የአባይ ወንዝ ከተለያዩ የሀገራችን ወንዞች ተጠራቅሞ አንድ ወንዝ የሆነ ታላቅ ወንዝ ነው። የአባይ ወንዝ በሁለት ይከፈላል። ከኢትዮጵያ የሚነሳውና ለም የሆነ መሬት እና የተለያዩ ንጥረ-ነገሮችን የሚሰበስበው 86% የሚሸፍነው አካል ጥቁር አባይ ይባላል። ከቪክቶሪያ ሐይቅ የሚነሳውና ብዙ በውስጡ ጠቃሚ ነገሮች የማይዘው 15% የሚሸፍነው ደግሞ ነጭ አባይ ይባላል። ይህ ወንዝ ለም የሆነ መሬትና የተለያዩ ንጥረ-ነገሮችን ከኢትዮጵያ ሰብስቦ በደቡብ ሱዳን አድርጎ ወደ ግብፅ ሲደርስ የናይል ወንዝ ይባላል።
የአባይ ወንዝ ትልቅ የኢኮኖሚ ፋይዳ ለወንዙ ተፋሰስ ሀገራት አለው። በተለይ የአባይ ወንዝ ለግብፅ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ስለሚያደርግ ግብፅ ከፍተኛ ትኩረት ትሰጥበታለች። ወንዙን መሠረት ያደረገ ትላልቅ ፋብሪካዎች፣ የግብርና ሥራዎች እና መዝናኛ ሆቴሎች መሥራቷንና እየሠራች መሆኗ ይታወቃል። ለእነዚህ ልማታዊ ፕሮጀክቶች ብዙ ገንዘብ በጅታለች። ይህ ደግሞ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት እደርስበታለሁ ብላ ካቀደችው የኢኮኖሚ ደረጃ ትልቅ ፋይዳ አለው።
የዓለም ሀገራት የኢኮኖሚ ዕድገት ሲተነተን ከስነ- ህዝብ ጋር ተያያዥነት አለው። የምዕራብ አውሮፓ ሀገራት የኢንዱስትሪ አብዮት የስነ-ህዝብ ዑደት ክፍልፋይን መሠረት ያደረገ ነው። በወቅቱ የነበሩ የምጣኔ ሀብት ምሁራን ፈጣን የህዝብ ዕድገት ለኢኮኖሚ ዕድገት ጠንቅ ነው በሚል ተንብየው ነበር። በዚህም የህዝብ ዕድገት ምክንያት የሆኑትን ከፍተኛ የውልደት ምጣኔ እና ከፍተኛ የሞት ምጣኔ ወደ ዝቅተኛ የውልደት ምጣኔ እና ዝቅተኛ የሞት ምጣኔ በመለወጥ የስነ-ህዝብ ዑደት ክፍልፋይ በማምጣት የሚገኘውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች አትርፈዋል። የምሥራቅ ኢሲያ ሀገራትም ምዕራባዊያን የፈጀባቸውን የ200 ዓመታት የስነ-ህዝብ ዑደት ክፍልፋይ ተሞክሮ በመውሰድ በ50 ዓመታት እና አራት እጥፍ ባነሰ ጊዜ የስነ-ህዝብ ዑደት ክፍልፋይ በማምጣት የሚገኘውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች አትርፈዋል።
እንደ ግብፅ ያሉ ብዙ የዓረብ ሀገራት ፈጣን የሚባል የህዝብ ዕድገት አላቸው። ከፍተኛ የውልደት ምጣኔ ሲኖራቸው ዝቅተኛ የሞት ምጣኔ አላቸው። ይህ በከፍተኛ ሁኔታ የህዝብ ብዛት እንዲጨምር ያደርጋል። ከፍተኛ የህዝብ
ብዛት መኖሩ ደግሞ የተፈጥሮ ሀብትን በብዛት የሚጠቀም ህዝብ እንዲኖር ያደርጋል። ይህም ቀድሞውንም የተፈጥሮ ሀብት መጠቀምን መሠረት ያደረገው ኢኮኖሚያቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ባለው ህዝባቸው የተፈጥሮ ሀብት ዕጥረት ችግር ሊፈጥርባቸው እንደሚችል ይገመታል።
የዓረብ ሀገራት ኢኮኖሚ የተፈጥሮ ሀብትን አብዝቶ ከመጠቀም ጋር ይያያዛል። እነዚህ ሀገራት ነዳጅና ወርቅ የመሠሉ የተፈጥሮ ሀብቶችን በሰፊው አሟጠው ይጠቀማሉ። ግብፅ፣ ሳውዲ፣ ኳታር፣ ሊቢያ እና ሌሎች ሀገራት ነዳጅን መሠረት ያደረጉ ናቸው። የተፈጥሮ ሀብት መመናመን ሲፈጠር ኢኮኖሚያቸው ከፍተኛ ጉዳት ሊገጥመው እንደሚችል ይጠበቃል።
የዓረብ ሀገራት በቴክኖሎጂ ባለማደጋቸው የነዳጅ ሀብትን አድምቶ መጠቀም መሠረት ያደረገ ነው። ይህ ደግሞ ሸማች ሀገራት ከነዳጅ ኃይል ወደ ታዳሽ ኃይል (ንፋስ፣ ውሃ፣ የፀሐይ ብርሃን፣ ከሠል) የኃይል ማመንጫዎች ከተለወጡ ነዳጅ ጥገኛ ኢኮኖሚ ያላቸው የዓረብ ሀገራት በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳሉ።
