የኢትዮጵያን ኮንስትራክሽን ዘርፍ ‹‹ፀደቀ ይሁኔ ኮንስትራክሽን›› በሚል ስያሜ በደረጃ 8 ተቋራጭነት ከዛሬ 28 ዓመት በፊት በ1984 ዓ.ም ዘርፉን ተቀላቅሏል:: ከአመት በኋላም ስያሜውን ወደ ‹‹ፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ›› በመቀየር የአገር ውስጥ የኮንስትራክሽን ሴክተር ገና በዳዴ በሚሄድበት በዛን ወቅት በዚህ የቢዝነስ ዘርፍ ከተሰማሩበት ጋር በንኡስ ተቋራጭነት ሰርቷል:: ይህም የግንባታ አስተዳደርና የሰው ሃይል አቅሙን ለማጎልበት አግዞታል:: ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ በሪል እስቴትና በኮንስትራክሽን ቢዝነስ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ቀዳሚ ከተባሉ ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ ለመሆን በቅቷል- ፍሊንትስቶን ሆምስ::
ኢንጂነር ፀደቀ ይሁኔ የፍሊንትስቶን ሆምስ መስራችና ባለቤት ናቸው:: የተወለዱት እዚሁ አዲስ አበባ ነው:: በሲቪል ምህንድስና የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከህንድ አገር አግኝተዋል:: ከዛ ተመልሰው በውሃ ልማት እና በቡና ተክል መስሪያ ቤቶች በተማሩበት ሞያ አገልግለዋል:: ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ ከአንድ አመት በኋላ በጥቅምት ወር በ1984 ዓ.ም ፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ የተሰኘ የኮንስትራክሽን ድርጅት በመቋቋም የግላቸውን ስራ ለሃያ ዓመታት ያህል ሲሰሩ ቆይተዋል:: የተሻለ ገቢ ለማግኘት በማለምም ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሪልእስቴት ቢዝነስ በመግባት እየሰሩ ይገኛሉ::
ወደ ሪልእስቴት ኢንቨስትመንት ቢዝነስ ከገቡ ወዲህ በአስራ ሁለት አመታት ውስጥ እያደገ የመጣውን የቤት ፍላጎት ለማርካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሲያበረክቱ ቆይተዋል:: በአሁኑ ወቅትም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ግንባታ ፕሮጀክቶችንና የመኖሪያ ቤት ግንባታዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ:: በስራቸውም በትንሹ 1 ሺ ከፍ ሲልም 2ሺ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዚያዊ የስራ እድል ፈጥረዋል:: በሪልእስቴትና በሌሎች ግንባታዎችም በአመት ከ600 እስከ 700 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ስራዎችን ሰርተው ያስረክባሉ::
