ጨረራ ወይም ራዲየሽን(radiation) የሚለው ቃል በቀላሉ ሲገለፅ አቅም ወይም ኢነርጂ ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ በሞገድ (wave) ወይም በንዑስ/ቅንጣት(Particle) መልክ ሲጓጓዝ ማለት ነው። “radiation” የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል የተለያዩ የሳይንስና የምህንድስና መስኮች ጨረራ እና ጨረር በማለት የተለያየ ትርጓሜ ይሰጡታል። ሆኖም በኀብረተሰባችን ዘንድ በተለይም በሒሳብ ትምህርት ውስጥ ከትምህርት ቤት ጀምሮ “ray” የሚለው ቃል ጨረር በሚል የተተረጎመ በመሆኑና የእንግሊዝኛውን “radiation” ከሚለው ቃል ትርጓሜው የሚለይ በመሆኑ ጨረራ የሚለውን ቃል መጠቀም ይመረጣል። ሆኖም ግን አሁንም ድረስ “alpha ray” እና “beta ray” እየተባለ በእንግሊዝኛውም ቋንቋ ቢሆን “ray” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ይውላል።
ጨረራ ወይም ራዲየሽን(radiation) የሚለው ቃል በቀላሉ ሲገለፅ አቅምን ወይም ኢነርጂን ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ በሞገድ (wave) ወይም በንኡስ/ቅንጣት(Particle) መልክ ሲጓጓዝ ማለት ነው
የጨረራ ዓይነት
የጨረራ ዓይነቶች በዋናነት በሁለት ይከፈላሉ። እነርሱም አዮን ፈጣሪ ጨረራ (Ionizing Radiation) እና አዮን የማይፈጥር ጨረራ(Non-Ionizing Radiation) ተብለው ነው።
አዮን ፈጣሪ ጨረራ (Ionizing Radiation)
አዮን ፈጣሪ ጨረራ በሰውነታችን ወይም በቁስ ውስጥ ሲያልፍ በሰውነታችን ወይም በቁሱ በሚገኘው አቶም ውስጥ የሚገኘውን ኤሌክትሮን በማስፈንጠር ወይም በማውጣት የቻርጅ ልዩነት በማኖር አዮን ይፈጥራል። ለአዮን ፈጣሪ ጨረራ (Ionizing Radiation) አለአግባብ መጋለጥ በሰዎች ጤና፣ በንብረት እና በአካባቢ ላይ ከፍ ያለ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፤ አዮን ፈጣሪ ጨረራ ባህሪዎችን በስሜት ህዋሳቶቻችን አማካኝነት ማወቅ የማንችል ሲሆን ጨረራው በአካባቢያችን መኖሩን ሳናውቅ ሁሉ ጉዳት ሊያደርስብን ይችላል:: በተለይ በጨረራ አመንጪ ቁሶች(Radiation Sources) የተበከሉ የምግብና የፍጆታ ዕቃዎች ወደ ኀብረተሰቡ ከተሰራጩ ጉዳቱ አስከፊ እንደሚሆን የተረጋገጠ ሲሆን ሁኔታውን ለመቆጣጠር ያመች ዘንድ ወሰን የወጣለት ነው።
በሰውነታችን ወይም በቁስ ውስጥ ሲያልፍ በሰውነታችን ወይም በቁሱ በሚገኘው አቶም ውስጥ የሚገኘውን ኤሌክትሮን በማስፈንጠር ወይም በማውጣት የቻርጅ ልዩነት በማኖር አዮን ይፈጥራል።
አዮን ፈጣሪ ያልሆኑ የጨረራ ዓይነቶች (Non- Ionizing Radiation)
