
ሂያጅ፤
በየቦታው ወራጅ።
በፍቅር ያልተገራ፤
ታጥቦ የማይጠራ፤
አድሮ ጥሬ አድሮ ቃሪያ።
ብስለት የለ፤
እውቀት የለ፤
እምነት የለ፤
ባሕል የለ፤
ወግ ክብራችን ገደል ገባ
በፆም በላን ሥጋ።
ልጓሙ ተፈታ ፆማችን ፈረሰ
እምነት ተበረዘ
እውቀት ደበዘዘ
ባሕል ፈር ለቀቀ
ተንቃቃ ደረቀ።
ሥልጣኔን መረጥን ስይጣኔ ገባን
ልጅ ባባት ሲደፈር ከእንስሳ ተጋባን።
እንደ አሸዋ በዛን ዘራችን ቀጠለ
መዳራት ከክብር ተቆጠረ።
በደመነፍስ ተጓዝን
ለሰይጣን ቃል ገባን፤
ከርኩስ ተወዳጅተን ለጋኔል ሰገድን
ገላችንን አርክሰን ክብራችንን ሸጥን።
ንፁህ አዲስ
2015 ዓ.ም
አዲስ ዘመን ዓርብ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም