
አዲስ አበባ፡– ባለሀብቶች ኃይል በራሳቸው አመን ጭተው ለብሔራዊ ቋት አስተዋጽኦ የሚያደር ጉበትን ልምምድ መፍጠር እንደሚያስፈልግ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በግቢው ውስጥ የተገነ ባውን 100 ኪሎ ዋት የሚያመነጭ የሶላር ፕሮጀክት ትናንት አስመርቋል።
ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በመርሃ ግብሩ ላይ እንዳሉት፤ ፕሮጀክቱ ለተቋሙ ከሚሰጠው አገል ግሎት ባለፈ የሚመነጨው ኃይል ወደ ብሔራዊ ቋት መግባት የሚችል መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።
በአደጉ ሀገራት ግለሰቦች ኃይል አመንጭተው ለብሔራዊ ቋት አስተዋጽኦ ማድረግ የተለመደ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶችም ኃይል በራ ሳቸው አመንጭተው ለብሔራዊ ቋት አስተዋጽኦ የሚያደ ርጉበትን ልምምድ መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በመላው ኢትዮጵያ ኢነርጂ ማመንጫዎችን እየገነባ መሆኑን አስታውሰው፤ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በግቢው ውስጥም ኃይል ማመንጨቱ እውነትም የኢነርጂ ምንጭ መሆኑን የሚያመላክቱ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል። ይህ ፕሮጀክትም እንደ ሠርቶ ማሳያ ሆኖ ለሌሎች ተቋማት ልምምድ ለማስተላለፍ እንደሚያገለግልም ጠቁመዋል።
እንደ ሀገር በእዚህ ደረጃ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው የሶላር ፕሮጀክት አለመኖሩን ገልጸው፤ ይህ ፕሮጀክት 100 ኪሎ ዋት በማምረት የመጀመሪያው ያደርገዋል ብለዋል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ዓመቱን ሙሉ ፀሐይ ያለባት ሀገር መሆኗ ከፍተኛ የሶላር ኢነርጂ ማመንጨት የሚያስችል አቅም እንዲኖራት እድል ፈጥሯል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ካላት መልክዓ ምድር አንጻር ሁሉንም አካባቢ ከመደበኛ የኃይል አማራጮች ማዳረስ አዳጋች ይሆናል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ እየተተገበረ ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርምም ተጨማሪ ኃይል ማመንጨትን ይጠይቃል። በመሆኑም በየዘርፉ ያለንን እምቅ አቅም አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ አብራርተዋል።
እስካሁን ድረስ በገጠራማ አካባቢዎች እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት የሶላር ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ ሲውሉ መቆየታቸውን አመልክተው፤ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተጀመረው ፕሮጀክት ለየት የሚለው የሚመነጨው ኃይል ቀጥታ ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት መግባት የሚችል መሆኑ ነው ብለዋል።
በቀጣይነት እያንዳንዱ ተቋም በየጣሪያው ይህን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ቢያውሉ የሀገሪቱን የኃይል አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ እንደሚያስችል አመልክተዋል።
የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ በአዲስ አበባ ካሉ ቤቶች በአማካይ ሰባት ኪሎ ዋት ኃይል ለብሔራዊ ኃይል ቋት አስተዋጽኦ ቢያደርጉ ጊቤ አንድ እና ሁለት የሚያመነጩትን ያህል ኃይል መቆጠብ እንደሚቻል ጨምረው ገልጸዋል።
ባለሀብቶችና ግለሰቦች ሕንጻዎችን ሲገነቡ ይህን ታሳቢ አድርገው እንዲሠሩ ግንዛቤ መፍጠር ብሎም አስገዳጅ ሕግ አድርጎ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑንም አብራርተዋል። ፕሮጀክቱ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና በዓለም አቀፍ የሶላር ኢነርጂ አሊያንስ ትብብር የተሠራ መሆኑ ተመላክቷል።
በፋንታነሽ ክንዴ
አዲስ ዘመን ዓርብ ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም