የዛሬው እንግዳችን የተወለዱት በራያ አላማጣ በ1967 ዓ.ም ነው። አንደኛና የሁለ ተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዚያው በአላማጣ ተምረው አጠናቀዋል። በሁለተኛ ደረጃ መልቀ ቂያ የተሻለ ውጤት በማምጣታቸው በ1989 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ተቀላቅለው የታሪክ ትምህርት አጠኑ። በመቀጠልም በ1998 በሶሻል አንትሮፖሎጂ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አገኙ። በ2002 ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲም በዲዛስተር ኤንድ ሪስክ ማኔጅ መንት በተጨማሪ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሰርተ ዋል። ከስፔን ሀገርም በኢንተርናሽናል ኮኦፕሬ ሽን ኤንድ ሂዩማን ኤድ ማስተርስ ዲግሪ አግኝተ ዋል። በአሁኑ ወቅትም በዴቨሎፕመንት ስተዲሰ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ከትምህርቱ ጎን ለጎንም የራያ ሕዝብን የማ ንነት ጥያቄ ለመመለስ በፖለቲካው ዘርፍ የቆየ ልምድ አካብተዋል። የራያ ሕዝብ ማንነትን በተ መለከቱ ጉዳዮች ዙሪያም ረዘም ላሉ ዓመታት ተሳትፈዋል። በአሁኑ ወቅት ራያ ራዩማ ዴሞ ክራሲያዊ ፓርቲን ከጓደኞቻቸው ጋር በማቋ ቋም በፖለቲካው ውስጥ በስፋት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍልም ከራያ ራዩማ ፓርቲ መስራችና ሊቀመንበር ከሆኑት ከአቶ አገዘው ህዳሩ ጋር ቃለ መጠይቅ በማድ ረግ እንደዚህ አቅርቦታል፦
አዲስ ዘመን– ራያ ራዩማ ፓርቲ መቼ ተመሰ ረተ? የተመሰረተበትስ ዓላማ ምንድን ነው?
አቶ አገዘው ህዳሩ– የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የተመሰረተው የካቲት 29 /2012 ዓ.ም ነው። ይህም ሆኖ ግን ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከሌሎች አጋር አካላትና ከመንግሥት ጋር በመሆን የሕዝቡን የማነ ንነት ጥያቄ ለማስከበር በኮሚቴ መልክ ስንንቀሳቀስ ቆይተናል። ‹‹የራያ ማንነትና የራስ በራስ አስተዳደር ኮሚቴ›› መስርተን ረጅም እርቀት ከተጓዝን በኋላ በፓርቲ ደረጃ ቢዋቀር የበለጠ ትግሉን ከዳር ለማድ ረስ ያስችለናል የሚል እምነት ጨበጥን የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን መሰረትን።
አሁን የማንነት ጥያቄ የሚጠየቅበት የራያ ክፍል ራያ አላማጣ የሚባለውና ወፍላም የተባለው አካባቢ ነው። አካባቢው ቀደም ሲል በወሎ ክፍለሀገር ውስጥ የሚገኝ ነበር። በአሁኑ ወቅት ራያ ጨርጨር፤ ራያ አዘቦ፤ መሆኒ ወረዳና ጨርጨር ወረዳ በትግራይ ግዛት ውስጥ እንዲጠቃለሉ ተደርገዋል። በአማራ አካባቢ ቀድሞ በወሎ ክፍለሀገር ውስጥ የነበሩትን ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመለሱ ጥያቄዎች እየቀ ረቡ ነው። በትግራይ ውስጥ ያሉትም የራያ ሕዝቦች ናቸው። ስለዚህም ሕዝቡ እየጠየቀ ያለው የትም ይገኝ የትም ራያ አንድ ነው። ጥያቄው የአስተዳደር ወሰን ሳይሆን የማንነት ጥያቄ ነው። የራያ ማንነት ሁሉንም አካባቢዎች አቅፎ ግን ደግሞ አስተዳደ ርን በተመለከተ ሕዝቡ ቁጭ ብሎ ተመካክሮ ወዴት አቅጣጫ ብንሆን ታሪካችን ባህላችን፤ ፍላጎቶቻቸችን እምነቶቻችን ሊሳኩ ይችላሉ፤ በሚል አስተዳደሩን መወሰን ይችላል። ማንነትን በተመለከተ ግን በትግ ራይ የነበረው ራያም፤ በወሎ በኩል የነበረው ራያም አንድ ማንነት ስለሆነ ያላቸው ከአስተዳደር ወሰኑ በፊት በቅድሚያ የማንነት ጥያቄው ምላሽ ሊያገኝ ይገባል። የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም ይህ የማንነነት ጥያቄ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ትግሉን ይቀ ጥላል ማለት ነው።
አዲስ ዘመን– የራያ ራዩማ ፓርቲ የሚንቀሳ ቀስባቸው አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው?