የኮንስትራክሽን ዘርፉ በተለያዩ ችግሮች እየተፈተነ በመጣበት በአሁኑ ወቅት ታዲያ ‹‹ፍሊንትስቶን ሆምስ የራሱን የቢዝነስ ሞዴል በመከተል ስኬቱን ለማስቀጠል ጥረት እያደረገ ነው›› ይላሉ ኢንጂነር ፀደቀ:: እንደ እርሳቸው ገለፃ፤ ቤት ወይም መደብሮችን ሰርቶ መሸጥ ወይም ማከራየት አልያም ከዚህ ጋር በተያያዘ ራስን ለመጥቀም የሚደረግ ጥረት ሁሉ በሪል እስቴት ቢዝነስ አዋጅ ውስጥ ይካተታል:: ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ የሪልእስቴት ቢዝነስ ተደራጀ ወይም ደራ የሚባለው መጠኑና ገበያው ከፍ ሲል ነው::
እዚህ ላይ ታዲያ መደብሮችንና ቤቶችን የሚሰራውና የሚያከራየው አካል መንግስት በመሆኑ የመጀመሪያው የሪል እስቴት ቢዝነስ ተግዳሮት ዘርፉ ከመንግስት አቅርቦት ወደ ግል አለመቀየሩ ነው:: ይህም የግል ባለሃብቱ በዚህ የቢዝነስ ዘርፍ ያለው ተሳትፎ አነስተኛ መሆኑን ያሳያል::
ከመንግስት በመቀጠል ትልቁና ዋነኛ የሪልእስቴት ቢዝነስ ተግዳሮት የአብዛኛው ህብረተሰብ ቤትና መደብር የመግዛት አቅም ዝቅተኛ መሆን ሲሆን ይሄ በሌለበት ሁኔታ ገበያ ሊኖር አይችልም:: ሰዎች አቅማቸውን ወደ ገንዘብ የሚመነዝር ኢኮኖሚ በሌለበት ሁኔታ፤ የረጅም ግዜ ገቢን ወደ ቤት ባለቤትነት ሊያሸጋግር የሚችል የፋይናንስና የቤት አቅርቦት ስርዓትና የግለሰቦች የሞያ ትርፋማነትና ምርታማነት ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት ቤት ከፍተኛ ገቢ ያላቸው መደብ ብቻ ሆኖ ተፈርጇል:: በመሆኑም መንግስት አቀርባለው የሚለውን ለግሉ ባለሃብት ቢተው ይህ ችግር ላይኖር ይችላል:: የመሬት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ ገበያው ለተወሰኑ ባለሃብቶች ብቻ ያደላ መሆኑም የሪል እስቴት ቢዝነሱ ተጨማሪ ተግዳሮቶች ናቸው::
በዚህ ረገድ ፍሊንትስቶን ሆምስ እየተከተለ ያለው የቢዝነስ ሞዴል መንግስት እየሰራቸው ካሉ የጋራ መኖሪያ ቤት በመማር ነው:: ብዙ ግዜ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለእድለኞች በእጣ ሲተላለፉ የቤቶቹ ገበያ ይደራል:: ይህ ገበያ ሲታይ ቤት በርካሽ ተሰርቶ በውድ ዋጋ ሊሸጥ እንደሚችል የሚያሳይ በመሆኑና ለሀብታም ሰው ብቻ ሳይሆን በኑሮ ደረጃ ዝቀተኛ ለሆኑ ሰዎች ቤት መስራት በደምብ የሚያዋጣ በመሆኑ ፍሊንትስቶን ሆምስ ከዚሁ የኮንዲሚኒየም ገበያ በመነሳትና የራሱን ቢዝነስ ሞዴል በመከተል የሪል እስቴት ቢዝነሱን ሰርቷል:: የቤትን ዋጋ ማውረድ በጣም አትራፊ መሆኑን በመገንዘብም በመጀመሪያ ዙር በሰራቸው ቤቶች ላይ ይህንኑ ሞዴል
ተግብሮታል::
ይሁንና ከዚህ በኋላ የመሬት የኮንስትራክሽን ግብአት ገበያው በሰዎች ቁጥጥር ስር ማለትም በሙስናና በተደራጀ የገበያ ቁጥጥር ስር እየዋለ መጣ:: የተወሰኑ ስልጣን ያላቸው አካላትና ባለሃብቶች በሚያደርጉት የጣምራ እንቅስቃሴ ገበያውን ሲቆጣጠሩት ፍሊንትስቶን ሆምስ ቀደም ሲል ለአዋጭነት አቅርቦት የቀረፀው የቢዝነስ ሞዴል የግንባታ ግብአቱ በመወደዱ አዋጭ ሊሆን እንደማይችል ተረዳ::
