የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ከሩቁም አስከ ቅርቡ በዘመናት መካከል ስክነት የሌለበት በኃይለኞች እና በባለ ጉልበተኞች ተጀምሮ የሚልቅ፤ ሁሌ ከዜሮ ጀምሮ ወደ ዜሮ የሚመለስ አዙሪት ውስጥ የኖረ ስለመሆኑ የታሪክ ማህደሮቻችን በደማቅ ቀለማት ያሰፈሯቸው ሀቆች ናቸው።
በእነዚህ የታሪክ ዘመናት ውስጥ ጉልበት ያለው ጉልበቱ እስኪደክም ወይም እስኪሞት አልፋና ኦሜጋ ሆኖ ምድራዊም ከዚያም ባለፈ ሰማያዊ የሆነ የመግዛት ባለመብት የሆነ እስኪመስለው ድረስ ጡንቻው እስካራመደው ድረስ በፊቱ ያለውን እየደፈጠጠ የሚሄድበት የፖለቲካ ስርዓቶች ተፈራርቀዋል።
ብዙም ሩቅ በማይባለው በዘመነ መሳፍንት የታሪክ ወቅት ያለውን እንኳን ብንመለከት የማዕከላዊ መንግሥት አቅም መዳከሙን የተረዳ ወይም የሴራው መንገድ ወደ ስልጣን ለመውሰድ አመቹ ሁኔታ መሆኑን ያመነና እራሱን ባለተራ ያደረገ ጉልበተኝ በሺዎች የሚቆጠሩ ከራሱ የቤት እቃ በተለየ መለክ የማያስባቸውን የዋሀን በእንድም ይሁን በሌላ አሰልፋ፤ በነሱው ደም ወደ ስልጣን መንበሩ መገስገሱ የተለመደ ነው።
በሀገሪቱ በተካሂዱ የእርስ በርስ ጦርነቶች ሕይወታቸውን የገበሩ በሚሊዮን ሊቆጠሩ የሚችሉ ኢትየጵያውያን ከጦርነቶቹ ምን አተረፉ ብለን ስንጠይቅ ልናገኝ የምንችለው መልስ አሳዛኝ ነው።
ሕይወታቸውን ከመገበር ባለፈ በአሳዳሪ ዎቻቸው እንደ ግል እቃ የመታየታቸውን እውነታ እንኳን መለወጥ የቻለ አልነበረም። ደማቸውን ገብረው በላያቸው ላይ የሚያነግሷቸው ጌቶቻቸው በቤተ መንግሥታቸው ለሚያስተርኩት የጦር ሜዳ ገድል ማጣፈጫ ከመሆን ያለፈ አይደለም፤አልነበረምም።
የጦር ሜዳ የገድል ታሪኩ በራሱ የባርነ ታቸውን፤ የፍጹም ተገዥነት ስነ ልቦናዊ የእስር ገመዱን የሚያጠብቀው፤ የአሳዳሪዎቻቸውን የስልጣንና የሁለን ተናዊ ገዥነት ስነልቦና ከማድለብ ያለፈ ሀገራዊ ሆነ ህዝባዊ ፋይዳ አልነ በረውም።
በ20 ክፍለ ዘመን ሳይቀር በሀገሪቱ የተካሄዱ የእርስ በርስ ጦርነቶች የዚህ ታሪካዊ አውነታ አካል ናቸው። የሚለዩት ርእዮተ ዓለማዊ ካባ የተሠ ራላቸው ህዝባዊ የሚመስሉ ግጥምና ዜማ የወጣላቸው መሆናቸው ብቻ ነው። ከዚያ ባለፈ አዳዲስ አምባገነኖችን ከመፍራት ያለፈ እውነታ ማምጣት አላስቻሉም።
የየዋሀን የደም መስዋእትነት ለጉልበተኞች የጦር ሜዳ ገድል ማድመቂያ ፤ለእነርሱ ለራሳቸው ለሚተርፈው አንባገነናዊነታቸው ጉልበትና አቅም ትምክህት ነው የሆኑላቸው።
ይህ በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ዘመናት እየቆጠረ ህዝባችን ለደም ግብር የዳረገውና ብዙ ዋጋ ያስከፈለን እውነታ ዛሬም ታሪካዊ ኡደቱን ጨርሶ ጉልበተኛ ነን፤ ሀገር የመምራት ሳይሆን የመግዛት ባለተራ ነን፣ ባለመብት ነን የሚሉ በቀደመው ዘመን አስተሳሰብ እርሾ የተቦኩ ፖለቲከኞች ፋታ እያጣች ነው።