አቶ አገዘው፡– ፓርቲው የተመሰረተው በሀገር አቀፍ ደረጃ ነው። የራያ ሕዝብ በየቦታው ተበትኖ ይገኛል። በተለይም በ1977 በተከሰተው ድርቅ በተ ለያዩ አካባቢዎች እንዲሰፍር ተደርጓል። በወለጋ፤ በኢሉባቦር፤እና በሌሎች አካባቢዎችም ተሰባጥሮ ይገኛል። የራያ ሕዝብ ከታሪክ አንጻር ትስስሩ ሰፊ ነው። ራያ ከኦሮሞ ማህበረሰብ፤ ከአማራ፤ ከአገው ጋር ውህድ ማንነት ያለው ግን በታሪክ ሂደት የራሱን ማን ነትን የፈጠረ ነው። ስለዚህም የራያ ማህበረሰብ የሚ ገኝበት አካባቢ በሙሉ የሚንቀሳቀስ ቢሆንም አሁን ግን የራያ ማንነት በተነሳበት አካባቢ ዋነኛ መሠረ ቱን አድርጎ በራያ አካባቢ ይንቀሳቀሳል። ይሁን እንጂ የራያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በራያ ውስጥ እንዲንቀሳ ቀስ በትህነግ አይፈቀድለትም። የራያ ራዩማ ዴሞክ ራሲያዊ ፓርቲንና ሌሎች ትህነግን የሚቃወሙ የፖ ለቲካ ፓርቲዎችን ባንዳ የሚል ተቀጽላ በማውጣት የማሸማቀቅ ሥራ በመስራት ላይ ይገኛል። በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ 12 የሚደርሱ ፓርቲዎች ውስጥም በግ ንባር ቀደምትነት ባንዳ ተብሎ የተፈረጀው ራያ ዲሞ ክራሲያዊ ፓርቲ ነው። ሌሎቹ አረናን የመሳሰሉ ፓር ቲዎች በሁለተኝነት የተፈረጁ ናቸው።
ይህም የሆነበት ዋነኛው ምክንያት የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጠንክሮ ከወጣ ተመሳሳይ የማ ንነት ጥያቄ ያላቸው የአገው፤ የኩናማ፤ የሳሆ፤ የው ጅራትና የኢሮብ ማህበረሰቦች ትግላቸውን ማፋፋማ ቸው አይቀርም። ስለዚህም የራያን የማንነት ጥያቄ ማፈን እና ጥያቄውንም የሚያነሱትንም እያሳደዱ ማጥፋት በዋነኝነት ትህነግ የሚከተለው ስልት ነው።
በጥቅሉ ግን በትግራይ ክልል ትህነግን የሚቃ ወሙ በሙሉ ባንዳ የሚል ተቀጽላ ይሰጣቸዋል። ይህን የሚሉት በምክንያት ነው። ትህነግ ሀገር እያ ስተዳደረ፤ ሕዝብ እየጨቆነና እየዘረፈ ባለበት ሰዓት ጭምር እራሳቸውን ከኢትዮጵያዊነት ውጪ ስለሚ ያደርጉ እና ኢትዮጵያዊነት ስለማይሰማቸው ኢትዮ ጵያውያንን በሙሉ ባንዳ ብለው የመፈረጅ ዕሳቤ አላቸው። የትህነግ አባላት ኢትዮጵያዊ ሥነልቦና ስሌላቸው ኢትዮጵያዊ ስሜት ያለው በሙሉ ለእነሱ ባንዳ ነው። ከትህነግ አስተሳሰብ ውጪ ያለ በሙሉ ለእነሱ ባንዳ ነው። ሆኖም ግን ኢትዮጵያውያን ባንዳ ብለው ስያሜ የሚሰጡት የሀገርን ጥቅም ለውጭ ጠላት አሳልፎ የሚሰጥ ከሃዲን እንጂ ኢትዮጵያዊ ዜጎችን እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በሌላም በኩል እን ገነጥላታለን ብለው ለሚያስቧት የትግራይ ዲፋክቶ ስቴት እንቅፋት የሚሆንን በሙሉ ባንዳ እያሉ ይፈ ርጁታል። የራያ ራዩማ እንቅስቃሴ ደግሞ ያሰቡትን የዲፋክቶ ስቴት የሚያኮላሽባቸው ዋነኛ እንቅስቃሴ ስለሆነ አምርረው ይጠሉታል።
አዲስ ዘመን– የራያ ማንነትን ለማስከበር ስትንቀሳቀሱ የገጠማችሁ ችግር አለ?