በመካከለኛው ኢስያና በሰሜን አፍሪካ የሚገኙት የዓረብ ሀገራት የተፈጥሮ ሀብት ማዕድናትን ከከርሰ-ምድር በመቆፈር፣ በማውጣትና በማጣራት ለዓለም-አቀፍ ገበያዎች በማቅረብና በመሸጥ የሚተዳደሩ ናቸው። የእነዚህ ሀገራት ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ አለመሸጋገር የተፈጥሮ ሀብት ቀጥተኛ ጥገኛ አደርጓቸዋል።
የአባይ ወንዝ ወደ የውሃ ኃይል ማመንጫ መቀየሩ ለብዙ ሀገራት በጊዜ ሂደት ከፍተኛ አደጋ ይኖረዋል። ነዳጅን መሠረት ያደረገ ኃይል ማመንጫ ወደ ወሃ ኃይል ማመንጫ መለወጡ የነዳጅ ፍላጎትን በምሥራቅ አፍሪካ ይቀንሰዋል። ይህ ደግሞ ነዳጅ በመሸጥ የሚተዳደሩ የዓረብ ሀገራት ከነዳጅ ብዙ ገንዘብ አግኝተው ኢኮኖሚያቸውን ያቆሙ በመሆናቸው ቀላል የማይባል ጉዳት ይደርስባቸዋል። ይህ ሁኔታ የዓረብ ሀገራት ከግብፅ ጎን እንዲቆሙ አስተዋፅዖ ያደርጋል።
ግብፅ የዓረብ ሀገራት ተሰባስበው በጋራ በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚሠሩበት ማህበር ማለትም የዓረብ ሊግ መቀመጫ ናት። ግብፅ የሊጉ መቀመጫ በመሆኗ ባላት ተደማጭነት አጋር የዓረብ ሀገራት በአባይ ግድብ ላይ ያላቸውን አቋም ለግብፅ እንዲያጋሩ ታደርጋለች።
የአባይ ግድብ ለግብፅ ፖለቲካ ትልቅ ፋይዳ አለው። በወታደራዊ አገዛዝ የምትመራው ግብፅ ወደ ዴሞክራሲያዊ
ሥርዓት ለመመለስ ብዙ ሥራዎችን መሥራት አለባት። ሥልጣን ላይ ያለው ወታደራዊ መንግሥት ህዝቡ እንዳይሞግተው ከአባይ ግድብ ጋር የተያያዙ እና ህዝቡን ሥጋት ውስጥ የሚከቱ ፕሮፖጋንዳዎችን መንዛት አጀንዳ እያስቀየሩ የሥልጣን ዘመን ማራዘሚያ መሣሪያ ሆኗል።
የአባይ ወንዝ ላይ እየተነሳ ያለው ግብግብ ከስነ-ህዝብ ጋርም ተያያዥነት አለው። ሁለቱ ሀገራት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ያለው ህዝባቸውን መመገብ የሚያስችል ኢኮኖሚ መገንባት ይኖርባቸዋል። ለዚህም ያላቸውን የተፈጥሮ ሀብቶች አሟጦ በመጠቀም ወደ እንዱስትሪ መሸጋገር አለባቸው። ይህም ሁኔታ የአባይ ወንዝ ላይ ሙጭጭ እንዲሉ ያደርጋቸዋል።
የግብፅና የኢትዮጵያ ጉዳይ ከእንግሊዝና ከህንድ የንግድ ተሞክሮ ጋር ይያያዛል። እንግሊዝ ሰፋፊ የጥጥ የእርሻ ማሣዎች በህንድ ውስጥ አላት። እንግሊዝ በህንድ በሚገኙት የጥጥ ማምረቻ ማሣዎቿ በህንድ ያለውን አነስተኛ የጉልባት ዋጋ ከፍያ ተጠቅማ ጥጥ ታመርታለች። የሚመረተው የጥጥ ምርት ወደ እንግሊዝ ይመጣና አልባሳት ተሠርቶበት ተመልሶ በህንድ ገበያዎች ለሽያጭ ይቀርባል። በዚህም በህንዶች መሬት፣ ጉልበት እና ገበያ እንግሊዝ በጨበጣ ከፍተኛ ገንዘብ ታገኛለች። ኢትዮጵያም በተመሳሳዩ በገዛ ወንዟ እና ከወንዟ ጋር ተያይዞ ከሚወሰደው ለም መሬትና ንጥረ-ነገሮች ግብፅ ተጠቃሚ ሆና ቆይታለች።
እንግዲህ ከላይ ለማብራራት እንደሞከርኩት የአባይ ግድብ ለግብፅ እና ለሌሎች የዓረብ ሀገራት ከፍተኛ የሆነ የአጭር-ጊዜና የረጅም-ጊዜ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ ይገባሉ። በተለይ ከነዳጅ ጋር በዋናነት ተያያዥነት ያለው ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገራት የአባይ ወንዝ በሚያመጣው የውሃ የታዳሽ ኃይል ምንጭ የነዳጅ ፍላጎት ይቀንሳል። በዚህም ተጎጂ ይሆናሉ። በዚህም የዓረብ ሀገራት ስጋት ውስጥ ገብተዋል። ግብፅም በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች። ስለዚህ ሀገራችን ኢትዮጵያ የእነዚህን ሀገራት ድብቅ ስጋት በመረዳት የአባይ ግድብ ዲፕሎማሲን የሚያራምደው ቡድን ውስጥ የተፈጥሮ ሀብት እና የስነ-ህዝብ ባለሙያዎችን አካታ ጉዳዩን ማብላላት አለባት። አበቃሁ!
አዲስ ዘመን ሰኔ 13/2012
በላይ አበራ ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ለሁሉም ጠቃሚ የሆነው የህዳሴ ግድብ