በተለያዩ ወቅቶች ተሞክሮ የመከነው የለውጥ ትግል (አስተሳሰብ) በአዲስቷ የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ዕለት ተዕለት አቅም እየጨመረ ፤ መሰረቱን እያጠነከረ፣ በዝምታ ረጅሙን መንገድ እየተጓዘ ነው ።መንገዱ ረጅም ብቻ ሳይሆን ወጣ ገባ ያለበት፣ ተራራና ኮረብታ የበዛበት መሆኑ በራሱ የጥንካሬና የብርታት ምንጭ እየሆነም ይገኛል ።
የለውጥ ጉዞ ከመለወጥና ከመታደስ የሚመነጭ የጉዞ ሂደት ነው፡፡ ተለውጦ ባለቀ ማንነት ተጀምሮ የሚያበቃ ሳይሆን በጉዞ ሂደት ውስጥ በተለወጡ ማንነቶች ለውጡን እያስቀጠሉ የሚጓዙበት የማህበረሰብ አንድ የታሪክ ምዕራፍ ነው። ውጤታማ መሆን የሚቻለውም በለውጥ ውስጥ መሆንን በማመን ከሂደቶች ያለማቋረጥ የመማር ፈቃደኝነት ሲኖር ብቻ ነው። በቅቻለሁ ከሚል አደጋና አደጋው ከሚፈጥረው መፋነን ራስን መጠበቅ ሲቻልም ጭምር ነው።
የለውጥ አስተሳሰብ ከቀደሙና ካረጁ አስተሳሰቦች ጋር ያለን ቁርኝት በአዲስ የአስተሳሰብ ልህቀት ሙሉ በሙሉ ማቋረጥን የሚጠይቅ ፤ለዚህ የሚሆን መረዳትና ከመረዳት የሚመነጭ ድፍረትን የሚፈልግ ነው። ሁልጊዜ ከትናንት ለተሻሉ አዳዲስ አስተሳሰቦች (እውቀቶች) ራስን ብቁ አድርጎ ማዘጋጀትን የሚጠይቅ ነው። ያረጁ የትናንት ድምጾችን ከጣራ በላይ ማስጮህ ወይም ትናንቶችን አዲስ የሆኑ ያህል ዛሬ ላይ በአዲስ ዜማ ማዜም አይደለም።
ዛሬ በሁለንተናው አዲስ ቀን ነው። ከትናንት ጋር የሚያስተሳስረው ደግሞ በራሱ ብቻውን የቆመ አለመሆኑ ነው። ከዚህ እውነታ በመነሳት በሀገሪቱ የነበሩ የተለያዩ ትውልዶች በየ ዘመኑ ዘመናቸውን የሚመጥን የለውጥ አስተሳሰቦችን አምጠው ለመውለድ ብዙ ቃትተዋል ፤ ሳይሳካላቸው ቀርቶም ብዙዎች ህይወታቸውን ገብረው አልፈዋል ።
ከ50 ዎቹ በኋላ የነበሩ የትውልዶች የለውጥ መሻቶችን ፤ ስለመሻቶቹ የተከፈሉ ዋጋዎች ብንመለከት እንኳን እነዚህ የትውልዶች የለውጥ መሻቶች የለውጥ ሁለንተናዊ እውነታ ባልገባቸው የትናንት ባሪያ በሆኑና ስለነጻነት እየደሰኮሩ የታሰሩበትን የትናንት ሰንሰለት ለማየት ባልታደሉ፤ በግርግር ወደስልጣን በሚመጡ ቡድኖች ስግብግብነት ትርጉም ያለው ወጤት ማምጣት ሳይችሉ መክነዋል።
እንደ ሀገር ብዙ ዋጋ ካስከፈሉን የተደጋገሙ ትናንቶች መማር ፤ በተማረ ማንነት ትናንቶችን መሻገር ባለመቻላችን ዛሬም ነገዎቻችን በሚያረክሱ ፤ ነገዎቻችን ተስፋ አልባ በሚያደርጉ ትናንቶች ውስጥ እንገኛለን። ዛሬን እየናፈቅን ዛሬን ግን በተጨባጭ እያጣን ዘመናትን በቁጭት እየቆጠርን እንጓዛለን ። የፖለቲካ ህይወታችንና የፖለቲከኞቻችን ህይወት በዚህ አዙሪት የተቃኘ መሆኑ ደግሞ ሁኔታችንን የከፋ ያደርገዋል ።
ከዓለም ታሪክ እንደምንረዳውና በተጨባጭም እንደሆነው ማህበረሰባቸውን ከአንድ የታሪክ ምእራፍ ወደ ሌላ ከፍታ የታሪክ ምእራፍ ማሻገር የቻሉ ፖለቲከኞች ትልቁ ብቃታቸው ቀድመው ትናንትን መሻገር መቻላቸው እና በዛሬ መንፈስ ህዝባቸውን ወደ ነገ ለማሻገር የነበራቸው ብቃት ነው። ከትናንት ባርነት ነጻ ወጥተው ህዝባቸውንም ነጻ ማውጣት መቻላቸው ነው ።