አቶ አገዘው፡– ከፍተኛ ችግር የገጠመን ብዙዎች ህወሃት ብለው ከሚጠሩት እኛ ግን ትህነግ ብለን ከምንጠራው ድርጅት ነው። ህወሃት ብለን መጥራት የማንፈልገው ‹‹ወያኔ›› የሚለው ቃል ከራያ ሕዝብ ጋር የተያያዘ የትግል መጠሪያ ነው። ወያኔ የሚለውን የትግል መጠሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙበት ራያዎች ናቸው። ከሰሜን ሸዋ ጫፍ ጀምሮ ውጅራት ድረስ ለማንነት የተደረገው ትግል ወያኔ የሚል መጠሪያ ነበረው። ትግሉም ወታደራዊ መልክ የነበ ረው ነው። በተለይም ከጣሊያን ወረራ በኋላ በ1933 ዓ.ም አካባቢ ይህ የራያ ማነንት ጥያቄ ወያኔ በሚል የትግል ስም በገበሬው አማካኝነት ሲካሄድ ቆይቶ በኋላ ሌሎች መጠሪያውን የራሳቸው አስመስለው ወስደውታል። ወያኔ የሚለው ታሪክ ከራያ ሕዝብ የተወረሰ ታሪክ ነው። ስለዚህም ወያኔ የሚለው መጠሪያ የራያዎች የትግል መጠሪያ ነው። ስለዚህም አሁን ወያኔ ብለው እራሳቸውን የሚጠሩትን እኛ ትህነግ ነው የምንላቸው።
ስለዚህም የራያ ማንነት ጥያቄን ስናነሳ ከፍተኛ ተግዳሮት የገጠመን ከትህነግ ነው። የራያ አካባቢ ሰፊና ለም አካባቢ ነው። ለእርሻ በጣም ተስማሚ ነው። ትህነግም ይህንን አካባቢ በግድ በመውሰድ የትግራይን የምግብ ፍላጎት ለማሟላት አቅዶ ሲን ቀሳቀስ ቆይቷል። እንደሚታወቀው የትግራይ አብዛ ኞቹ አካባቢዎች ደረቅና ለእርሻ ተስማሚ ባለመሆና ቸው የራያን አካባቢዎች ዋነኛ የግብርና ምርት ማግኛ አድርገው ተስፋ ጥለውባቸዋል። ትግራይ ትገነጠላ ለች የሚል አዋጅ የሚጎሰመውም የራያን ለም መሬት በመተማመን ነው። ራያን ወደ ትግራይ ለመውሰድ የታቀደው በ1968 ዓ.ም አካባቢ ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ሥራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል። ስለዚህም እኛ ይህንን ሃቅ መግለጽ ስንጀምር በርካታ ተጽዕኖ ዎች ሲደርሱብን ቆይተዋል። ከማሳደድና መግደል ጀምሮ በራያ ውስጥ በነፃነት እንዳንንቀሳቀስ ተደርገ ናል። በተለይም የራያን ኅብረተሰብ የራያራዩማ ዴሞ ክራሲያዊ ፓርቲ ደጋፊዎቻ ናችሁ በማለት የማንገላ ታትና ኅብረተሰቡም በልዩ ልዩ የማሰቃያ መንገዶች ተማሮ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ እየተደረገ ነው። የራያ ማንነትን የሚያቀነቅኑ ግለሰቦችን አድኖ ከመግ ደል አንስቶ የማህበረሰቡን ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለ ሰቦችን ስልታዊ በሆነ መንገድ የመግደልና የማጥፋት ሥራዎችን ሀገሪቱን ማስተዳደር ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ሲሰሩ ቆይተዋል። የራያ ማንነትን የጠየቁ ሰዎች ኮረም ከተማ ላይ በገበያ መሃል ሕዝብ በተሰበ ሰበበት በገሃድ እንዲረሸኑ ተደርገዋል።
ከዚያ በኋላ የትህነግ ጥቃት እያየለ በመም ጣቱ የራያ ማንነት እንዳይጠፋ የሚያግዙ ሥራ ዎችን በህቡዕ መስራት ጀመርን። የራያን ባህል፤ ታሪክና ማንነት ላይ የተመረኮዙ የጥናትና ምርምር ሥራዎች በምሁራንና በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በማ ስጠናት ለህትመት የማብቃትና በመጽሐፍም የማሳ ተም ሥራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል። በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ከ29 የማያንሱ የመመረቂያ ጽሑፎች በራያ ማንነት፤ ባህልና ታሪክ ዙሪያ እንዲዘጋጁ ተደርጓል። እነዚህ ሥራዎችም የራያ ማንነት እንዳይበረዝና እንዳይከለስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።
