ ባይችልም አክት-ኤ ሙሉ በሙሉ ገንዘብ ቢያወጣ እና ቢሳካለት እንኳን ለአብዛኛው የዓለም ህዝብ በቂ ክትባቶች
አይኖሩም ማለት ነው።
ያለፈው ልምድ
በዚህ ወረርሽኝ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ወቅት የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች፣ የግል የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎች፣ ሳኒታይዘሮች እና የእጅ ጓንት እንዲሁም ሌሎች የኮቪድ 19 አስፈላጊ መሳሪያዎችን ማግኘት በቻሉት አካላት ያለ አስቸኳይ ፍላጐት እንኳን መደርደሪያዎች ባዶ ተደርጐ ነበር።
ተመሳሳይ ሁኔታ በክትባቶቹ ላይ መፈፀም የለበትም። በስተመጨረሻ አለም የኮቪድ -19 አስፈላጊ መሳሪያዎችን ማምረት ማሳደግ ችለው ነበር። ምክንያቱም ይህንን አሰራር ወደኋላ የሚጐትት የአእምሯዊ ንብረት ክፍተት ስለሌለ ነው። በአሁኑ ጊዜ ተመሳሳይ የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብቶች ድጋፍ እና ክትባቶቹ እና ህክምናዎቹን የማምረት አቅም እንዴት ማሣደግ እንደሚቻል ማወቅ ያስፈልገናል። እንደ አጋጣሚ ይህ የክልከላውን አያቆምም፣ ለማቆም አስፈላጊ አይሆንም።
ይህ ወረርሽኝ እና በጣም የተለየ ሁኔታ ነው፣ በህይወት ዘመን አንድ ጊዜ የሚያጋጥም እና የበርካታ ባለ ድርሻ አካላትን ትብብር ያንቀሳቀሰ ነው። የሀገራትን ትብብሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የገንዘብ መዋጮ እንዲወጣ ያስቻለው በሳይንቲስቶች፣ በተመራማሪዎች፣ በመንግስት የጤና ባለሙያዎች እና በዩኒቨር ስቲዎች የተያዘው እውቀት እና ክህሎቶች ሲሆን ይህም ሪከርድ በሆነ ጊዜ ክትባቶቹን መፍጠር እንዲቻል ሁኔታዎችን ያመቻቸ ሲሆን እንዲሁም የአእምሯዊ ንብረት ጉዳይ ብቻ አይደ ለም!
ለወደፊት የሚሰራበት መንገድ
ከንግድ ጋር የተገናኙ የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብቶች ክልከላ ምክረ ሀሳብ በዚህ ዘመን አለም ያጋጠማት ድንገተኛ እና ልዩ የህዝብ ጤና አደጋ ምላሽ ለመስጠት ኢላማ ያደረገ እና የታለመ ነው። የዚህ አይነት ክልከላ በአለም የንግድ ድርጅት ማቋቋሚያ የማራካሽ ስምምነት ድንጋጌዎች አንቀጽ IX ውስጥ በደንብ የሚታወቅ ነው። የሰው ልጅ ህይወት በጊዜ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ክትባቶችን ለማግኘት በመፈለግ ሳሉ እንዳያልፉ ለማረጋገጥ ሊረዳ የሚችል ነው።
የክልከላ አሰራሩ የአለም የንግድ ድርጅትን አስማማኝነት በድጋሚ የሚመሰርት እና ዘርፈ ብዙ የንግድ ሥርዓቱ አስፈላጊ ሆኖ እንዲቀጥል እንዲሁም በአደጋዎች ጊዜ መድረስ የሚችል መሆኑን ያሳያል። የአሁኑ ጊዜ የአለም የንግድ ድርጅት አባላት ህይወትን ለማዳን እና በፍጥነት የኢኮኖሚ መነቃቃትን እንዲያገኙ ለመርዳት እርምጃ መውሰድ እና ክልከላውን ማውጣት አለባቸው።
ክትባቶቹ እንዲኖሩ ማድረግ የሳይንስ ምርመራ ሲሆን እንዲቀርቡ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገኙ ማድረግ ደግሞ የሰብዓዊነት ፈተና ነው። ታሪክ የ“ኤኤኤ ሬቲንግ” አሰራርን ሊያስታውሰን ይገባል ይህም የኮቪድ-19 ክትባት እና ህክምናዎች መገኘት፣ መቅረብ እንዲሁም የዋጋ ተመጣጣኝነት ሲሆን እንዲሁም ለነጠላ “ኤ ሬትንግ” ለመገኘት ብቻ አይደለም። የሚቀጥሉት ትውልዶቻችን ምንም ያነሰ ነገር አይገባቸውም።
አዲስ ዘመን ታህሳስ 28/2013