መከላከል የሚቻል የነቀርሳ/ ቲዩበርክሎዝ ህክምና ጤነኛ ለሆኑ ሆኖም ግን የቲቢ(ቲቢ የነቀርሳ/ ቲዩበርክሎዝ በአጭሩ ሲፃፍ ነው) ባክቴሪያን ተሸካሚ ለሆኑ ሰዎች የሚደረግ የህክምና እንክብካቤ ነው። ህክምናው የሚደረገው ሰዎች ከጊዜ በኋላ በነቀርሳ/ ቲዩበርክሎዝ ባክቴሪያ አማካኝነት የሚያጋጥማቸውን የመታመም አደጋ ለመቀነስ ነው። በነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ መከላከያ ህክምና ላይ ያሉ ሰዎች የነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ የለባቸውም። ሌሎች ሰዎችን በነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ ባክቴሪያ አይበክሉም። ሳይታመሙ የቲቢ ባክቴሪያን መሸከም ምን ማለት ነው? አብዛኞቹ በቲቢ ባክቴሪያ የተያዙ ሰዎች አይታመሙም።
የቲቢ ባክቴሪያ በሰውነታቸው ውስጥ “ተሸሽጎ” ይገኛል። የሰውነት በሽታ መከላከል ሥርዓት ባክቴሪያው ተሸሽጎ እንዲቀመጥ ያደርገዋል። የነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ በሽታ ሳይታመሙ በሰውነትዎ ውስጥ የቲቢ ባክቴሪያን በሕይወት ዘመንዎ ሁሉ ተሸክመው ሊኖሩ ይችላሉ። በርካታ ሰዎች ሰውነታቸው ውስጥ የተሸሸገ (የተደበቀ) ቲቢ ባክቴሪያ አላቸው። የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሦስት ሰዎች አንዱ ይህንን ባክቴሪያ ተሸክመው እንደሚገኙ ይገምታል። የቲቢ ባክቴሪያ ከተሸከሙ አስር ሰዎች አንዱ ብቻ የሳንባነቀርሳ በሽታ ይይዛቸዋል።
ሳይታመሙ የቲቢ ባክቴሪያን መሸከም ላተንት ነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ ወይም የላተንት ነቀርሳ/የተደበቀ ነቀርሳ (LTBI) በመባል ይታወቃል። የላተንት ነቀርሳ/ የተደበቀ ነቀርሳ ያለበት ሰው፡• በነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ በሽታ የተያዘ አይደለም፣ ሌሎች ሰዎችን አይበክልም። • የቆዳ ምርመራ (ማኖተስ) ወይም የደም ምርመራው ግለሰቡ የቲቢ ባክቴሪያ እንዳለበት ያሳያል።
• ሆኖም ግን የአክታ ወይም በሳል አማካኝነት ከአፍ የሚወጣ ወፍራም ምራቅ ምርመራ ውጤት ኔጋቲቭ ነው (ከመደበኛው ውጭ የሚያሳየው ነገር የለም) የነቀርሳ/ ቲዩበርክሎዝ በሽታ ለሌለባቸው ሰዎች የቲቢ መድሃኒት ለምንድን ነው የሚሰጠው? በሰውነት ውስጥ ተሸሽጎ (ተደብቆ) የሚኖርን የቲቢ ባክቴሪያ ለመግደል ሲባል የቲቢ መከላከያ መድሃኒት ይሰጣል፣ ይህ ህክምና የሚደረገው በበሽታው የመያዝ እና የመታመም አደጋን ለመቀነስ ነው። ይህ ህክምና ግለሰቡ በመቀጠል ነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ በሽታ የመያዙን ሁኔታ ይቀነሳል። ለመከላከል ማለት ለማስቀረት ማለት ነው። ለዚህ ነው ህክምናው የመከላከል ህክምና ተብሎ የሚጠራው።
በቲቪ ቫክቴሪያ የተያዘ ሰው የመከላከያ ህክምናውን መውሰድ የሚገባቸው እነማን ናቸው?