ትህነግ ፌዴራሊዝም በሚል ማሳሳቻ ሁለት ስል ቶችን ይጠቀም ነበር። ትግራይ ውስጥ ራያ አለ፤ ኩናማ አለ፤ ሳሆ አለ፤ አገው አለ። እነዚህን ማንነቶች ጨፍልቆ አንድ የትግራይ ማንነት ለመፍጠር ይንቀ ሳቀሳል። በትግራይ ምንም ዓይነት የማንነት ልዩነት እንደሌለ ተደርጎ እና ተጨፍልቆ ሕዝቡ እንዲኖር ተፈርዶበታል። በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ የማን ነት ያልሆኑ ትናንሽ ልዩነቶችን በማስፋትና በመለ ጠጥ ኅብረተሰቡ በግጭት አዙሪት ውስጥ እንዲቆይ ሲያደርግ ቆይቷል። ጎንደር፤ ወሎ፤ ኦሮሚያ፤ ደቡብ፤ ቤኒሻንጉልና ጋምቤላ በዚህ መልኩ ያለልክ ልዩነቶ ችን በማስፋት ኅብረተሰቡ እርስ በእርስ እንዳይተማ መንና አበረው ለዘመናት የኖሩ ጎረቤታሞች ጭምር እርስ በእርስ እንዲጠፋፉ ተደርገዋል። ብዙዎች ለዘ መናት ከኖሩበት ቀዬም ተፈናቅለዋል። ሌላው ቢቀር አንድ የሆነውን የኦሮሞ ብሔረሰብ በመከፋፈል የማዳከም ዕቅዶች ነበሩ። የትህነግ ባለሥልጣኖችና የዚሁ ፓርቲ ምሁራኖች አርሲና ባሌን ኦሮሞ ነው ብለው አያምኑም። የአርሲና ባሌ ኦሮሞ ሃድያ ነው ብለው አቅደው ብሔረሰቡን የመከፋፈል ውጥን ነበ ራቸው። ከአማራም ቀጥሎ በስፋት የመከፋፈል ሥራ ለመስራት ያቀዱት ኦሮሞ ላይ ነበር።
የጋራ ማንነት በዘመናት ሂደት የፈጠሩ ግን ደግሞ በግጦሽና በሌሎችም ፍላጎቶች የሚጋጩ ማህ በረሰቦችን ልዩነቶችን በማጦዝ ሰፊ ልዩነት እንዳለ የማስመሰል ተግራት በስፋት ሲሰሩ ቆይተዋል። ቤኒ ሻንጉል ብትሄድ ለዘመናት የእርስ በእርስ ማንነት ያዳበሩ ማህበረሰቦች እንዲጋጩና በጥርጣሬ እንዲተ ያዩ ተደርገዋል። ጋምቤላ ብትሄድ በአኝዋክና በንዌር መካከል ከፍተኛ ግጭት እና መተላለቅ እንዲኖር አድ ርገዋል። በተለይም የጠነከረ ማንነት ያለው የንዌር ብሔረሰብ የእርሻ ቦታውን በኢንቨስትመንት ስም እንዲቀማ በማድረግና በግጭቱ ውስጥ ተጎጂ እንዲ ሆን ተደርጓል።
በሶማሌ ክልልም ተመሳሳይ ክልሉን የማተራ መስ ሥራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል። የሶማሌ አካባቢ የኮ ንትሮባንድ መውጫ መግቢያ በር በመሆኑና በተለ ይም ከፍተኛ የሆነ ሕገወጥ የዶላር ዝውውር የሚ ካሄድበት በመሆኑ በዚህ ሕገወጥ ተግባር ያለማንም ከልካይ ለመሳተፍ ክልሉን የማተራመስና በሽብርተ ኝነት ስም የማመስ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል። ለዚህ ነው ትህነግ ወደ መቀሌ ከሸሸ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሶማሌ ክልል ሰላም የሰፈነበት አካባቢ መሆን የቻለው።
የራያ እንቅስቃሴ በተመሳሳይ መልኩ ከትህነግ ጥቃት እንደሚደርስበት ግልጽ ነው። በአሁኑ ወቅት ባንዳ የሚል ስያሜ በመስጠት ወደ ራያ አካባቢ እን ዳንገባ ተደርገናል። የራያ ማንነት ከዳር ለማድረስም ‹‹ስበር›› በሚል መጠሪያ ተደራጅቶ የተለያዩ እንቅ ስቃሴዎችን የሚያደርገውን ወጣት በገፍ በማሰርም ጥያቄውን ለማፈን ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ባለፉት ሁለት ዓመታት ስበር ባደረገው እን ቅስቃሴም በመደናገጥ የተለያዩ የኃይል እርምጃዎች ወስደዋል። ከ17 በላይ ወጣቶች ተገድለዋል። ከ2ሺ በላይ ወጣቶች አሁንም ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅትም ምርጫ እናካሂዳለን በሚል ቅስቀሳ ምርጫውን የሚያደናቅፍ ግለስብም ሆነ ቡድን እርምጃ እንደሚወሰድበት በግልጽ እየዛቱ ነው።
በራያ ወረዳዎች ማለትም በጨርጨር፤ በመሆኒ፤ አላማጣ፤ ወፍላ ወረዳዎች በአንድ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ሰላሳ ሰዎችን በማዋቀር ኅብረተሰቡን እንዲሰልሉ እየተደረገ ነው። የተወሰኑት ተቃዋሚዎ ችን በእነሱ አጠራር ባንዳዎችን መንጥሮ የሚያወጣ፤ ሌላው ደግሞ ጸጉረ ልውጥ አሳሽ፤ የተቀረው እነሱ እንጀምረዋለን ብለው የሚያስቡት ጦርነት ሲጀመር ምግብና ውሃ የሚያስተባብር ቀሪው ደግሞ ሙትና ቁስለኛ የሚያነሳ አድርገው አደራጅተውታል። በተ ጨማሪም ትራንስፖርትና ሌሎች ሎጅስቲኮችን የሚያቀርብ ቡድንም የዚሁ አካል ተደርጎ ተዘጋጅ ቷል። በአጠቃላይ ትህነግ ተከበሃል በሚል ውዥን ብር ወጣቱን ለጦርነት እየመለመለ ይገኛል። በተለ ይም ከሃጫሉ ህልፈት በኋላ የትህነግ አፈና በእጅጉ ጨምሯል።
አዲስ ዘመን፡– ከሃጫሉ ህልፈት በኋላ አፈናው የጨመረበት ምክንያት ምንድን ነው ?
