አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬን የደረሰችው ተአምር ተፈጥሮና ባለልዩ ዕድል ሆና ሳይሆን ለዘመናት ያጋጠሟትን ተግዳሮቶችና ፈተናዎች ሁሉ በጽናት በመታገሏና ለዚሁ ሲባል ክቡር ህይወታቸውን ጭምር ሳይሳሱ የሰጡላት በርካታ እንቁ ዜጎች ባለቤት በመሆኗ ነው! ተደጋጋሚ ወረራዎች፣ እጅግ አስከፊ ድርቅና ርሃብ፣ የርስ በርስ ጦርነትና ወረርሺኝ ወዘተ በተለያዩ ጊዜያት ደጋግመው የተነሱና የአገርና የህዝብን ህልውና በእጅጉ የተገዳደሩ ፈተናዎቻችን ነበሩ።
አገራችን በፈተና በወደቀችባቸው ጊዜያት ካጋጠማት ፈተና በባሰ ጋሬጣ የሆኑባት የእናት ጡት ነካሾች ተነስተውም ፈተናዋን አብዝተውባታል። ከብዙ በጥቂቱ እንኳን በጣሊያን ወረራ ወቅት ባርነትን እምቢ ብሎ ፋሽስቶችን በየዱሩ የታገለውን የአገራችን አርበኛ ከወራሪዎቹ በላይ የተዋጉትና ያደሙት ከአገራችን ማህጸን የፈለቁ እኩይ ባንዳዎች እንደነበሩ የታሪክ ድርሳናት ይመሰክራሉ። ጥቂት ባኮረፉ ቁጥርም አገርንና ገዥን መለየት አቅቷቸው ለባዕዳን ጥቅም ሲሉ አገራቸውን አሳልፈው የሰጡ ብዙ ባንዳዎች እነደነበሩም ጸሀይ የሞቀው ሀቅ ነው። መልካሙ ነገር የባዳንዎቹንና የከሃዲዎቹን እልፍ ዕጥፍ የሆኑ አገር ወዳድ ዜጎች አሉንና እንደነሱ ዕቅድና ሴራ ሳይሆን አገራችን ክብሯንና ሉኣላዊነቷን አስጠብቃ አሁንም እንዳንጸባረቀች አለች።
አገር መውደድ የሚለው ክቡር ቃል ትርጉም ከምንም ነገር በፊት አገርንና ህዝብን መውደድና በችግሯ ጊዜ ሁለንተናን አሳፎ መስጠት የሚል ትርጉም አለው። አገር መውደድ ለአገርና ለህዝብ ሲባል ክቡር የሆነውን ህይወት እንኳን አሳልፎ መስጠትንም ይጠይቃል። አገር መውደድ ክቡር ነገር ነውና ሊከፈልለት የሚገባ ክቡር ዋጋ አለ። አገር መውደድ በቃላት ጋጋታና በዜማ ብቻ የሚቀነቀን ተራ ነገር ሳይሆን በተለይም በችግር ጊዜ የሚታይ መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ክቡር ተግባር ነው።
ከዚህ አንጻር ለአገራችን ለኢትዮጵያ የችግር ጊዜ የደረሱና ለአገርና ለወገኖቻቸው ሲሉ ክቡር መስዋዕትነትን የከፈሉ እልፍ ዜጎች ከአገራችን ማህጸን በቅለዋል፤ አሁንም በመብቀል ላይ ናቸው። በክቡር የህይወትና የአካል መስዋዕትነት የጣሊያን፣ የግብጽ፣ የሶማሌ፣ የኤርትራና ሌሎች ወረራዎችን ቀልብሰውና ወራሪዎችን አሳፍረው የመለሱ አውነተኛ ኢትዮጵያውያን ለዚህ ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው። ከዚህም ባሻገር በተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ወቅት የህዝብ ህይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ራሳቸውን ሻማ አድርገው በማቅለጥ አገርና ህዝብን የታደጉ ወርቃማ ዜጎች በደማቅ ቀለም የተጻፈና ለዘላለም የማይደበዝዝ አሻራቸውን ጥለው አልፈዋል። የባንዳዎችና የከሃዲዎች ከንቱ ቅዠትና ሙከራ ህልም ሆኖ አገራችን የነጻነት ቀንዲል ሆና እያንጻባረቀች ዘመናትን የተሻገረችውም በእኒህ መሰል ወድ ኢትዮጵያውያን ክቡር መስዋዕትነት መሆኑ መቼም አይዘነጋም።
አገራችን ማህጸነ ለምለም ነችና ለዘመናት የሚያጋጥሟትን ተግዳሮቶች በመስዋዕትነት የሚያሻግሩ ጀግኖች አርበኞችን አሁንም ማፍሯቷን ቀጥላለች። ዓለም አቀፍ ችግር የሆነውና በአገራችንና በህዝቦቿ ህልውና ላይ አደጋ የደቀነውን የኮሮና ወረርሺኝ ለመከላከል ህይወታቸውን ቀብድ አስይዘው ታላቅ ርብርብ እያደረጉ ያሉ የህክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት የሚሰሩ ሠራተኞች ለዚህ ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው። እኒህ የዘመኑ አርበኞች የበሽታው አደገኛ የመተላለፍ ባህሪና የቤተሰብ ናፍቆት ሳይበግራቸው ህሙማንን በመንከባከብና ሌሎች ዜጎች በዚሁ ጦስ እንዳይጎዱ ለማድረግ ለ24 ሠዓታት ያለማቋረጥ ትግል እያካሄዱ ይገኛሉ። የወገንን ህይወት ለመታደግ እየተደረገ ላለው ለዚህ በገንዘብ የማይታመን መስዋዕትነት ከአውነተኛ ኢትዮጵያውያን የሚጠበቅ የአርበኝነት ተግባር ነውና ከአንገታችን ዝቅ ብለን ምስጋና ልናቀርብላቸው ይገባል።
ለአገር ጥቅምና ኢፍትሃዊነትን ለመታገል ሲል መሃመድ አልአሩሲ የተባለው ኢትጵያዊ ከሰሞኑ እያደረገው ያለው የአገር መውደድ ተግባርም የእውነተኛ አርበኝነት መገለጫ። መሃመድ አልአሩሲ ግብጽ እውነታን ጭፍን አድርጋ በመካድ የኢትዮጵያን ገጽታ ለማጠልሸትና የስግብግብነት ምኞቷን ለማሳካት የምታደርገውን የውሸት ፕሮፖጋንዳ እግር በእግር እየተከታተለ በማጋለጥ ለአገሩ ያለውን ተቆርቋሪነትና ሃላፊነት በሚገባ በመወጣት ላይ ይገኛል። ይህ የመሃመድ አልአሩሲ ተግባር ሁሉም ኢትጵያዊ ለአገሩ አምባሳደርና ጠበቃ ነው የሚለውንም አባባል በተግባር ያሳየ ተምሳሌታዊ ተግባር ነውና ታላቅ ምስጋና ሊቸረው ይገባል።
በአጠቃላይ አገር ችግር ውስጥ በገባችበት ወቅት ይህን ተገንዝቦ ለአገርናና ለወገን መቆምና ተፈላገውን መስዋዕትነት መክፈል እውነተኛ የአርበኝነት ተግባር ነውና በዚህ አኩሪ ተግባር ላይ ለተሳተፉ አካላትና ግለሰቦች ሁሉ ታላቅ ክብር ሊቸራቸው ይገባል!
አዲስ ዘመን ግንቦት 13/2012
ለኢትዮጵያ በችግሯ ጊዜ የደረሱና የቆሙ ሁሉ አርበኞቻችን ናቸው!