በዋናነት ከጊዜ በኋላ ከፍተኛ የሆነ በበሽታው የመያዝ ዕድል ላላቸው ሰዎች ብቻ ነው። ይህ ህክምና እንዲሰጣቸው የሚመከሩ ሰዎች የመጀመሪያው እና ዋነኛው ናቸው፡-
• ልጆች እና ታዳጊ ወጣቶች
• በሽታ የመከላከል ችሎታቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎች
• በሽታ የመከላከል ሥርዓታቸውን የሚቀንስ መድሃኒት የሚወስዱ ሰዎች
• ሌሎች በሸታ ያለባቸው ሰዎች (እንደ ስኳር እና የኩላሊት መሳን ያለባቸው)
• ኤችአይቪ ፖዘቲቭ የሆኑ ሰዎች
• የሰውነት ክብደታቸው ዝቅተኛ (በጣም ቀጭን) የሆኑ ሰዎች
• በቲቢ በቅርቡ የታወኩ ሰዎች፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ወይም ከዚያ በታች በሆኑ ጊዜ ውስጥ በባክቴሪያው የታወኩ ሰዎች ከእነኝህ ከተጠቀሱት በአንዱ ምድብ ውስጥ የሚካተቱ ከሆነ፣ በሽታ የመከላከል ሥርዓትዎ ባክቴሪያውን በሰውነትዎ ውስጥ “ሸሽጎ” ለማስቀመጥ በጣም ደካማ ሊሆን ይችላል፣ እና ባክቴሪያው በሰውነትዎ ውስጥ “የመነሳት” አደጋ ሊኖር እና በነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ በሽታ መታመምዎን ከፍተኛ ሊያደርገው ይችላል።
ስለዚህም ከላይ ከተጠቀሱት ቡድኖች በአንዱ (ከአንድ በላይ) ውስጥ ላሉ ለማንኛውም ሰዎች ይህን የመከላከያ ህክምና ይመክራሉ። በተለይም ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በባክቴሪያው የመታወክ እድል ካለዎ፣ ምክንያቱም በበሽታው ከታወኩ በኋላ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ የመታመም ስጋቱ ከፍተኛ በመሆኑ ከፍተኛ በመሆኑ ነው። ሆኖም ግን፣ አንዳንድ
ሰዎች ምንም አንኳ በስጋት ምድቦች ውስጥ ባይሆኑም የመከላከያ መድሃኒቶችን እንዲወስዱ ሊመከሩ ይችላሉ። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ በአስጊው ምድብ ውስጥ ሆነው የመከላከያ ህክምናውን እንዳይወስዱ ሊመሩ ይችላሉ።
በእያንዳንዱ የግለሰቦች ጉዳይ ዶክተሩ የመከላከያ ህክምና መውሰድ እንዳለባቸው እና እንደሌለባቸው ይወስናል። ዶክተሩ መሰረት የሚያደርገው የግለሰቦችን አጠቃላይ የጤና ግምገማ እና ሁኔታዎች ውጤት ላይ ነው። ጥቂት የቲቢ ባክቴሪያ ተሸካሚ የሆኑ ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ዶክተሮቻቸውን በየጊዜው ለመደበኛ ምርመራ እንዲጎበኙ ይመከራሉ፣ ነገር ግን የመከላከያ መድሃኒት እንዲወስዱ አይደለም። በመደበኛ ምርመራ አማካኝነት፣ ዶክተሩ የግለሰቡን የጤና ሁኔታ ይከታተላል። “ የተሸሸገ ቲቢ ባክቴሪያ” ወደ ንቁ ቲቢ ባክቴሪያ እያደገ እንደሆነ የሚያሳይ ማንኛውም ምልክት ካለ፣ ዶክተሩ ይህንን ሁኔታ ያገኛል እና ህክምናው ወዲያውኑ እንዲጀመር ያደርጋል። የነቀርሳ/ ቲዩበርክሎዝ ምልክቶችን የሚያሳዩ ከሆነ፣ ወዲያውኑ ዶክተርዎን መጎብኘት አለብዎ።
የነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ ምልክቶች
• ከ 2 እስከ 3 ሳምንታት ወይም ከዚያ በላይ የቆየ ሳል
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
• የክብደት መቀነስ (በጣም ቀጭን ይሆናሉ)
• የአቅም መቀነስ እና ድካም ስሜት
• ለረዥም ጊዜ ትኩሳት ሲኖርዎ
• የሌሊት ላብ
• በጉሮሮ፣ በብብት እና መገጣጠሚያ ስፍራዎች ላይ የሚኖር እብጠት ወይም ጠጣር ነገር በአብዛኛው የታወቀው የነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ የሳንባ-ቲቢ ነው። ሆኖም ግን አንድ ሰው በሌሎች የሰውነት ክፍሎችም ቲቢ ሊገኝበት ይችላል። ወደ ሌላ ሰው የሚተላለፈው የሳንባ ቲቢ ብቻ ነው። የመከላከያ ቲቢ ህክምና በፍላጎት የሚደረግ ነው። የመከላከያ ህክምናን ማድረግ ከፈለጉ፣ ህክምናውን ማጠናቀቅዎ በጣም አስፈላጊ ነው።
የቲቢ መከላከያ ህክምና በነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ የመያዝ ሁኔታን ይቀንሳል። ቲቢን የመከላከል ህክምና በቲቢ የመያዝ ዕድሎትን ይቀንሰዋል። እንደሚገመተው ህክምናው ወደፊት በቲቢ የመታመም አደጋውን በግማሽ ያህል ይቀንሰዋል። ሆኖም ግን በመከላከል ህክምናውም ቢሆን ሙሉ በሙሉ ጠነኛ ሆነው ሊቆዩ ይችላሉ ብሎ ማረጋገጫ መስጠት አይቻልም። ህክምናውን ካጠናቀቁ በኋላ አንስተኛ መጠን ያለው የቲቢ ባክቴሪያ በሰውነትዎ ውስጥ ሊቀር ይችላል። አነስተኛ በሆኑ አጋጣሚዎች እነዚህ ባክቴሪያዎች “ሊነቁ” እና እንዲታመሙ ሊያደርግዎ ይችላሉ። በሳንባ ነቀርሳ/ቲዩብርክሎዝ እንደገና ሊበከሉ የሚችሉበት አጋጣሚ አለ። የመከላከል ህክምናው ሊሰራ የሚችለው በህክምና ወቅት ቀድሞውኑ በሰውነትዎ ውስጥ ያሉት ባክቴሪያዎች ላይ ብቻ ነው። እንደገና መታመም ምናልባትም ወደፊት “በአዲስ ” ባክቴሪያ መበከልዎን ሊከላከልልዎት አይችልም።
የቲቢ ባክቴሪያዎች ወደ ሰውነት የሚገቡበት መንገድ
የቲቢ ባክቴሪያ የሚሰራጨት በዓይን ሊታዩ በማይችሉ ረቂቅ በአየር ላይ ባሉ ጠብታዎች አማካኝነት ነው፥ በምንስልበት፣ በምናስነጥስበት ወይም በምናወራበት ወቅት ጠብታዎቹ ከሳንባችን ተነሰተው በአፍንጫችን እና አፋችን አድርገው ወደአየር ውስጥ ይገባሉ። ተላላፊ የቲቢ በሽተኛ ከሆነ ሰው ሳንባ ውስጥ የሚወጡ ጠብታዎች የቲቢ ባክቴሪያ ይይዛሉ። ይህንን አየር ከሳቡት የቲቢ ባክቴሪያ የያዙ ጠብታዎች ወደሳንባዎ ሊገቡ ይችላሉ። በሽታው ካለበት ሰው ጋር ተመሳሳይ አየር ከተነፈሱ የሳንባ ነቀርሳ/ቲበርክሎዝ ባክቴሪያ ወደሰውነትዎ ሊገባ ይችላል።
ተላላፊ የሳንባ ቲቢ ያለባቸው ሰዎች ጋር የተቀራረበ እና ለረጅም ጊዜ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በቲቢ ባክቴሪያ የመበከል አደጋ አለባቸው። የቲቢ ባክቴሪያ በቀላሉ አይተላለፍም። ስለዚህ በአብዛኛው ሊበከሉ የሚችሉት አብሮ በመኖር ወይም ለረጅም ጊዜ አብሮ በመኖር ነው። ነገር ግን በሚገባ የቲቢ መድሃኒት ለሁለት ሳምንት የወሰደ ሰው ሊበክሎት አይችልም። ከሳንባ ነቀርሳ/ ቲበርክሎዝ ጋር የሚኖር በእያንዳንዱ አገር በዓለም ላይ ብዙ ሰዎች አሉ።