አቶ አገዘው፡– ሃጫሉ ከመሞቱ ጥቂት ቀናት በፊት ትህነግ ከፍተኛ መተማመን አዳብሮ ነበር። ‹‹አዲስ አበባ ጀምረን አዲስ አበባ እንጨርሰዋለን›› የሚለው የአቶ ስዩም መስፍን አባባል በሁሉም የትህነግ መዋቅር ውስጥ ገብቶ ነበር። እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ይህ አባባል ሰርጾ ገብቶ ነበር። የሃጫ ሉን ሞት ትህነግ ሁልጊዜ ለሚያልመው ዳግም ወደ ሥልጣን የመመለስ ወይም ኢትዮጵያን የማፈራረስ ትልም የሃጫሉን ሞት እንደትልቅ ብስራት ነው የቆ ጠሩት። ሆኖም ግን የቀየሱት ዕቅድ ሲመክን በጣም አሸማቋቸዋል። ሕዝቡም እንደታዘባቸውና ድጋፉ ንም እየነፈጋቸው መምጣቱን በመረዳታቸው ሙሉ ለሙሉ ከቁጥጥራቸው ሳይወጣ በአፈና እንዲገዛቸው እያደረጉ ነው። በተለይም ቀድሞውንም የሚቃወማ ቸውን አካባቢ እስከግድያ ድረስ የሚደርስ እርምጃ በመውሰድ ጸጥ ብሎ እንዲገዛ ለማድረግ እየሞከሩ ነው። ሕዝቡም እንዲሸበር ልዩ ኃይሎችንና ሚሊሻ ዎችን በማዟዟር የጦር አቅማቸውን ለማሳየት እየሞ ከሩ ነው። ይባስ ብሎም ለሚሊሻው ቀለብ እንዲሰፍ ርና ለሚሊሻው ደመወዝ ጭምር እስከአምስት መቶ ብር ድረስ እንዲያዋጣ ግዴታ እየተጣለበት ይገኛል። ገንዘብ የለኝም ያለ ጤፍና ስንዴ በመስፈር እንዲያስ ረክብ ግዴታ ተጥሎበታል።
አዲስ ዘመን፡– የአካባቢው የሕዝብ አሰፋፈር ምን ይመስላል?
አቶ አገዘው፡– በራያ ባሉ አራት ወረዳዎች አብ ዛኛው ሕዝብ ለዘመናት የኖረ ነባር ሕዝብ ነው። በተ ለይም ገጠሩ ያልተበረዘ የራያ ባህልና ማንነት ያለው ነው። ከተማውም ቢሆን አብዛኛው የራያ ሕዝብ ነው። ሆኖም ግን ይህንን የሕዝብ ስብጥር ለመቀየር ራያ ቫሊ የሚባል ፕሮጀክት በትህነግ ተነድፎ ነበር። ይህ ፕሮጀክት በቀድሞ የትህነግ አባል በአቶ ገብሩ አስራት አማካኝነት የተነደፈ ነው። በልማት ስም የሚፈልጉትን ኅብረተሰብ በማስፈር የአካባቢውን የሕዝብ ስብጥር ለመቀየር ታልሞ ሲሰራበት የቆየ ነው። ሆኖም ግን ትህነግ በ1993 ሲከፋፈል እነገብሩ አስራት በመባረራቸው ፕሮጀክቱ ተቋርጧል። ይህ ለራያ ሕዝብ መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል። ሴራውን ያልተረዱ ግን ልማቱ እንደተቋረጠ ያስባሉ።
ሆኖም ግን አሁንም በጨርጨርና በመሆኒ ወረዳ ዎች ሰፋፊ እርሻዎች በትህነግ ባለሀብቶች ተይዘዋል። በነዚህ ሁለት ወረዳዎች ሰፋፊ እርሻዎችን የያዙ አርባ ባለሀብቶች ሲገኙ ሰላሳስምንቱ በትህነግ አመራሮች የተያዙ ናቸው። ሆኖም ኅብረተሰቡ እያደረገ ባለው ተቃውሞ እነዚሁ የትህነግ አባላት እርሻዎቹን እየለ ቀቁ መሄድ ጀምረዋል። በአጠቃላይ ግን የሕዝቡ አሰ ፋፈር የራያ ሕዝብ የጎላውን ድርሻ የሚይዝበት ነው።
አዲስ ዘመን፡– ትህነግ ኢትዮጵያዊነትን እንደሚጠላ ብዙዎች ሲናገሩ ይደመጣሉ፤ የራያ ሕዝብ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት በደም ስሩ የሚገኝ ሕዝብ ነው፤ ሁለቱ ልዩነቶች እንዴት ይጣጣማሉ?