የህብረተሰቡ ገቢም ውስን ከሆነና የግንባታውም ግብአት እየጨመረ ከመጣ ይህን መቋቋም የሚችል ገበያ ስለማይኖር የሪል እስቴት ቢዝነሱ ይቆማል:: ፍሊንትስቶን ሆምስም ከአራት አመታት በፊት ገበያው ሲዛባ የገጠመው ይኸው ነው:: እነዚህ ነገሮች በሚፈጠሩበት ግዜ አዋጭ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ቤቶች የማያዋጡበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ:: በዚህም ምክንያት ፍሊንትስቶን ሆምስ የቤት ሽያጩን በማቆም ስራውን በዝግታ መስራት ጀምሯል::
በመቀጠልም የግንባታ ግብአት ዋጋ መጨመርን ደምበኛው መሸከም የለበትም በሚል አዲስ ሃሳብ በማምጣት ዋጋ እንዳይጨምር በተለይ መንግስት የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎች፣ በብልሹ አሰራሮች የሚጨምሩ ዋጋዎችንና የውጪ ምንዛሬ ምደባን በተመለከተ መታገሉን ዋነኛ ስራ አድርጓል:: የዛሬ አምስት አመት ከነበረው አኳያ በአሁኑ ወቅት ለደምበኞች የሚተላለፉ ቤቶች ዋጋም በእጥፍ ጨምሯል:: ይሁንና ‹‹ከሌሎች ተፎካካሪ የሪል እስቴት ካምፓኒዎች ጋር ሲነፃፀር ግማሽ ያህል ነው›› ይላሉ ኢንጂነር ፀደቀ::
እንደ እርሳቸው ገለፃ፤ በየቤቱ ያሉ ደምበኞች በማህበር ሲደራጁ የሪል እስቴት ካምፓኒው ቤቱን ገንብቶ ማጠናቀቅ ቢያቅተው በውሉ መሰረት ካምፓኒውን አባረው ቤታቸውን ይዘው መቀጠል ይችላሉ:: የሪል እስቴት ቢዝነስ ብዙ ግዜ የሚጎዳውም የሪልእስቴት ስራው ሲወድቅና ደምበኞች ንብረታቸውን ሲያጡ ነው::
የተደራጀ ማህበረሰብ ለአንድ ሪልእስቴት ቢዝነስ ከምንም በላይ ትልቁ መሰረት በመሆኑ ፍሊንትስቶን ሆምስም ይህን ሞዴል በዋናነት ይከታተላል:: በሪል እስቴት ህግ ውስጥ እንዲካተትም በተደጋጋሚ ለመንግስት ጥያቄ አቅርቦ ረቂቁ ገብቷል::
የሪልእስቴት ቢዝነስ ኢንቨስትመንት ዋነኛ ተግዳሮቶች የግንባታ ግብአት ዋጋ በየግዜው መጨመር፣ መንግስት በገበያው ወስጥ ጣልቃ መግባቱና የደምበኞች ቤት የመግዛት አቅም በመሆናቸው የድርጅቶችና በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ ተዋንያኖች አስተዋፅኦ እንዳለ ሆኖ እነዚህን ጉዳዮች አቀናጅቶ የመስራት ትለቁ ሃላፊነት የመንግስት ነው:: የዘርፉን ውስብስብነትና በውስጡ ያሉትን ዋና ዋና አካላት የመገንዘብ አቅም ያለው የመንግስት አመራርም ያስፈልጋል::
በዘርፉ ትልቁን ገንዘብ የሚያፈሰው መንግስት ከመሆኑ አኳያ ይህን ያህል ገንዘብ ለዘርፉ ከሚያጠፋ የሚያፈሰውን ገንዘብ በመቀነስ ለቅንጅት ቢያወጣና የሰው ሃብት ቢጨምር ዘርፉን ማሳደግ ይችላል:: የግል ሴክተሩን ለማንቀሳቀስ መንግስት የሚሰራው ስራ ምንድን ነው? የሚለውም ጉዳይ መታየት ይኖርበታል::
በሪል እስቴት ቢዝነስ ኢንቨስትመንት እየገጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች ልክ እንደ ሌሎቹ የሪል እስቴት ካምፓኒዎች ሁሉ ፊሊንትስቶን ሆምስንም የነኩ ቢሆንም ሰዎች በሰፈሩባቸው ቦታዎች ላይ ዘመናዊ ቤቶች ውስጥ እንዲኖሩ በማድረግ፣ ሰፈሮችን በመንግስት፣ በግልና በማህበረሰብ አጋርነት የማልማት ስልትን በመከተል ሰፈሮችን በማልማት ስኬታማ መሆን እንደሚቻል ተገንዝቧል::