የእውቀት ማነስ በቲቢ መበከልን እና ቲቢ በሽታን ወደ መፍራት ያመራል። በርካታ ሰዎች ስለ ብክለቱ፣
እንዲሁም በቲቢ መበከል (ላተንት ቲቢ በሰውነት ውስጥ መኖር) እና በቲቢ በሽታ መታመም መካከል ስላለው ልዩነት ጥቂት ነገር ነው የሚያውቁት። የዕውቀት ማነስ ወደ ፍርሃት እና አላስፈላጊ መላመት ይመራል። አንዳንድ ጊዜ፣ ሰዎች አንድ ሰው ነቀርሳ/ ቲዩበርክሎዝ እንዳለበት የሚያስቡ ከሆነ ከዚያ ሰው ጋር መብላት ይፈራሉ። እንዲሁም ከእንዲህ ያለው ሰው ጋር መነጋገርም ይፈራሉ። ምክንያቱም በበሽታው እንያዛለን ብለው ስለሚያሰቡ ነው። ለሌሎች ሰዎች እርስዎ እንዳልታመሙ ፣ እንዲሁም ደግሞ ምንም እንኳ እርስዎ የቲቢ መከላከያ ህክምና ላይ ቢሆኑም እርስዎ በሽታውን እንደማያስተላልፉባቸው እንዲረዱ ማሳመን ከባድ ሊሆን ይችላል። ይሁንና ስለ ነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ እና የቲቢ ባክቴሪያ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ እንዴት እንደሚተላለፍ የበለጠ በሚያውቁ ጊዜ፣ ፍራቻቸው ይቀንሳል። የቲቢ መከላከያ ህክምናን እየወሰዱ እንደሆነ ለሌሎች የመንገር ግዴታ የለብዎትም። የቲቢ መከላከያ ህክምናን የሚወስዱ ሰዎች በቲቢ በሽታ ታማሚዎች አይደሉም። ስለዚህም ሌሎች ሰዎችን አያውኩም/ አይበክሉም።
የመከላከያ ህክምና ለመጠየቅ ከመረጡ፣ ለእርስዎ የሚሆን ግላዊ የህክምና እቅድ ይዘጋጅልዎታል። ስለዚህም ህክምናዎ ከእርስዎ ግላዊ ፍላጎት ጋር ሊዛመድ ይችላል። የህክምና ዕቅድ አብዛኛውን ጊዜ የሚዘጋጀው ህክምናው ከመጀመሩ በፊት ነው፣ ዶክተርዎ፣ የቲቢ አስተባባሪ እና እርስዎ በሚሳተፉት ስብሰባ ላይ ይሆናል።
መደበኛ የቲቢ ህክምና እና የቲቢ መከላከያ ህክምና ጥቂት ተመሳሳይ መድሃኒቶችን ያካትታል። ነገር ግን ሁልጊዜም የመከላከያ ህክምናው አጭር የህክምና ጊዜን ያካትታል። አብዛኛውን ጊዜ፣ ሁለት ዓይነት መድሃኒቶች (ሪፋምፒሲን እና አይሶናይዝድ) ለሦስት ወራት በየዕለቱ ይወሰዳሉ። አንዳንድ ጊዜ በአንድ ዓይነት መድሃኒት ብቻ (አይሶናይዝድ) የህክምና ጊዜው ስድስት ወራት ይሆናል። አንድ ሰው ከሁለት ሳምንታት በኋላ እንዲሁም በድጋሚ ከስድስት ሳምንታት በኋላ የደም ምርመራዎች አንዲያደርግ ይጠየቃል።
ጥቂት ታማሚዎች መድሃኒቶቹ ይሰጡዋቸው እና ያለ ምንም የዕለት ተዕለት እገዛ ወይም ምክር ይወስዱዋቸዋል። ሌሎቹ ደግሞ በጤና ሠራተኛ መድሃኒቱ በየዕለቱ ይመጣላቸዋል። ይህ በቀጥታ የሚታይ ህክምና ተብሎ ይጠራል። ጥቂት ታካሚዎች በየዕለቱ የሚወስዱት በህክምናቸው የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ነው፣ ነገር ግን ለቀሩት ጊዜያት መድሃኒቱን እራሳቸው በቤት ውስጥ ይወስዳሉ። ከዚህ ውጭ የሚደረግ ህክምና መድሃኒቱን በራሳቸው የሚወስዱ ታካሚዎች አብዛኛውን ጊዜ ለአንድ ሳምንት የሚሆን መድሃኒት