አቶ አገዘው፡– ትህነግ ገና ከምስረታው ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ማንነት ያልነበረው ድርጅት ነው። ይህ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መስዋዕትነት ከከፈለው የትግ ራይ ሕዝብም ሆነ ከራያ ሕዝብ ጋር ፍጹም የተራራቀ ነው። አሁን አሁን የትህነግን ሴራ እና ኢትዮጵያን ጠልነት የተረዱ ወላጆች ‹‹እንዲህ መሆኑን ብናውቅ ልጆቻችንን ባልገበርን›› የሚሉ ድምጾችን እያሰሙ ነው። ገና በረሃ እያሉ ኢትዮጵያዊ ስሜት ያላቸውን ታጋዮች አድነው አጥፍተዋቸዋል። ኢትዮጵያዊ ዕሴ ቶችንም ቀሰበቀስ እያጠፉ ሕዝቡ የማንነት ቀውስ ውስጥ እንዲገባ ብዙ ሰርተዋል። ሥልጣን ከያዙ በኋላ መጀመሪያ የሰሩት ይህ ለዘመናት የኖረ ሕዝብ ምንም የጋራ ማንነትና ጉዳይ እንደሌለው አድርጎ መሳል ነው። ይህንኑ ሃሳባቸውን ባረቀቁት ሕገመን ግሥት ጭምር በማስደገፍ ዕውቅና እንዲያገኝ አድር ገዋል። ኤርትራውያን እስኪገርማቸው ድረስ የአሰብ ወደብ ለኢትዮጵያ አይገባትም ብለው ተከራክረዋል።
የትህነግ ካድሬዎች አጀንዳ እየተሰጣቸው የሚ ያቃርኑ ጉዳዮችን በመያዝና የጋራ ማንነቶችን ለመበ ጣጠስ የሚያስችሉ ትርክቶችን በማንገብ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን የማኮላሸት ሥራዎች በስፋት ሲሰሩ ቆይተዋል። የትህነግ አባላት እንኳ ኢትዮጵያዊ ነትን በትግራይዋን መካከል እንኳን ልዩነቶችን የሚፈጥሩ ጠባቦች ናቸው። ለትህነግ ተመራጩ ዜጋ የአድዋ ተወላጅ የሆነው ሰው ብቻ ነው። አሁን ያሉትን የትህ ነግ ቁንጮዎችን እንኳን ብንመለከት በጣት ከሚቆጠ ሩት በስተቀር የአድዋ ተወላጆች ናቸው። አሁን በሥ ልጣን ቁንጮው ላይ ከሚገኙት ሰዎች ጋር ሲታገሉ የነበሩ የትግራይ ልጆች ድህነት ተጭኗቸው ወድቀው ቀርተዋል። በአሁኑ ወቅት በሕዝብ ትግል ጥጋቸውን ይዘው የሚገኙትም እነዚህ የጥፋት ኃይሎች መቀሌ ተቀምጠው ኢትዮጵያን የማተራመስና የማፍረስ ሥራ በመስራት ላይ ይገኛሉ። የህልማቸው መጨረ ሻም ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው።
አዲስ ዘመን፡– የትግራይ ሕዝብ በትግል ሂደቱ ልጆቹን ገብሮ ከትግሉ ምን አገኘ ብለው ያስባሉ?
አቶ አገዘው፡– ለ17 ዓመታት በተካሄደው ጦርነት የትግራይ ሕዝብ ብዙ መስዋዕትነት እንደከፈለ ግልጽ ነው። በጦርነት ልጆቹን ከመገበር አንስቶ በርካታ ሰቆቃና ግፍ ቀምሷል። ሆኖም ግን ትግሉን ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በመሆን በድል ከተወጣ በኋላ ያጋጠመው የባሰ ስቃይና መከራ ነው። የትግ ራይ ሕዝብ እኮ እንደልቡ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ እንዳይ በላ አድርገውታል። እነሱ በሰሩት ሥራ እንዲሸማቀቅ ፈርደውበታል። 2004 ዓ.ም አካባቢ ወደ አዲግራት ለሥራ በሄድኩበት ወቅት አንድ አባት ያሉኝ ትዝ ይለኛል። ትንሽ ከተጨዋወትን በኋላ ሥራ እንዴት ነው? ኑሮ እንዴት ነው? የሚል ጥያቄ አነሳሁላቸው። ‹‹አዬ ልጄ ምን ሥራ አለ ብለህ ነው፤ የገዛ ልጆቻችን ሀገራችንን አጥብበውብን›› የሚል አስገራሚ ምላሽ ሰጡኝ። የሽማግሌው አባባል የአብዛኛውን የትግራ ይን ሕዝብ ስሜት የሚገልጽ ይመስለኛል።
የመቀሌ አካባቢ አርሶ አደር እኮ በአዲስአበባ ዙሪያ ከሚገኘው የኦሮሞ አርሶ አደር ቀጥሎ መሬቱን የተዘረፈና ይህ ነው በማይባል ሽራፊ ሳንቲም ለትህ ነግ ባለሀብቶችና ባለሥልጣናት ሸጦ ሜዳ ላይ የቀረ ሕዝብ ነው። በአጠቃላይ ትግራይ ሕዝብ እንኳን ሊጠቀም ቀርቶ በብዙ መልኩ ተጎድቷል የሚል እምነት ነው ያለኝ።
አዲስ ዘመን፡– ህወሃት ምርጫ ለማካሄድ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ በእርግጥ ህወሃት ምርጫ ውን ያካሂዳል ብለው ያስባሉ?
