የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከታኅሣሥ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየዉን መደበኛ ስብሰባ አጠናቋል። ኮሚቴዉ በሰላም። በልማት። በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና መጪዉን አገራዊ ምርጫ በተመለከቱ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። በዋናነት ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በአገራችን የታየዉ ለዉጥ በርካታ ፖለቲካዊ። ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፈተናዎችን ተጋፍጦ የአገራችንን ብልጽግና እዉን ለማደረግ ሰፊ ዕድል የፈጠረና አገራችንን ከብተና አደጋ ያዳነ መሆኑ በዉይይቱ ከስምምነት ተደርሷል።
በተለይም ብልጽግና ዉሁድ ህብረ ብሄራዊ አገራዊ ፓርቲ ሆኖ መደራጀቱ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ከፍተኛ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ ከአገሪቱ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ተገልለዉ የዳር ተመልካች የነበሩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማቀፍና ለማሳተፍ የቻለ የመጪዉ ትዉልድ ፓርቲ መሆኑ ተረጋግጧል። በአገራዊ ለዉጡ የተገኙ ድሎችን ጠብቆ በማስቀጠል ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን፤ ለዚህም የፓርቲዉን መርሆዎች።
እሴቶችና አሠራሮችን በጥብቅ ዲሲፕሊን ተግባራዊ ማድረግና ጠንካራ ተቋማዊ ባህል መገንባት አስፈላጊ መሆኑ ከስምምነት ተደርሷል። ኮሚቴዉ በሁለቱ ቀናት መደበኛ ስብሰባዉ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን አቅጣጫዎች አስቀምጧል።
1. አገራችንን ለመበታተን በከፍተኛ ሁኔታ ሲዘጋጅ ቆይቶ ፍጹም አረመኒያዊ በሆነ መልኩ በአገር መከላከያ ሠራዊታችን ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ይታወቃል። ይህ ስግብግብ ጁንታ በአጭር ጊዜ እንዲፈርስና አገራችን ከዚህ ከሃዲ ኃይል ነፃ እንድትወጣ ጀግናዉ መከላከያ ሠራዊታችን።
የአማራና አፋር ክልሎች ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እንዲሁም በተለያየ ደረጃ ድጋፍ ላደረጉ መላዉ የሀገራችን ህዝቦች ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን። ጀግንነት ልምዳችን ስለሆነ በዚህ ድል ሳንኩራራ ይህንን አገራዊ የአንድነት ስሜትና ቁርጠኝነት በሌሎች የልማት ዘርፎችም በመድገም የአገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ አስቀምጧል።
2. የወንጀለኛዉን ከሃዲ ጁንታ አባላት ከተደበቁበት አድኖ ለፍርድ ለማቅረብ ከሚደረገዉ ርብርብ
ጎን ለጎን በህግ ማስከበር ዕርምጃው ሂደት ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀዬያቸዉ ተመልሰዉ እንዲቋቋሙና እብሪተኛው ጁንታ ያፈራረሳቸዉ የህዝብ መሰረተ ልማቶች በፍጥነት ተጠግነዉ ለአገልግሎት እንዲውሉ ለማድረግ የተጀመረዉ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ ተቀምጧል።
በትግራይ ክልል የህዝብ አገልግሎቶችን ለማስጀመር። የዕለት ደራሽ ሰብዓዊ አገልግሎቶችን በፍጥነት ለማድረስና ህብረተሰቡ ወደ መደበኛ የዕለት ተዕለት ህይወቱ እንዲመለስ በሚደረገዉ ርብርብ ዉስጥ የፓርቲዉ አመራሮች። አባላት። ደጋፊዎችና መላዉ የአገራችን ህዝቦች የቻሉትን አስተዋጽኦ ሁሉ እንዲያደርጉ ኮሚቴዉ ጥሪ ያቀርባል።
3. በኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥትና ብሄረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የተለያዩ የፖለቲካ ኃይል አሰላለፎች የሚታዩበት ነዉ። በአገራችን የሚታየዉን ዉስብስብ ብዝሃነት የሚያስተናግድ አገራዊ አንድነት ከመገንባት አንጻር በወንድማማችነት እሴት ላይ የተመሰረተ ህብረብሄራዊ አንድነትን የሚያረጋግጥ የፌዴራል ስርዓት ግንባታ እዉን እንዲሆን የፓርቲያችን አመራሮችና አባላት በቁርጠኝነት እንዲታገሉ አቅጣጫ ተቀምጧል።