እነዚህ የጨረራ ዓይነቶች በሰውነታችን ውስጥ በሚያልፉበት ወቅት አዮን የመፍጠር አቅም የሌላቸው ሲሆን በተጋለጠው የሰውነታችን ህብረህዋስ(Tissue) ክፍል ላይ ግን ሙቀት እና መጠነኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ጅረት እንዲፈጠር ያደርጋሉ። የሚፈጥሩት የሙቀት መጠን ከፍተኛ ከሆነ የሰውነታችንን ህዋስ(cell) የመግደል አቅም ያላቸው ሲሆን በዚህም ምክንያት ሞት ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ። እነዚህ ጥናቶች በአብዛኛው ያተኮሩትና ያገኟቸው ውጤቶች በሙቀቱ አማካይነት እና በሚፈጠረው መጠነኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ጅረት የሚመጣውን የጤና እክል በማየት ነው። ይህም የጤና ችግር ከሰው ሰው የሚለያይ ነው። በተጨማሪም ይህ የጨረራ ዓይነት ካንሰር ሊፈጥር ይችላል ወይስ አይችልም በሚለው ላይ የተለያዩ ጥናቶች በተለያዩ ተመራማሪዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ከዓለም አቀፍ የአዮን ፈጣሪ ያልሆኑ የጨረራ መከላከያ ኮሚሽን (International Commission on Non-Ionizing Radiation Protection – ICNIRP) የሚወጡ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ። ይህ ኮሚሽን ለዚህ የጨረራ ዓይነት ቁጥጥር እንዲያመች ዓለም አቀፍ ወሰን ያወጣ ሲሆን በብዙ አገራት ዘንድ ተቀባይነትን በማግኘት ተፈፃሚ እየሆነ ይገኛል። እነዚህን አዮን ፈጣሪ ያልሆኑ የጨረራ ዓይነቶች (Non- Ionizing Radiation) በተለይም ካንሰር ያመጣሉ ወይም አያመጡም የሚሉት ጥናቶች ተረጋግጠው ተገቢው ውሳኔ ላይ እስኪደረስ ድረስ በሳይንሱ ዓለም እንደተለመደው ተገቢ የጥንቃቄ መንገድ (Precautionary Approach) እንድንከተል ሁሉም ወገኖች ያስገነዝባሉ።
አዮን ፈጣሪ ያልሆኑ የጨረራ ዓይነቶች (Non-Ionizing Radiation) ከሚባሉት ውስጥ እንደ የራዲዮ ሞገድ /Radio wave/፣ ማይክሮ ዌቭ /Microwave/፣ ታህታይ ቀይ ጨረራ /Infrared/፣ ብርሃን /Visible Light/፣ ላዕላይ ወይነጠጅ ጨረራ/Ultra Violet/፣ የሌዘር ጨረራ /laser/ የሚጠቀሱ ሲሆን እነኝህ የጨረራ ዓይነቶች በሕክምናው፣ በኢንዱስትሪ፣ በሞባይል ቴሌኮሙኒኬሽን ሥርዓት፣ በራዲዮና ቴሌቪዥን ሥርጭት፣ የራዳር ሥርዓት፣ ብሎም በመዝናኛ ቤቶችና ሲዲና ዲቪዲ ማጫወቻዎች ጨምሮ በስፋት የሚገኙ ናቸው።
የጨረራ ምንጮች
የጨረራ ምንጮች በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ መልክ የሚገኙ ናቸው። በሰውነታችን ውስጥ የካልስየም ራዲዮኑክላይድ በተወሰነ መጠን ይገኛል፣ በሁሉም አፈር