አቶ አገዘው፡– ቀደም ሲል ጀምሮ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎችን ሲያወያይ ብልጽግና ፓርቲና ትህነግ ምርጫው እንዲካሄድ ፍላጎት አሳይተዋል። ሆኖም ግን የኮሮና ቫይረስ በፈጠረው ስጋት ብልጽግና ፓርቲ የነበረውን ፍላጎት ሲተው ትህነግ ግን የኮሮና ቫይረስ ስጋትን ወደጎን በመተው ምርጫውን አካሂ ዳለሁ ብሎ ሙጭጭ ብሏል። አሁን ባለኝ መረዳ ትና ትህነግ ከገጠመው አጣብቂኝ አንጻር ምርጫውን ማካሄዱ አይቀሬ ይመስለኛል። ምርጫውን የሚያካ ሂደው ለሕገመንግሥቱ ጠበቃ በመሆን፤ ሕግን በማ ክበር፤ ለኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄ በማድረግ ወይም ለት ግራይ ሕዝብ በማሰብ ሳይሆን ምርጫውን ከገባበት አጣብቂኝ ውስጥ መወጣጫ ለማድረግ ነው። ትህነግ ሁሉም ፓርቲዎች ከተሳተፉ በምርጫው ተወዳድሮ እንደማያሸንፍ ያውቃል። ስለዚህም ሌሎች ፓርቲ ዎች የኮሮና ቫይረስንና ሌሎችንም ሀገራዊ ጉዳዮች ከግምት ውስጥ በማስገባት ምርጫውን ከማካሄድ በተቆጠቡበት ወቅት ብቻውን ተወዳድሮ ብቻውን ለማሸነፍ ወጥኖ እየሰራ ነው። እንደ አብነት በራያ አካባቢ ተወዳድሮ አንድ ድምጽ እንደማያገኝ ያውቀ ዋል። በመቀሌ እና እንደርታ የብልጽግና ፓርቲ ተቀ ባይነት እያገኘ መጥቷል። አረና ፓርቲ ህውዜንና ተንቤን ላይ ያሸንፋል። ኢሮብ ላይ አሲንባ ፓርቲን መወዳደር አይችልም። በሌሎችም አካባቢዎች ተመ ሳሳይ ዕጣ እንደሚገጥመው የታወቀ ነው። ስለዚ ህም ይህችን ወቅት ለብቻው ተወዳድሮ ብቻውን ለማሸነፍ እንደምቹ አጋጣሚ ለመጠቀም አስቧል። አሁን እንኳን የምርጫ ኮሚሽን ተደርገው የተመ ረጡት ሰዎች ትግራይ መገንጠል አለባት በማለት የከረረ አቋም የሚያራምዱ ሰዎች ናቸው። በእነዚህ የምርጫ አስፈጻሚዎች የሚካሄድ ምርጫ ህወሃትን ከማስመረጥ የዘለለ ፋይዳ እንደማይኖረው ግልጽ ነው። ስለዚህም ትህነግ ያለውን ቀዳዳ በመጠቀም ምርጫውን ማካሄድ ብቸኛ አማራጭ አድርጎ ወስ ዶታል። በሌላ በኩል በሕዝብ ተመርጫለሁ በሚል ማሳሳቻ ጊዜ ለመግዛትም የምርጫው መካሄድ ለት ህነግ ይጠቅመዋል።
የሆኖ ሆኖ ግን ይህንን ሴራ ከግምት ውስጥ በማ ስገባትና በሀገሪቱ ውስጥ እየፈጸመ ባለው የሽብር ድርጊት ትህነግ እንደፓርቲ ሳይሆን በሽብርተኝነት ተፈርጆ ከሰላማዊ ትግል ውስጥ መፋቅ አለበት የሚል እምነት አለኝ።
አዲስ ዘመን፡- ህወሃት ምርጫውን ለማካሄድና ተቀባይነት ለማግኘት እየተከተላቸው ያሉ ስልቶች ምንድን ናቸው?