4. በተለያዩ አካባቢዎች ህዝቦች የሚያነሷቸዉ የማንነት ጥያቄዎች ተገቢነት ያላቸዉ ፍትሐዊ የህዝብ ጥያቄዎች መሆናቸዉን ኮሚቴዉ ያምናል። እነዚህ ጥያቄዎች ነባራዊ ሁኔታዉን መሰረት በማድረግ የህዝቦችን ወንድማማችነትና አብሮነት እንዲሁም የህዝቡን ነፃ ፍላጎት ከግምት ባስገባ መልኩ ህጋዊ አሠራርን ተከትሎ ምላሸ እንዲሰጣቸዉ ኮሚቴዉ አቅጣጫ አስቀምጧል።
5. በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በአፋጣኝ እንዲቆሙ ተገቢዉ ዕርምጃ ሁሉ እንዲወሰድ ኮሚቴዉ ከስምምነት ደርሷል። እነዚህን እኩይ ተግባራት የሚፈጽሙ የጥፋት ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ለማዋልና ዕርምጃ ለመዉሰድ በሚደረገዉ ርብርብ በየደረጃዉ የሚገኙ የብልጽግና አመራሮች በከፍተኛ ጽናትና ቁርጠኝነት እንዲሠሩ አቅጣጫ ተቀምጧል።
6. የአገራችንን ፖለቲካዊ።ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች በየትኛዉም ቦታ የሚገኙ የብልጽግና አመራሮችና አባላት ከሚለያዩ ጥቃቅን ጉዳዮች ወጥተዉ ከፍ ያለ አገራዊ እይታ በመያዝ ኢትዮጵያንና የሁሉንም ዜጎቿን ሁለንተናዊ ብልጽግና እዉን በሚያደርግ መልኩ እንዲደጋገፉ።እንዲረዳዱ።በአብሮነትና በትብብር መንፈስ መሥራት እንደሚገባቸዉ አቅጣጫ ተቀምጧል።
7. በ2013 ዓ.ም የሚካሄደዉ ምርጫ አገራችን ወደ እዉነተኛ የዴሞክራሲ ስርዓት ለምታደርገዉ ሽግግር ያለዉ ትርጉም እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ይታመናል። የሚካሄደዉ ምርጫ ሰላማዊ። ዴሞክራሲያዊ። ነፃና በሂደቱም ሆነ በዉጤቱ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለዉ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የብልጽግና አመራሮች። አባላትና ደጋፊዎች በከፍተኛ ቁርጠኝነት እንዲሠሩ አቅጣጫ ተቀምጧል።
8. ብልጽግና ፓርቲ በመጪዉ ምርጫ ጠንካራ ተወዳዳሪ ሆኖ በዉጤታማነት እንዲያጠናቅቅ በፓርቲዉ ማኒፌስቶ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ አጽድቆታል። መላዉ የፓርቲዉ አመራሮችና አባላት የጸደቀዉን ማኒፌስቶ መሰረት በማድረግ አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተቀምጧል።
9. በአገራችን በህጋዊ መንገድ ተመዝግበዉ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ እዉነተኛ የዴሞክራሲ ስርዓት ለመሸጋገር የተወሰዱ የአገራዊ ለዉጥ ዕርምጃዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም መጪዉ ምርጫ ሰላማዊ። ዴሞክራሲያዊ። ነፃና በሂደቱም ሆነ በዉጤቱ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለዉ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።
10. መላዉ የአገሪቱ ህዝቦች ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት በኢትዮጵያ የታዩ ለዉጦችና የተገኙ ድሎች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ።መጪዉ አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ። ዴሞክራሲያዊ። ነፃና ተቀባይነት ያለዉ ሆኖ እንዲጠናቀቅና የዜጎች ፖለቲካዊ።ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ብልጽግና የተረጋገጠባት ጠንካራ አገር ለመገንባት በሚደረገዉ ርብርብ ዉስጥ የሚጠበቅባቸዉን አስተዋጽኦ ሁሉ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።
ብልጽግና ፓርቲ
ታኅሣሥ 10 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ ዘመን ታህሳስ 11/2013