ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ ዘጠኝ ዓመታትን አስቆጥሯል። የግድቡ ግንባታ የተጀመረው በኢትዮጵያውያን ሀብት፣ ጉልበት እና ቁርጠኝነት ነው። የሚጠናቀቀውም በተመሳሳይ መልኩ ነው። ከደሀ እስከ ሀብታም፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከህጻን እስከ አዋቂ እያንዳንዱ ዜጋ ያለውን በማዋጣት እና ግንባታው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የማያቋርጥ ድጋፉን እየገለጸ ግድቡን አሁን ላለበት ደረጃ አድርሷል።
እያንዳንዱ ዜጋ ለግንባታው የተረባረበው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በመረዳት ነው። አሁን ድረስ በሀገራችን ከ60 ሚሊየን በላይ ህዝብ የኤሌክትሪክ ብርሃን ተጠቃሚ አይደለም። ዛሬም በጭለማ ውስጥ የሚኖር እና የኢኮኖሚው አቅሙም ዝቅተኛ ነው። በመሆኑም በተፈጥሮ ሀብት የመልማት መብቱን ለማረጋገጥ ነው ያለውን ብቻ ሳይሆን ከጎዶሎው እያዋጣ መጠናቀቁን በጉጉት የሚጠብቀው። የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሲቪል ምህንድስና ስራ 87 በመቶ አጠቃላይ የግንባታ ሂደቱ 73 በመቶ ደርሷል። ቀሪውን 27 በመቶ ለማጠናቀቅም የሁሉም ርብርብ ቀጥሏል።
ኢትዮጵያ በአባይ ላይ የመልማት ፍላጎት ቢኖራትም ይሄ ፍላጎቷ ለብቻ የሚል ግን አይደለም። ከተፋሰሱ በታችም ሆነ በላይ ያሉትን ሀገራት ታሳቢ ባደረገ እና አብሮ መልማት በሚል መርህ ላይ የተመሰረተ ነው። ኢትዮጵያ ከ1902 ዓ.ም ጀምሮ የዓባይ ወንዝ ፍትሃዊ፣ ምክንያታዊና ጉልህ ጉዳት በማያደርስ መርህ እንዲሁም ባለፉት አስር ዓመታት ወንዙ በፍትሃዊነት ጥቅም ላይ እንዲውል ሰርታለች። የናይል ተፋሰስ ኢንሼቲቭ እንዲቋቋም ለ13 ዓመታት በግንባር ቀደምትነት ሞግታለች። የተፋሰሱ አገራት ላይ ጉልህ ጉዳት በማያደርስና
በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ ለሌሎች አገራት ምሳሌ ሆናለች። ግድቡ በመገንባቱ ምክንያት የታችኛው ተፋሰስ አገራት ተጠቃሚ ይሆናሉ እንጂ እንደማይጎዱም አረጋግጣለች። እንዳውም ተደማሪ ኃይል ያገኛሉ። ኃይል በማግኘታቸው ደግሞ ተጨማሪ ምርት ማምረት የሚችሉበት ሁኔታ ይፈጠራል። ይሄም የኢኮኖሚ አቅማቸውን ያሳድገዋል።ይሁን እንጂ ግብጽ ከ80 በመቶ በላይ ውሀ የምታመነጨውን ሀገር የመልማት መብት በመጋፋትና ኢፍትሃዊ አቋም እያራመደች በተለያየ ጊዜ አጀንዳዎችን እየቀያየረች ቅሬታና ተቃውሞ ስታቀርብ ከርማለች።
ከግድቡ ግንባታ መጀመር አንስቶም ባለፉት ስምንት ዓመታት ኢትዮጵያ ግድቡን እንዳትሰራ፣ የግድቡ ቁመት እንዲያጥር፣ ሌሎችም ምክንያቶችን በመደርደር ችግር ስትፈጥር ቆይታለች። አሁንም የውሀ ሙሌቱ እንዳይከናወን የተለያየ ጥረት በማድረግ ላይ ናት። በቅርቡም ለተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት አቤቱታ አቅርባለች። ይሁን እንጂ በሀሰት ውንጀላ የሚቆም ነገር ስለሌለ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የግንባታ ስራ ለአፍታም ሳታቋርጥ አጠንክራ ቀጥላለች። በመጪው ሐምሌ ወር የውሀ መሙላት ስራ እንደምትጀምር ለዓለም አቀፍ ተቋማት ጭምር ደጋግማ አረጋግጣለች። ከ2013 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮም የመጀመሪያዎቹ ሁለት ዩኒቶች ኃይል የማመንጨት ስራ እንደሚጀምሩ አቅዳ በመስራት ላይ ትገኛለች።
ግብጾች ምንም ይበሉ ምን ኢትዮጵያ በዕቅዷ መሰረት መስራቷን አሁንም ወደፊትም ለአፍታም ያህል አታቋርጥም። ምክንያቱም ትናንት ዛሬም ሆነ ነገ የኢትዮጵያ አቋም በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ነውና። አገራችን ጥንትም ሆነ ዛሬ ማንንም የመጉዳት አካሄድ አትከተልም። አሁንም ደግማ ደጋግማ እንደምትገልጸው የህዳሴ ግድብ ግንባታ እየተከናወነ ያለው የታችኞቹን ሀገራት በማይጎዳና ይልቁኑ ተጠቃሚነታቸውን ባረጋገጠ መልኩ ነው። ለዚህ ደግሞ የማንንም ይሁንታ አትፈልግም፤ አትጠብቅምም። ስለዚህ አሁንም በያዘችው የግድቡ የውሀ ሙሌት ዕቅድ መሰረት ውሀ የመያዝ ስራው ይጀመራል። ይሄ ደግሞ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ትልቅ የድል ብስራትና የህዝባዊ ተሳትፎው ውጤትም ነው።
ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሟን በማስጠበቅ ረገድ የራሷን አቋም ይዛለች። በፍትሀዊነት እና የተፋሰሱን ሀገራት ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መንገድ የአባይን ወንዝ የመጠቀም አቋሟን አጠናክራ ትቀጥላለች ።!
አዲስ ዘመን ግንቦት 9/2012
የጋራ ተጠቃሚነት ዛሬም በአባይ ዙሪያ ያለ የኢትዮጵያ አቋም ነው!