በአንድ በኩል ለህዝቡ ጠላት በመፍጠር ፤ ከጠላት እራስህን ጠብቅ በሚል ለከፋ አደጋ እያዘጋጁት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ትርኪ ምርኪ ለህዝባችን እንደ ህዝብ አንዳች ፋይዳ የሌላቸውን አጀንዳዎች በመፍጠር፤ አጀንዳዎቹን የህዝብ አጀንዳ እድርጎ ግጥምና ዜማ በመድረስ ህዝቡን የከፋ ዋጋ ለማስከፈል እየተጉ ነው።
ይህ በህዝባችን ደም መስእዋት የሚታሰብ የስልጣን መሻት እስከአሁን ባለው ታሪካችን መላውን ህዝባችንን ከአንድ የባርነት እስር ወደሌላ የባርነት እስር ከማሸጋገር ባለፈ የነፃነት ባለቤት አላደረጋቸውም። ብዙ የተዘመረላቸው የህዝባዊነትና የነፃነት ትግሎች ህዝባችንን የከፋ ዋጋ አስከፈሉ እንጂ ትግሉ ያስከፈለውን ዋጋ ፍሬ ለመብላት ባለ ዕድል አላደረጋቸውም።
ለህዝባዊነትና ለነፃነት የተከፈሉ ዋጋዎች ለአምባገነኖች አምባገነናዊ አቅም የሚሆን ትርክትን ፈጠሩ እንጂ የትግሉን የመስዋእትነቱን ፍሬ እንዲመገብና በዚያም የታሪክ ሠሪነት መንፈስ እንዲላበስ አላድረጉትም። በመስዋእትነቱ እንዲያፍርና እንዲቆዝም አረጉት እንጂ አፉን ሞልቶ እንዲናገር አላስቻሉትም።
ከዚህ ተጨባጭ ከሆነው በየዘመኑ በሽግግር ዘመናቸን በመሻገሪያው ድልድ ላይ እያደባ የደም ዋጋ ከሚያስከፍለን የእርግማ አዙሪጥ የምንወጣበት ወቅት አሁን ነው። ለዚህ ደግሞ ሀገርና ህዝብን ግርግር ወስጥ ከተው ከግርግር የፖለቲካ ገበያ ተጠቃሚ ለመሆን የሚተጉ ፖለቲከኞችን በአግባቡ ቆም ብለን ልናያቸው ይገባል።
የጀመርነው የሽግግር ጉዞ ረጅም መንገድ ለመጓዝ እንደተዘጋጀ መንገደኛ ሰፊ ጊዜ ሰጥተን ልንዘጋጅበት የሚገባ ነው። ድንገት ሱቅ እንደሚሄድ ገበያተኛ እየሄድን የምናስበው ወይም በሱቁ መደርደሪያ ላይ እያየን የምንገበያው ሸቀጥ አይደለም።
የለውጥ ሃሳቦች ትውልድ ተሸጋሪ ከመሆናቸው አንጻር እየሄድን የምናስባቸው፤ በሞቅታና ከወቅታዊ ትርፍና ኪሳራ አንጻር የምናሰላቸው አይደሉም። ከፍተኛ መስዋእትነት የሚጠይቁ ናቸው። በብዙ ራስን ከመካድና የህዝብን የነገ ተስፋ የማንነት ልእልና ምንጭ አድረጎ ማሰብናን ለዚህም እራስን መስዋእት ለማድረግ መዘጋጀትን ይጠይቃል። የጀመርነው የለውጥ መንገድ የደም መንገድ አደለም። የአስተሳሰብ ልእልና ትግል ፍሬ ውጤት ነው።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 28/2012
የጀመርነው የለውጥ መንገድ የአስተሳሰብ ልእልና ትግል ፍሬ ውጤት ነው