በጥረት ኮርፖሬት ከህግና መመሪያ ውጭ ግዥ በመፈፀም የሃብት ብክነት ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዝጋለ ገበየሁ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት የጥረት ኮርፖሬት አክሲዮን ማህበሩ ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች በአምስት ካምፓኒዎች ላይ በተደረገ የሒሳብ ምርመራ የሃብት ብክነት ማድረሳቸው ተረጋግጧል። እስካሁን በአምስት ካምፓኒዎች ላይ የተደረገ የሒሳብ ምርመራ የተጠናቀቀ ሲሆን በሁለት ካምፓኒዎች ላይ የሚካሄደው የሒሳብ ምርመራም በሂደት ላይ ነው፡፡
በተለይም ባህር ዳር ሞተርስ፣ ላፓልማ፣ ኢስታንቡል ጋዝ ማምረቻ፣ በየዳ ሰስቴኔብል ኬሚካል ማምረቻና ደሴ መጠጥ ውሃ ማምረቻ ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ማህበራት የሒሳብ ምርመራ የተደረገባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።
እንደ ኮሚሽነር ዝጋለ ገለጻ ለእነዚህ አክሲዎን ማህበሮች 77 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ግዥ የተፈፀመ ቢሆንም ከዚህ ውስጥ ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ያለአግባብ ክፍያ ተፈፅሞ ተገኝቷል። ይህ ገንዘብ የወጣባቸው አክሲዮን ማህበራት ስራም አልጀመሩም፤ ለማህበራቱ ተብለው የተገዙ ንብረቶችም ካለአግባብ ለብልሽት ተዳርጎ ተገኝቷል።
የዳሸን ቢራ ፋብሪካና የዱቤቱስ አክስዮን ማህበር በሒሳብ ምርመራ የማጣራት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ኮሚሽነሩ አመልክተዋል። በመሆኑም ማህበሩን በከፍተኛ ኃላፊነት ይመሩ የነበሩት ሁለቱ ግለሰቦች የካምፓኒዎቹን የአዋጭነት ጥናት ሳይካሄድ ግዥ እንዲፈፀም በማድረግ በህዝብ ሃብት ላይ ጉዳት ማድረሳቸው በመረጋገጡ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።
’’ከእዚህ በተጨማሪ ከፋይናንስ ህግና ደንብ ውጭ በግለሰቦች ውሳኔ ብቻ ብድር ለግለሰቦችና ለድርጅቶች ሲሰጥ መቆየቱን ለማወቅ ተችሏል” ብለዋል። በመሆኑም ሙስናውን በዋናነት አንቀሳቅሰዋል የተባሉ ሁለቱ ግለሰቦች በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንዲታይ ለማድረግ ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።
በቀጣይም ከእነሱ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ያላቸውን አመራሮችም ሆነ ግለሰቦችን በማጣራት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የሚደረግ መሆኑን የገለጹት አቶ ዝጋለ፤ የሁለቱ ተጠርጣሪ ግለሰቦች የህግ ጉዳይ በክልሉ የሚታይ መሆኑን ጠቁመው፣ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የክልሉ የፖሊስ ኃይል ከፌዴራልና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ መስራቱን አስታውቀዋል። በጥረት ኮርፖሬት ላይ የተጀመረው የማጣራት ሥራም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነር ዝጋለ አብራርተዋል።
ማድረሳቸው ተረጋግጧል። እስካሁን በአምስት ካምፓኒዎች ላይ የተደረገ የሒሳብ ምርመራ የተጠናቀቀ ሲሆን በሁለት ካምፓኒዎች ላይ የሚካሄደው የሒሳብ ምርመራም በሂደት ላይ ነው፡፡
በተለይም ባህር ዳር ሞተርስ፣ ላፓልማ፣ ኢስታንቡል ጋዝ ማምረቻ፣ በየዳ ሰስቴኔብል ኬሚካል ማምረቻና ደሴ መጠጥ ውሃ ማምረቻ ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ማህበራት የሒሳብ ምርመራ የተደረገባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።
እንደ ኮሚሽነር ዝጋለ ገለጻ ለእነዚህ አክሲዎን ማህበሮች 77 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ግዥ የተፈፀመ ቢሆንም ከዚህ ውስጥ ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ያለአግባብ ክፍያ ተፈፅሞ ተገኝቷል። ይህ ገንዘብ የወጣባቸው አክሲዮን ማህበራት ስራም አልጀመሩም፤ ለማህበራቱ ተብለው የተገዙ ንብረቶችም ካለአግባብ ለብልሽት ተዳርጎ ተገኝቷል።
የዳሸን ቢራ ፋብሪካና የዱቤቱስ አክስዮን ማህበር በሒሳብ ምርመራ የማጣራት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ኮሚሽነሩ አመልክተዋል። በመሆኑም ማህበሩን በከፍተኛ ኃላፊነት ይመሩ የነበሩት ሁለቱ ግለሰቦች የካምፓኒዎቹን የአዋጭነት ጥናት ሳይካሄድ ግዥ እንዲፈፀም በማድረግ በህዝብ ሃብት ላይ ጉዳት ማድረሳቸው በመረጋገጡ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።
«ከእዚህ በተጨማሪ ከፋይናንስ ህግና ደንብ ውጭ በግለሰቦች ውሳኔ ብቻ ብድር ለግለሰቦችና ለድርጅቶች ሲሰጥ መቆየቱን ለማወቅ ተችሏል» ብለዋል። በመሆኑም ሙስናውን በዋናነት አንቀሳቅሰዋል የተባሉ ሁለቱ ግለሰቦች በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንዲታይ ለማድረግ ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።
በቀጣይም ከእነሱ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ያላቸውን አመራሮችም ሆነ ግለሰቦችን በማጣራት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የሚደረግ መሆኑን የገለጹት አቶ ዝጋለ፤ የሁለቱ ተጠርጣሪ ግለሰቦች የህግ ጉዳይ በክልሉ የሚታይ መሆኑን ጠቁመው፣ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የክልሉ የፖሊስ ኃይል ከፌዴራልና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ መስራቱን አስታውቀዋል። በጥረት ኮርፖሬት ላይ የተጀመረው የማጣራት ሥራም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነር ዝጋለ አብራርተዋል።
አዲስ ዘመን ጥር 16/2011
ኢዜአ (ባህር ዳር)