በመንግስት በኩልም የተጎሳቆሉ መንደሮችንና 65 ሺህ ቤቶችን በዚህ ዘዴ ለማልማት እቅድ መያዙን ተረድቷል:: እነዚህኑ የዘርፉን ተግዳሮቶችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድና የራሱን የቢዝነስ ሞዴል በመጠቀም የሪል እስቴት ስራውን በማከናወን ላይ ይገኛል::
ለዚህም በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ ሰፈሮች ውስጥ በመግባት የሰፈሮቹን አመራር በወረዳው ሱፐርቪዥን፣ የሰፈሩን ነዋሪ፣ ፍሊንትስቶን እና በሰፈር ውስጥ ያሉ የመሬት ባለቤቶች /መንግስትና ባለሃብቶችን/ አንድ ላይ በማድረግና ፕሮፖዛል በማቅረብ ዘመናዊ ቤቶችን ይገነባል:: በቅድሚያም ባለሃብቶች የነበራቸውን የመሬት ይዞታ ወደተገነባ ነገር እንዲቀየር ያደረጋል:: የልማት ተነሺዎችም እንዳይፈናቀሉ በማድረግ
በድጎማ የሚኖሩበት ቤት ውስጥ እንዲገቡ ያደረጋል:: እንዲህ አይነቱ ስራ በየሰፈሩ ሲሰራ መጠኑ እየጨመረ ስለሚመጣና ሰፊ ቦታ ስለሚፈጠር መሸጥ የሚችልና ለፍሊንትስቶን ሆምስ ትርፍ ሊሆን የሚችልና ለባለሃብቶቹም ሀብት የሚሆን ነገር ይፈጠራል::
በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት የሚፈጠረውን ክፍት ቦታ ለጋራ መኖሪያ መስሪያነት ባዘጋጃቸው ቦታዎች ላይ የሚፈናቀሉ ሰዎችን እዛው ቤት እንዲያገኙ ለማድረግ ያስችለዋል:: ወረዳዎችም ከፓርኪንግ ኪራይና ከልዩ ልዩ አገልግሎት የሚያገኟቸው ገቢዎች እያደጉ ይመጣሉ:: እነዚህንም ሞዴሎች ፍሊንትስቶን ሰርቶ ለመንግስት አቅርቧል::
እንደ ኢንጂነር ፀደቀ ገለጻ፤ እነዚህን የሪል እስቴት ቢዝነስ ፈተናዎችን ለማለፍ የመንግስትን ፖለቲካዊ ውሳኔ ይጠይቃል:: በዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ ሁሉንም በማቻቻል ለመኖር የሚያስችል የፖለቲካ ኢኮኖሚ ማእቀፍ ማምጣት የማይቻል ከሆነና የግል በለሃብቱንም በዚህ ላይ እገዛ እንዲያደርግ ካልተደረገ በምርጫም ማሸነፍ አይቻልም:: በመሆኑም በቅድሚያ የግል ባለሃብቱን በሪልእስቴት ኢንቨስትመንት ውስጥ ሚናውን ህዝባዊ ለማድረግ የፖለቲካ ስርዓቱን ማስተካከል ያስፈልጋል::
ነፃ ገበያ ለፀረዲሞክራሲ አይመችም:: ስለሆነም አንድ መንግስት ዲሞክራሲ ስርዓትን ይዞ እስከተነሳ ድረስ ኢኮኖሚውንም እውነተኛ ነፃ ገበያ እና ፍትሃዊ ሊያደርገው ይገባል:: የሆነው ሆኖ ግን በሪልእስቴት ዘርፍ እየታዩ ያሉ ተግዳሮቶች ፍሊንትስቶንን ይበልጥ እንዲሰራና ተፈላጊ እንዲሆን አድርጎታል::