ይሰጣቸዋል። ጥቂት ሰዎች ያለምንም ችግር ሳይረሱ መድሃኒታቸውን በተከታታይ ይወስዳሉ፣ ሆኖም ግን ለሌሎቹ ደግሞ ይህ በጣም ፈታኝ ነገር ሊሆንባቸው ይችላል። ሁልጊዜ የማያስታውሱ ከሆነ፣ የማስታወሻ ደወል ያቀናብሩ ወይም ለራስዎ ማስታወሻ ይፃፉ። መድሃኒቱን መቼ እና እንዴት መውሰድ እንዳለብዎ እርግጠኛ ካልሆኑ፣ ወይም ሌላ ማንኛውም ዓይነት ጥያቄ ካለዎ፣ እባክዎን የቲቢ አስተባባሪውን ወይም ዶክተርዎን ያነጋግሩ።
መድሃኒትዎን በየዕለቱ የመውሰድ ስሜት ላይሰማዎ ይችላል፣ በተለይም የጎንዮሽ ጉዳቶች ካጋጠመዎ። ወይም ደግሞ ሊረሱ ይችላሉ። ህክምናዎ እንዲሰራ፣ መድሃኒቱ በየዕለቱ መወሰድ አለበት እንዲሁም የህክምና ጊዜው መጠናቀቅ አለበት። ይህ መሆኑን ያረጋግጣል። እንዲሁም ማለት የጤና ሠራተኛው በእርስዎ ላይ የመድሃኒቱን ውጤት እና የጎንዮሽ ጉዳት ይመለከታል፣ እናም ስለሚታየው የጎንዮሽ ጉዳት ብሎም በአጠቃላይ ስለ ህክምናው ምክርን ይለግስዎታል። የህክምና ዕቅድ ስብሰባ
መድሃኒቱን በመውሰድዎ ሊከሰቱ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች
የቲቢ መከላከያ መድሃኒቶች አንዳንድ ጊዜ የጎንዮሽ ጉዳቶች ያመጣሉ። ከቲቢ ባክቴሪያ ጋር በሚያደርገው ትግል፣ መድሃኒቱ በሰውነት አካል ላይ አላስፈላጊ ጉዳቶች ሊኖረው ይችላል። ይህ ክፍል ስለ ጎንዮሽ ጉዳቶች እንዲሁም የጎንዮሽ ጉዳት ሲከስት ምን ማድረግ እንደሚችሉ መረጃን ይሰጥዎታል። ታካሚዎች ለመድሃኒቱ የተለያየ ዓይነት ምላሽ አላቸው። አብዛኞቹ የቲቢ መከላከያ ህክምና ላይ ያሉ ሰዎች ምንም የጎንዮሽ
ጉዳት ችግር የላቸውም ሆኖም ግን ጥቂቶች አላቸው። እንዲህ ያለው የጎዮሽ ጉዳት አብዛኛውን ጊዜ መድሃኒቱ ከሰውነት ጋር በሚላመድ ጊዜ ይቀንሳል (ችግሩ እየቀነሰ ይሄዳል)።
ይህ አብዛኛውን ጊዜ ከሁለት እስከ አራት ሳምንታትን ይወስዳል። አንዳንድ ጊዜ የጎንዮሽ ጉዳቱ በአጠቃላይ ይጠፋል። ከባድ የጎዮሽ ጉዳቶች አብዛኛውን ጊዜ አይኖሩም፣ ሆኖም ግን ሊከሰቱ ይችላሉ። ስለዚህም ማንኛውንም የሚያጋጥምዎትን ህመሞች እና ሌሎች የጎዮሽ ጉዳቶች ለዶክተርዎ፣ ለቲቢ አስተባባሪዎ ወይም ለወረዳ ነርስ መንገርዎ በጣም አስፈላጊ ነው። በህክምናው ጊዜ በሁኔታዎ ወይም በፍላጎቶችዎ ላይ ለውጥ ካለ፣ የህክምና ዕቅድዎ እንዲለወጥ መጠየቅ ይችላሉ። በአንዳንድ አጋጣሚዎች፣ የቲቢ መድሃኒቶች የጉበት ኢንፌክሽን (ሄፕታይተስ) ሊያመጡ ይችላሉ።
ዶክተርዎ ጉበትዎ መድሃኒቱን ምን ያህል እየተቋቋመ እንደሆነ ለመቆጣጠር እንዲችል፣ በህክምና ጊዜ ውስጥ በርካታ የደም ምርመራዎች ይኖርዎታል። በአንዳንድ አጋጣሚዎች፣ ህክምናውን ማቋረጥ ወይም እረፍት መውሰድ ሊያስፈልግ ይችላል። ዶክተርዎን በፍጥነት ይጎብኙ፡ የአይንዎ ነጩ ክፍል ቢጫ ከሆነ (ጆንዲስ)፣ መጥፎ የሆነ የሆድ ህመም/ቁርጠት ካለዎ፣ በጣም የሚያቅለሸልሽዎ (ከታመሙ) ከሆነ፣ ካስመለስዎ፣ የድካም ስሜት የሚሰማዎ ከሆነ (በጣም ከደከምዎ እና ጉልበት ካነስዎ)፣ ወይም በሰውነትዎ አብዛኛው አካል ላይ ቆዳዎ የመቆጣት እና ሽፍ የማለት ነገርን ካሳየ። አልኮል: አልኮል እና የቲቢ መከላከያ መድሃኒት ሁለቱም የሚወሃዱት (የሚፈጩት) በጉበት ውስጥ ነው።