ውስጥ መጠኑ ይለያይ እንጂ ጨረራ አመንጪ ፖታስየም ይገኛል፤ እንዲሁም በሙዝ፣ ቡና፣ ወዘተ ውስጥ የተለያዩ ራዲዮኑክላይዶች ይገኛሉ። ከከዋክብትና ከጋላክሲዎችም የተለያዩ የጨረራ ዓይነቶች ማለትም የኮስሚክ ጨረራዎች ወደምድር በመምጣት በተወሰነ ደረጃ የጨረራ መጋለጥ በሰው ልጅ ላይ ይፈጥራሉ። እንደምንገኝበት ቦታ መልከአ ምድር ሁኔታም በተለይ ከዩራንየምና ቶርየም ራዲዮኖክላይዶች (primordial sources) እና ከእነሱ በመፈራረስ(decay) ሂደት ተፈጥረው በምድር ላይ ለሚገኙ በርካታ የጨረራ ምንጮች ልንጋለጥ እንችላለን። ከነዚህ በተፈጥሮ ከሚገኙ የጨረራ ምንጮች(Background Radiation) የሰው ልጅ ለጨረራ ይጋለጣል:: ምንም እንኳን ይህ የተፈጥሮ የመጋለጥ ሁኔታ ከቦታ ቦታ የሚለያይ ቢሆንም በዓለም ላይ አንድ ሰው በአማካይ ለ2.4 mSv በዓመት ይጋለጣል። ይህም በተለምዶ በደረት አካባቢ የሚታዘዝ አንድ ራጅ (chest radiography) ስንነሳ የሚኖረው የጨረራ መጋለጥ ስድስት እጥፍ ይሆናል።
በሰው ሰራሽ መልክ የሚዘጋጁ የጨረራ አመንጪዎች ደግሞ ማለትም የታሸጉና ያልታሸጉ የሬዲዮአክቲቭ ቁሶች(Sealed and Unsealed Radioactive Sources) በትላልቅ አፋጣኞች(Accelerators) እና በኒዩክለር ማብለያዎች(Nuclear Reactor) የከፍተኛ የኒዩትሮን ምንጮችን በመጠቀም መፈብረክ የሚቻል ሲሆን፣ የተለያዩ የኤክስሬይ መሳሪያዎችም (X-rays) በፋብሪካ ይመረታሉ። በሕክምና መስክ የሚገኙ
የኤክስሬይ መሳሪያዎች (X-ray) በተለምዶ ራጅ ተብለው የሚታወቁ ሲሆን በአጠቃላይ መደበኛ ራጅ(Conventional X-ray)፣ የጥርስ ራጅ(Dental Radiography)፣ ሲቲ ስ ካ ን (C T- S c a n ) ፣ የ ማ ሞ ግ ራ ፊ ( M a m m o g ra p hy ) ፣ ፍ ሎ ሮ ስ ኮ ፒ ( F l u o r o s c o p y ) ፣ ኢ ን ተ ር ቬ ን ሽ ና ል ራዲዮሎጂ(Interventional Radiology) ወዘተ… ይባላሉ:: የኤክስሬይ መሳሪያዎች በሌሎች ዘርፎችም ለምሳሌ በኢንዱስትሪው የብረታ ብረት ምርቶች ጥራት ቁጥጥር ይውላሉ፤ ይህውም ከፍተኛ ግፊት(pressure) የሚያርፍባቸውን የአውሮፕላን አካላትና ሌሎች የብረት ምርቶችን ጥራት ለመቆጣጠር(Industrial radiography) ሥራ ይውላሉ:: እንዲሁም በበርካታ አየር መንገዶች፣ ሆቴሎችና ሌሎች ሕንፃዎች ላይ ለጥበቃ አገልግሎት ማለትም ዕቃዎችን ለመፈተሽ ግልጋሎት ይሰጣሉ:: በተጨማሪም በሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች፣ የትምህርትና ምርምር ተቋማት፣ የምርቶችን ጥራትና የናሙናዎችን ተፈጥሯዊ የውስጥ ቅርፅ(internal structure ) ለመለካት፣ በወደቦችና የጉምሩክ ኬላዎች የሚገኙ የከፍተኛ የካርጎ እንቅስቃሴዎች ላይ ለቁጥጥር አገልግሎት በመዋል በተግባር ላይ ይገኛሉ። ይህም የኤክስሬይ መሳሪያዎች በሕክምናው ላይ በተለምዶ ራጅ ብለን ለምንጠራው ተግባር ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ውስጥ የሚገኙ መሆኑን ያሳያል::
አዲስ ዘመን ሰኔ 20/2012