አገራት ለሚያጋጥሟቸው ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች መፍትሄ የሚጠብቁት ከምርምር ውጤቶች ነው። በተለይ ደግሞ እንደ በሽታና ወረርሽኝ አይነት ዓልታሰቡና ተከስተው የማያውቁ ችግሮች ሲያጋጥሙ ከችግሩ መውጫ በማፈላለግ ተስፋ የሚጣልባቸው ተመራማሪዎች፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የምርምር ማዕከላት ናቸው። ለዚህም ሲባልም መንግሥታት የየአገራቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ አውድ መሠረት በማድረግና ለምርምር ሥራዎች ትኩረት በመስጠት የምርምር ሥራዎችን ያግዛሉ።
ከዚህም ባለፈ በርካታ የግል የቢዝነስ ተቋማት የምርምር ሥራዎችን ከመደገፍ አልፈው በባለቤትነትም ያሠራሉ። ምርምሮችን ከኢንደስትሪዎች ጋር በማስተሳሰርም የምርምር ውጤቶች ወደ ምርትና አገልግሎት የሚገቡበትን መንገድም ያመቻቻሉ።
የኢትዮጵያ መንግሥትም ይብዛም ይነስ ለምርምር ሥራ በሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር በጀት በየዓመቱ ይመድባል። የምርምር ሥራን የሚያበረታቱና የሚከታተሉ የምርምር ተቋማትንም በስፋት አደራጅቷል። ከነዚህ ተቋማት የምርምር እና ሥርፀት ሥራዎችን ይጠብቃል። ከተቋቋሙባቸው ዓላማዎችም አንዱና ዋነኛውም ይሄው ነው።
ዩኒቨርሲቲዎቻችን በየዓመቱ የሚያስመርቋቸው በርካታ የድህረ ምረቃ ተማሪዎችም ለመመረቅ እንደ ግዴታ ከሚጣሉባቸው ተግባራት አንዱ የምርምር ሥራ መሥራት ነው። በዚህ ረገድ ስንመዝነው ምንም እንኳን ከሌሎች አገራት አንፃር የምርምር መሠረተ ልማቱና ድጋፉ ብዙም የሚያመጻድቅ ባይሆንም የተወሰነ ርቀት ሊያስጉዝ እንደሚችል ግን ይታመናል።
አሁን ያለንበት ጊዜ ኮቪድ -19 ዓለምንና አገራችንን ያስጨነቀበትና በምላሹም በርካታ የምርምር ሥራዎች እየተካሄዱ ያለበት ወቅት ነው። በዚህ አይነት ወቅት ደግሞ አገራት በተናጥል ከሚያደርጓቸው የምርምር ሥራዎች በተጨማሪ በተለያዩ አገራት ካሉ ተመራማሪዎችና የምርምር ማዕከላት ጋር በትስስር የሚሠሯቸው ምርምሮች ትኩረት ይሰጣቸዋል።
በዚሁ መሠረት ለወትሮው በትልቅ ክፍያዎችና በተለየ ስምምነት ብቻ ይገኙ የነበሩ ሳይንሳዊ መረጃዎች፣
የምርምር ውጤቶች እና ቴክኖሎጂዎች ለማንኛውም በኮቪድ – 19 ላይ ምርምር ለሚያካሂዱ ተመራማሪዎች በነፃ ተደራሽ እንዲሆኑ ተደርጓል።
አሁን ላይ በአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች፣ በቢዝነስ ተቋማት እና በመላው ዓለም ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ያለው ትብብርም ምቹ ነው። በርካታ ለጋሽ ተቋማትም የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በላይ ፍቃደኛና ዝግጁ ናቸው። የአፍሪካ መሪዎችም የገንዘብም ሆነ የፖሊሲ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኝነታቸውን እያሳዩ ነው።
ኮቪድ – 19ን በአገራችን ከፈጠረው ሁለንተናዊ ሥጋት አንፃር የአገራችን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስመልክቶ ምን እየሠሩ ነው የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ወቅታዊና ተገቢ ነው። አብዛኛዎቹ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በስፋት ስለበሽታው ግንዛቤ ከማስጨበጥ ጀምሮ፣ ቁሳዊ ድጋፍ በማሰባበሰብና በማሰራጨት እንዲሁም ሳኒታይዘር በማምረት ሥራዎች ላይ እየተሳ ተፉ መሆንን በተደጋጋሚ እየሰ ማን ነው።
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ እያከናወኑት ያለው ተግባራት ካለባቸው ማህበራዊ ሃላፊነት አንፃር የሚበረታታና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባውም ጭምር ነው። ይሁንና ተቋማቱ ግን ከማህበራዊ ሃላፊነት ባለፈ የምርምር ተቋማት እንደመሆናቸው መጠን ድንገት ተከስተው ህዝብን የከፋ አደጋ ውስጥ ሊከቱ ለቻሉና ለሚችሉ ችግሮች የምርምር መፍትሄ በማፈላለግ ግንባር ቀደም መሆን ይጠበቅባቸዋል።
ችግሮች ከቁጥጥር ውጭ ሆነው እንደ ሀገር ብዙ ዋጋ እንዳያስከፍሉን ፈጥነው በመንቀሳቀስ ፤ ለህዝባችን የጭንቅ ጊዜ ተስፋ መሆን ይጠበቅባቸዋል። በተለይም በዚህ አይነት ወቅት የራስን አቅም በማሳደግ ከተለያዩ አገራት ካሉ ተመራማሪዎችና የምርምር ማዕከላት ጋር በትስስር የመሥራትን ባህል ማሳደግ ይገባቸዋል። የዓለም አቀፍ ጥረት አካል ሆነው መገኘትም ይኖርባቸዋል።
በትልቅ ክፍያዎችና በተለየ ስምምነት ብቻ ይገኙ የነበሩ ሳይንሳዊ መረጃዎች፣ የምርምር ውጤቶች እና ቴክኖሎጂዎች ለማንኛውም በኮቪድ -19 ላይ ምርምር ለሚያካሂዱ ተመራማሪዎች በነፃ ተደራሽ እየሆኑ ባሉበት በአሁኑ ወቅት አጋጣሚውን ወደ ተሻለ ዕድል በመለወጥ ለአገርና ለህዝብ ያላቸውን አጋርነት በተጨባጭ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። ከፍ ያለ በጀት ከመመደብና ተመራማሪዎችን ከማበረታታት ባለፈ የምርምር ሥራዎቹ ወቅቱ በሚፈልገው ፍጥነትና ጥራት ተከናውነው ሕዝባችንን ከበሽታው ሥጋት መታደግ ይኖርባቸዋል።
እንደ አገር በዩኒቨርሲቲዎቻችን ላይ ያለን ተስፋ ትልቅ ነው። ተመራማሪዎቻችን ውሏቸው ቤተ መጻህፍት፤ አዳራቸው ቤተ ሙከራ፤ ትኩረታቸው የህዝባችን ጤና እንዲሆን አደራ ማለትም እንወዳለን። ይህም ሕዝባችን በዚህ ወቅት ከናንተ የሚጠብቀውና በታላቅ የሃላፊነት መንፈስ ልትተገብሩት የሚገባ አደራ ነው!
አዲስ ዘመን ግንቦት 2/2012
ከምርምር ተቋሞቻችን በኮሮና ዘመን