የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በክፍል ሁለት አንቀጽ ሰላሳ አምስት ሴቶች ሊጠበቁላቸው የሚገቡ መብቶቻቸውንና ሊያገኟቸው ስለሚገቡ ጥቅሞች በዝርዝር ያስቀመጠ ቢሆንም ዛሬም ድረስ በተለያዩ ምክንያቶች የአተገባበሩ ነገር እንደ ሀገር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በአንጻሩ አብዛኛው የቤተሰብ ኃላፊነትና ሸክም የሚያርፈው ደግሞ በሴቶች በተለይም እናቶች ጫንቃ ላይ ሆኖ ይገኛል። በመሆኑም በመንግስትና በሚመለከታቸው አካላት ለሴቶች አስፈላጊውን ጥበቃና ከለላ በማድረግ ቤተሰብን ብሎም ማህበረሰብንና ሀገርን ከችግር መታደግ እንደሚገባ የሴታዊት እኩልነት መስራችና አስተባባሪ ስሂን ተፈራ (ፒኤችዲ) ይናገራሉ።
አስተባባሪዋ እንደሚያበራሩት የሴቶች ተሳትፎም ሆነ ተሰሚነትና ተጠቃሚነት በአንዳንድ ቦታዎች ለዚያውም ለጥቂቶች ብቻ እውነት ከመሆኑ ባለፈ ለብዙሃኗ ሴት መሬት የወረደ ተጨባጭ ለውጥ ዛሬም አልመጣም። ለዚህ ደግሞ የባህል ተጽእኖ፤ የማህበረሰቡ ንቃተ ህሊና አለመዳበር፤ ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠትና የወጡ ህጎችንም ተከታትሎ አለማስተግበር ከምክንያቶቹ መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው።
በኢትዮጵያ የሴቶች የስራ ድርሻ በከተማ አንዳንዶች ገቢ ለማግኘት ተቀጥረው ከሚሰሩት ባለፈ ቤት በማስተዳደር ምግብ በማብሰለና ልጆች ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል። በአሁኑ ወቅት በክፍያ የሚሰሩ ሴቶች ከ 40 በመቶ በታች ሲሆኑ ይህም ሆኖ በቀን እስከ አስራ ስድስት ሰዓት እንደሚሰሩ የወንዶች ግን ከስምንት ሰዓት የዘለለ እንዳልሆነ ዩኒሴፍ ያስጠናው ጥናት ያመላክታል። በገጠሩ አካባቢ ደግሞ ሌሊት ተነስቶ ውሃ መቅዳት ለቤተሰቡ ምግብ ማዘጋጀት በየእለቱም ባይሆን ልብስ አጠባ ማገዶ ለቀማው እንደተጠበቀ ሆኖ ከእርሻ ስራውም አረምና ጉልጓሎ የመሳሰለው በአብዛኛው የሚከወነው በእነሱ ነው። እነዚህን ስራዎች ሲያከናውኑ እርግዝና ላይ ሆነው ከዛም በኋላ ልጅ አዝለውና እየጠበቁ መሆኑ ደግሞ የእነሱን ሸክምና ኃላፊነት ድርብ ድርብርብ ያደርገዋል።
በሌላ በኩል የገቢ ምንጩ ላይ እነሱ አስተዋጽኦ ኖራቸውም አልኖራቸው አጠቃቀሙ ላይ ውሳኔ በመስጠቱ ረገድ የሚኖራቸው ድርሻ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ በቤተሰብ ውስጥ የታዘዙትን የተለመደ የጉልበት ስራ ከመስራት የዘለለ ድርሻ ሲኖራቸው አይታይም። አንዳንዶች ውሳኔ እንዲሰጡ እድል የሚሰጧቸው ቢኖሩም ብልሀት አላቸው ብለው ስለሚያምኑ ብቻ ነው። ነገር ግን ሴቶች በውሳኔ ሰጪነት መሳተፍ ሀሳባቸው መደመጥ ያለበት የተለየ ብልሀት ወይንም ጥበብ አላቸው በሚል እሳቤ ብቻ ሳይሆን ሴቶች የሚያመጡት ለውጥ እንደተጠበቀ ሆኖ የመብት ጉዳይ እንደሆነም መታወቅ አለበት። ይህ አይነቱ ችግር በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በበርካታ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት በስፋት የሚስተዋል በመሆኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ከሴቶች ሊያገኙ የሚችሉትን ዘርፈ ብዙ ጥቅም በየወሩ እያጡ ይገኛሉ። እንደ ምሳሌ አሁን የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ብንመለከት በመከላከል ረገድ ጥሩ ለውጥ እያሳዩ ካሉ ሀገራት መካከል እንደ ጀርመን ኒውዝላንድ ያሉት የሴቶች እኩልነት የሰፈነባቸው፤ የሴቶች ተሳትፎ ከፍ ያለባቸውና በሴቶች የሚመሩ ሆነው እናገኛቸዋለን።
ሴቶችን ተጠቃሚ በማድረግና መብታቸውን በማስጠበቅ ረገድ አሁን አሁን መንግስትና አንዳንድ ግብረ ሰናይ ደርጅቶች በተለያየ መልኩ ማስተማርን ጨምሮ እየተሰሩ በመሆኑ እንዳንድ ወላጆችም ተምረው ለውጥ ያመጡትን በማየት ለሴት ልጆች ትኩረት እየሰጡ ይገኛሉ።ቢሆንም ከሚጠበቀው አንጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በኢትዮጵያ ሴቶች ከሚገጥሟቸው ችግሮች መካከልም አስካሁንም በቂ ለውጥ ማስመዝገብ ካልተቻለባቸው ጕዳዮች መካከል በልጅነት መዳር ቀዳሚው ነው። መንግስት ያለእድሜ ጋብቻን በህግ ከማስቀመጥ አልፎ በተለያዩ መንገዶች ለማስተማርም ለመቆጣጠርም እየሰራ ቢሆንም ዛሬም ድረስ በርካታ ልጆች በተለይ በገጠር አካባቢ በልጅነታቸው በአስራ አንድና አስራ ሁለት አመታቸው እየተዳሩ ይገኛል። በተጨማሪ ከጎጂ
ልማዳዊ ድርጊቶችም መካካል በየአመቱ ከሚወለዱት ሴቶች ከስልሳ አምስት እስከ ሰባ አምስት በመቶ ግርዛት እየተፈጸመባቸው ይገኛል። እነዚህ ሁሉ የሚያመላክቱት ሴቶችን በማብቃቱም ሆነ በመጠበቁ ረገድ እየተሰሩ ያሉት ስራዎች በቂ አለመሆናቸውን ነው።
በሴቶች ላይ ሲሰራ ግን ያገቡትን ወይንም እናቶችን ብቻ ትኩረት አድርጎ ሳይሆን ሴት ልጆችንም ጨምሮ መሆን አለበት የሚሉት ዶክተር ስሂን፤ በቤተሰብ ውስጥ የወንድ የበላይነት አባት ላይ ብቻ የሚቀር አይደለም፤ ወደ ወንድምም ባልም የሚሸጋገር ይሆናል። በገጠርም በከተማም በስፋት እንደምንመለከተው ሴት ልጆች ከወንዶቹ እኩል ትምህረት ቤት ገብተው እኩል አጥንተው የመማር እድሉ የላቸውም። እድሉን አግኝተው እኩል ትምህርት ቤት ቢውሉ እንኳ እቤት ሲገቡ ሴቷ ምግብ እንድታቀርብና ሌሎች ስራዎችን እንድትሰራ መደረጉ የተለመደ ግን የተሳሳተ ተግባር ሆኖ እናገኘዋለን። ከቤት ለመውጣትም ለወንድ በፈለገበት ሰዓት እንዲንቀሳቀስ ሲፈቀድ ለሴት ልጅ ነውር ተደርጎ ይወሰዳል በቤተሰብ ወስጥ አንዳች የገንዘብ አልያም ሌላ ችግር ገጥሞ አንዳቸው ትምህርታቸውን ማቋረጥ ወይንም መቅረት ቢጠበቅባቸው ቀዳሚ የምትደረገው ሴቷ ናት። ይሄ ደግሞ የሚደረገው ተምራ የትደርሳለች? ብትማርም አግብታ ወልዳ ነገ ለሌላ ሰው ነው የምታገለግለው፤ ከሚል እንደ ማህበረሰብም እንደ ግለሰብም ከተያዘ የተሳሳተ አመለካካት ነው።