በአሁኑ ወቅት መኖሪያ ቤት የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥርና የሪልእስቴት ካምፓኒዎች የሚያቀርቧቸው ቤቶች ቁጥር በፍፁም የሚመጣጠኑ አይደሉም:: በአገር አቀፍ ደረጃም አዲስ አበባ መጥቶ ቤት የሚፈልገው ሰው ቁጥርም በጣም ከፍተኛ ነው:: ለአብነት እንኳን ፍሊንትስቶን የሚሰራቸውን ቤቶች የሚፈልግ ሰው ቁጥር አንድ ሚሊዮን ይሆናል ተብሎ ይገመታል:: ለዚህ ሁሉ ቤት ፈላጊ ቤቶችን ማቅረብም ይቻላል:: በዛው ልክም ቤቱን የመግዛት አቅም ያላቸው ሰዎችም ቁጥር ከፍተኛ ነው:: ይሁን እንጂ ቤቱ ስለመኖሩና እንዴት ሊኖርበት እንደሚችል የሚያውቀው ሰው ቁጥር አጠያያቂ ነው::
ፍሊንትስቶን በቀጣይ በሁሉም ክልሎች ያሉ ሰዎች በካሬ ሜትር 20 ሺ ብር የሚሸጡ ቤቶችን አዲስ አበባ ላይ መግዛት እንደሚችሉ ለማድረግ ይሰራል:: አስካሁንም 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ፍላጎት አሳይተዋል:: ባለ ሁለት መኝታ ቤት በ900 ሺ ብር በአሁኑ ወቅት እያዘጋጀ ይገኛል:: ይህም በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ያሉ አርሶ አደሮች ሊገዙት የሚችልና አዲስ አባባ ላይ ንብረት መያዝ የሚያስችላቸው ይሆናል::
ይሁን እንጂ ትልቁ ፈተና ሊሆን የሚችለው በሩቅ ያሉ ሰዎች አዲስ አበባ ላይ ያላቸውን ንብረት ለማስተዳደር ምን ያህል ይቻላቸዋል የሚለው ነው:: ለዚህም የንብረት ይዞታ ማረጋገጥ መብት አዋጆች አሁን ካሉት የተሻሉ መሆን ይኖርባቸዋል:: በቀጣይም በኢትዮጵያ ውስጥና ከኢትዮጵያ ውጪ ያለ ማንኛውም ሰው በንብረቱ ላይ ያለው መብት በመንግስት እንደሚከበር የሚያረጋግጥ ስርዓት እየዳበረ በሄደ ቁጥር ካምፓኒው የትም ቦታ በመሄድ ቤትን መሸጥ ያስችለዋል::
የመኖሪያ ቤት ፍላጎት በአዲስ አበባ ከግዜ ወደ ግዜ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱ ይታወቃል:: መንግስትም ይህንኑ ፍላጎት ለማርካታ የተለያዩ የጋራ መኖሪያ ቤት ፕሮግራሞችን በመጀመር ለተጠቃሚዎች በማስተላለፍ ላይ ይገኛል:: ይሁን እንጂ አሁንም እያደገ የመጣውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት በዚህ ብቻ መፍታት አልቻለም::
ከፍተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ለመኖሪያ ቤት ፍላጎት ሁነኛ አማራጭ ሊሆኑ የሚችሉት ፍሊንትስቶን ሆምስን የመሰሉ የሪል እስቴት ካምፓኒዎች ናቸውና የጀመሯቸውን ስራዎች በስፋት አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ይጠበቃል:: በዚህ ዘርፍ መግባት ለሚፈልጉ አዳዲስ ባለሃብቶችም መንግስት ተገቢውን ማበረታቻ ሊሰጣቸው ይገባል:: እኛም ፍሊንትስቶን የጀመራቸው ስራዎች ከግብ ደርሰው የከተማዋን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እንዲቀርፉ ምኞታችን ነው:: ሰላም!
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 27/2012
አስናቀ ፀጋዬ
ለተግዳሮቱ ብልሃት ያበጀው የፍሊንትስቶን ሆምስ ሪልእስቴት ኩባንያ