የቲቢ መከላከያ ህክምናን በመውሰድ ላይ እያሉ አልኮል ከወሰዱ፣ የጉበት መጎዳት አደጋን ይጨምራሉ። አልኮል መጠጣት ከፈለጉ፣ በመጀመሪያ ይህን ከዶክተርዎ ጋር መወያየት አለብዎ። የህመም ስሜት መከላከያዎች፡ ጥቂት የህመም ስሜት መከላከያ መድሃኒቶች (ፓራሲታሞልን ያካተቱ) የሚዋሃዱት በጉበት ውስጥ ነው። የህመም ስሜት መከላከያ መድሃኒቶችን መጠቀም ከፈለጉ፣ የትኛውን መውሰድ እንዳለብዎ እና የጥንቃቄ ገደቡ ምን እንደሆነ ከዶክተርዎ ጋር ይወያዩ። የጎንዮሽ ጉዳቶችን ለመታከም ታካሚዎች የአገልግሎት ክፍያውን መክፈል አለባቸው። የመከላከያ ህክምናው ነፃ ቢሆንም፣ የጎንዮሽ ጉዳቶች መድሃኒት ዋጋ አይሸፈንም።
የህመም ስሜት እንዲሰማዎ የሚያደርጉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ቢያጋጥምዎም መድሃኒቱን መውሰድ መቀጠልዎ አስፈላጊ ነው። በአብዛኛው የተለመዱ የጎንዮሽ ጉዳቶች በዚህ ክፍል የምንዘረዝራቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች ምቾት ያላቸው አይደሉም፣ ሆኖም ግን አደገኛ አይደሉም። እነኝህን የጎንዮሽ ጉዳቶች ብዙ ገንዘብ ሳያወጡ እንዴት መታከም እንደሚችሉ ከታካሚዎች እና ጤና ሰራተኞች ምክሮችን እናጋራለን። አስተያየቶቹ የተጠበቁ ናቸው፣ እና የቲቢ መድሃኒቶች ሥራ እንዲቀንስ አያደርጉም። እዚህ የተሰጡት ዘዴዎች የማይረዱዎት ከሆነ፣ ለተጨማሪ ምክር የቲቢ አስተባባሪዎን፣ ዶክተርዎን ወይም የወረዳ የጤና ነርስን ያነጋግሩ።
የቲቢ መድሃኒት በጣም የተለመዱ የጎንዮሽ ጉዳቶች
ማቅለሽለሽ (የህመም ስሜት)
• ቀይ ሽንት
• ምግብ የመፈጨት ችግሮች (የሆድ ህመም፣ የሆድ ድርቀት ወይም ማስቀመጥ)
• ማሳከክ እና የሰውነት መጉረብረብ/ሽፍታ
• ትኩሳት
• በመገጣጠሚያዎች ላይ እንዲሁም በሌሎች የሰውነት አካላት ላይ የሚኖር ህምም እና እብጠት
• የመደንዘዝ፣ በእጅዎ እና በእግርዎ ላይ ስፒል እና መርፌዎች የመውጋት ስሜት
• የደካማነት እና የድካም ስሜት መሰማት
• ራስ ምታት
የቲቢ መከላከያ መድሃኒት እና ሌሎች መድሃኒቶች የቲቢ መድሃኒት ሌሎች መድሃኒቶች ኃይላቸው እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል። ስለዚህም ለዶክተርዎ ስለሚወስዱዋቸው ሌሎች መድሃኒቶች መንገር አለብዎ። ራፋምፕሲን በሚወስዱ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች እርግዝናን አይከላከሉም ስለዚህም ሌላ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ፣ እንደ ኮንዶም ወይም በማህፀን ውስጥ የሚገባ የህክምና መከላከያ ያለውን መጠቀም አለብዎ (ኮንደም ወይም “ስፒራል”).
ምንጭ፡- LHL Internasjonal
አዲስ ዘመን ግንቦት 1/2012
ጌትነት ተስፋማርያም
የነቀርሳ/ቲዩበርክሎዝ መከላከያ ህክምና ምንድን ነው?