አቶ አገዘው፡– ህወሃት ሕዝቡን እያደናገረባ ቸው ያሉ አጀንዳዎች አሉ። የመጀመሪያው ህዳሴ ግድብ ነው። የህዳሴ ግድብ ተሸጧል የሚል አሉ ባልታ በመንዛት ሕዝቡ በፌዴራል መንግሥት ላይ ጥርጣሬና ጥላቻ እንዲያሳድር አበክረው ሲሰሩ ቆይተዋል። አሁን መንግሥት የመጀመሪያውን ውሃ ሙሌት ማድረጉን ሲያሳውቅ ነገሩን ማድበስ በስ ጀምረዋል። ሕዝቡም ተራ አሉባልታ መሆኑን ተረድቶ ታዝቦ አልፏቸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ሀገሪቱ እየፈረሰች ነው የሚል የማስፈራሪያ ወሬ በመንዛት ሕዝቡን ሽብር ውስጥ ለመክተት ሲጥሩ ቆይተዋል። ይህ ከሃጫሉ ሞት ጋር ተያይዞ ዕቅዳቸው ሙሉ ለሙሉ ሲከሽፍ መልሰው ትተውታል። በቅርቡ ደግሞ የፌዴራል መንግሥትና ኤርትራ መንግሥት ሊወራችሁ ነው ታጥቃችሁ ጠብቁ የሚሉ ማስፈራሪያዎችን በማሰ ራጨት ወጣቱን በስፋት በማስታጠቅ ላይ ይገኛሉ። የአብይ መንግሥት ከውጭ ወራሪ ጋር በመሆን ሊወርህ ነው በሚል ሕዝቡ ሌላ ስሜት ውስጥ እን ዲገባ እያደረጉት ነው። በአጠቃላይ ህወሃትን ካልመ ረጥክ አደጋ ውስጥ ትገባለህ የሚል ሰፊ ፕሮፓጋን ዳና ቅስቀሳ እያካሄዱ ነው።
አዲስ ዘመን፡– ህወሃት ዲፋክቶ ስቴት ለመ መስረት ዕቅድ እንዳለው ይሰማል፤ ይህ ምን ያህል እውነት ነው፤ የመሳካት ዕድል አለው ወይ?
አቶ አገዘው፡– የራያ፤ የወልቃይት፤ የኢሮብ፤ የዋጅራትና ሌሎችም ሕዝቦች ኢትዮጵያዊነት መለያቸው የሆነ ሕዝቦች ናቸው። ከኢትዮጵያዊ ነት የበለጠ ማንነት የላቸውም። ስለዚህም እነዚህ ሕዝቦች ባሉበት ትግራይን መገንጠል አይችሉም። የትግራይ ሕዝብም በኢትዮጵያዊነቱ የሚደራደር አይደለም። ስለዚህም ይህ ከቅዠት የዘለለ አይመስለ ኝም። ትህነግ ቢመኘው እንኳን የሚሳካ አይደለም።
አዲስ ዘመን፡– የትግራይ ሕዝብና ህወሃት አንድ ናቸው የሚለው አባባል በአሁኑ ወቅት ምንያህል ውሃ ይቋጥራል?
አቶ አገዘው፡– እንኳን የተለያዩ ማንነቶች ያሉበት አካባቢ ቀርቶ አንድ ማንነት ያለበት አካባ ቢም ቢሆን በአንድ ፓርቲ ብቻ አይወከልም። ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት በአካባቢው አራትና አምስት ማንነቶች ባሉበት ሁኔታ እኔብቻ ነኝ የትግ ራይ ሕዝብ ወኪል ማለት ሕዝቡን ካለማወቅ የሚ መነጭ ይመስለኛል። ሌላው ቢቀር ትህነግ የጥቂት ቡድኖች ስብስብ በመሆኑ የጥቅም ተጋሪ ከሆኑ ግለ ሰቦችና የቤተሰብ አባላት ውጪ ይህ ነው የሚባል ደጋፊ ያለው አካል አይደለም። ስለዚህም የትግራይ ሕዝብና ህወሃት አንድ ናቸው የሚለው ከተራ ፕሮ ፖጋንዳ ያለፈ አይደለም። መሬት ላይ ያለውም ሃቅ ይሄ አይደለም።
አዲስ ዘመን፡– የህወሃትን መሠረት የሚውቁ ሰዎች ህወሃት በመቃብር አፋፍ ላይ ይገኛል ሲሉ ይደመጣሉ፤ ይስማሙበታል?
አቶ አገዘው ህዳሩ፡- በሚገባ። ህወሃት በሰ ራቸው መጥፎ ሥራዎች በርካታ ጠላቶችን አፍር ቷል። የትግራይ ሕዝብም እየተፋው ነው። ሌሎችም የታፈኑ አካላት መብታቸውንና ማንነታቸውን በድፍ ረት እየጠየቁ ነው። ሕዝቡ ከፍርሃት ቆፈን ተላቋል። ሕዝብን አፍኖ ዘላለም መኖር ስለማይቻል ዛሬ የሕ ዝቦች ትግል ፍሬ አፍርቶ ህልውናው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። ሌላው ይቅርና በትህነግ ውስጥ እራሱ አካሄዱን የሚቃወሙ አካላት ድምጻቸውን ማሰማት ጀምረዋል። በጎ ህሊና ያላቸው አባላቱ አካ ሄዱን እየተቃወሙት ነው። በዚህ ሁኔታም በመደና ገጥም በቅርቡ የካቢኔ ሽግሽግ ለማድረግ እስከማሰብ ደርሷል። በተለይም ያለማንም ከልካይ ሲያጋብሱት የነበረው ገቢ በመቀነሱ እንዳሻው የፈለገውን ለማ ድረግና በጥቅም ለመደለል እጅ አጥሮታል። እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተደማምረው ትህነግ በመቃብር አፋፍ ላይ እንዲገኝ አስገድደውታል።
አዲስ ዘመን፡– ለነበረን ቆይታ በአዲስ ዘመን ዝግጅት ክፍል ስም ምስጋናዬን አቀርባ ለሁ።
አቶ አገዘው፡– እኔም አመሰግናለሁ።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012
እስማኤል አረቦ