የኛ ሀገር ፖለቲከኞ ግን በዘመናት መካከል ሁሌም ከትናንት መውጣት ሳይችሉ ፣ ትናንት ላይ ሆነው በየዘመኑ የተነሱ የለውጥ አስተሳሰቦችን ሲያመክኑ ዘመናት አስቆጥረዋል። ዛሬም በ21ኛው ክፍለ ዘመን ህዝብን ከማሻገር ይልቅ በዘመነ መሳፍንት እንደነበረው የማዕከላዊ መንግሥትን ስልጣንን ለመያዝ መላውን ህዝብ ዋጋ ሊያስከፍል በሚችል በከፋ ሁኔታ ሲንቀሳቀሱ ም እየታየ ነው።
ፖለቲከኞቻችን በዘመነ መሳፍንት በነበረው የመንግሥት የስልጣን አተያይና በ21ኛው ክፍለ ዘመን ባለው የመንግሥት ስልጣን አተያይ መካከል ያለውን ልዩነት በአግባቡ መገንዘብ የቻሉ አይመስልም ። ዛሬም ስልጣን የሁሉ ነገር ምንጪ አድርገው ከማየት ገና አልወጡም። ስልጣን አልፋና ኦሜጋ ነው ብለው ከማመን አልተመለሱም። የስልጣን መሻታቸው ከዚህ ያለፈ አይደለም። ዛሬ ላይ በአካል ይኑሩ እንጂ የተገዙበት መንፈስ ብዙ ዘመን የኋላ ታሪክ ያለው ነው።
የሚያሳዝነው እነዚህ ፖለቲከኞቻችን በአግባቡ ከትናንት ሳይወጡ ፤ ዛሬም የትናንትን ጩኀት እየጮሁ ዛሬአችን ለማርከስ ሌት ተቀን ያለ መታከትና ያለ እረፍት የሚተጉ መሆናቸው ነው። እነዚህ በየዘመኑ የህዝባችንን ዛሬዎች እየተናጠቁ ህዝባችን ዛሬ ላይ ሊኖር የተገባውን እና የሚመጥነውን ኖሮ እንዳይኖር ከዚህ ይልቅ ዛሬዎቹን እያመከኑ የነገዎች ተስፈኛ እንዲሆኑ አድርገውታል። በተስፈኝነት ህይወትም ብዙ ዛሬዎቹን ተናጥቀውታል ። የህይወት መስዋእትነት ከፍሎ እንኳን ዛሬዎቹን እንዲኖር አላስቻሉትም።
ዛሬም በለውጡ ማግስት ሥራቸው አስደንብሯቸው ተሰባስበው መቀሌ የከተሙት በትግራይ ህዝብ ደም አዲስ አበባ ገብተው በባለተረኝነት መንፈስ ብዙ ዋጋ የተከፈለለትን የትግል አላማ ብቻ ሳይሆን ለትግሉ ዋጋ የከፈለውን የትግራይ ህዝብ ሳይቀር አንገት ያስደፉትን ጨምሮ በግርግር ወደ ስልጣን ለመምጣት ሌት ተቀን የሚዳክሩ ፤ ከትናንት ያልወጡ የህዝብን ዛሬ ለማርከስ የሚተጉ ብዙ ናቸው ።
የጥላቻ አስተሳሰቦችን በህዝብ ውስጥ ማስረጽን የትግል ስትራቴጂ አድርገው መውሰዳቸው ምን ያህል በቀደሙ ዘመኖች ውስጥ ቆመው እንዳሉ የሚያመላክት ነው ፤ ማህበረሰብን በጥላቻ መንፈስ ከአቅም በላይ መጋት ከዓለም ታሪክ እንደምንረዳው ለአምባገነኖች ጊዜያዊ ምሽግ እንጂ መኖሪያ ሊሆን አልቻለም፤ አይችልምም።
ጥቂቶች በክፋት የዘሩትን የሚያጭዱበት ጊዜ ሲደርስ በብዙ ብልጠትና በቀደመው ዘመን የጥፋት አስተሳሰቡ የሚከውኗቸው ተግባራት ” ከመጀመሪያው ስህተት የሁለተኛው” እንደሚባለው የአንደኛውን ጥፋት ዋጋ ሳያወራርዱ በሌላ የጥፋት ሃሳብ ጥፋትን ለማወራረድ የሚደረጉ ጥረቶች ሊያስከፍሉ የሚችሉት ዋጋ ምን ሊመስልና ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችል በኢትዮጵያዊ ስነ ልቦና መገመት የሚከብድ አይሆንም ! ለዚህም ነው ከመጀመሪያው ስህተት ሁለተኛው እንዳይብስ ማለታችን!
አዲስ ዘመን ግንቦት 26/2012
“ከመጀመሪያው ስህተት የሁለተኛው”