ሴቶችን በማብቃት ረገድ ትምህርት ጥቅም እንዳለው ቢታመንም ችግሩን ለመቅረፍ ግን የመደበኛ ትምህርት መስፋፋት ብቻውን መፍትሄ ሊሆን አይቸልም። ይህም ሆኖ በመደበኛው ትምህርት አንደኛ ክፍል ሲገቡ በእኩል ቁጥር ሊገቡ ቢችሉም ከፍ እያሉ ሲሄዱ ግን ቁጥራቸውም ተሳትፏቸውም እየቀነሰ ይመጣል።በተለይ ከከተማ ውጪ ከአምስተኛና ስድስተኛ ክፍል ሲዘሉ አይታይም። በዚህ እድሚያቸው የወር አበባ የሚያዩበትው ወቅት በመሆኑ ተምራ ምን ትሰራለች ከሚለው የቤተሰብ አመለካከት ባለፈ ወላጆች እንዳይጠለፉባቸውም በመስጋት ከትምህርታቸው ያሰናክሏቸዋል። እድሉን አግኝተው ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱትም በትምህርት ቤትም በተማሪዎችም ሆነ በመምህራን
የሚፈጸሙባቸው ትንኮሳዎች ስለሚኖሩ ከዚህ እድሜ በኋላ ሴቶቹ ለመማር ምቹ ሁኔታ አይኖራቸም። አንዳንዶች ከዚህ የክፍል ደረጃ ተሻግረው ስድስትኛም ሰባተኛም ክፍል ሲደርሱ ቢታዩም ከስምንተኛ ክፍል አልፈው ሁለተኛ ደረጃ የመግባት እድል የነበራቸው እስከ ባለፈው ዓመት ድረስ ሰላሳ በመቶ ብቻ ናቸው። ወደ ዩኒቨርስቲዎች የሚገቡትም ባለፈው ዓመት ብቻ በአዲሷ ሚኒስትር ወሳኝነት የመግቢያ ቁጥሩ ዝቅ በማለቱ አርባ በመቶ ከመደረጉ በፊት ከሰላሳ በመቶ ዘሎ አያውቅም። በመሆኑም በአንድ ወገን መብታቸውን ለማስጠበቅ ችግራቸውን በመቅረፍ የትምህርት ተደራሽነቱ ራሱ አጠያያቂ ሲሆን በሌላ በኩል እኩልነትንና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ የትምህርቱ ጥራትና የሚያስከትለውም ውጤት በቂ አለመሆኑ ራሱን የቻለ አንድ ችግር ሆኖባቸዋል።
ሴቶች በትምህርት አንድ ክፍል በመጨመራቸው የሚያተርፉት ብዙ ነገር አለ።ለምሳሌ ከሀገር ሊወጡ ቢፈልጉ በአሁኑ ወቅት ስምንተኛ ክፍል ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል።ይሄ ለመስፈርቱ ብቻ ሳይሆን ሲሄዱም የተሻለ ንቃተ ህሊና እንዲኖራቸውም የሚረዳ ነው። ብዙ ልጆችን የሚወልዱ ያልተማሩ ሴቶች ናቸው ትምህርት የቀጠሉት።የሚወልዷቸው ልጆች ቁጥር ይቀንሳል።ይሄ ለልጆችም ለእነሱም ጤና ጥሩ ነው። በኢትዮጵያ ካሉ ክልሎች የሴቶች የትምህረት ተሳትፎ ዝቅተኛ የሆነበት ክልል ሶማልያ ነው።ሴቶች በልጅነታቸው በርካታ ልጆችንም የሚወልዱት በዚሁ ክልል ነው፤ በአንጻሩ በርካታ የተማሩ ሴቶች ያሉት በአዲስ አበባ ነው።በአዲስ አበባም የወሊድ ቁጥሩ ዝቅተኛ ነው። የህዝብ ብዛት ጥቅም የሚኖረው የተማረና ሰራተኛ ትውልድ ሲኖር ነው።ለዚህ ደግሞ የሴቶች በሁለንተናዊ መስክ መጠናከር ወሳኝ ነው።
በአንድ ወቅት የወርልድ ባንክ ያወጣው ጥናት እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ ያሉ ሴቶች ላይ በሙሉ ኢንቨስት በማድረግ ማስተማር ቢቻል ዩኒቨርስቲ ሳይገቡ እንኳን እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ድረስ ቢማሩ አራት ቢሊየን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደሚያስችል ያሳያል። ይህ ማለት ሀገሪቱ በእርዳታ ከምታገኘው ገንዘብ ጋር የሚስተካከል ነው። ሁሉንም ሴቶች በማስተማር የተገመተውን ያህል ገቢ ማግኘት ባይቻል እንኳ አሁን ካለንበት ደረጃ አንጻር ብዙ መስራት እንደሚጠበቅና ብዙ እንዳልተሰራ ነገር
ግን ሊሰራ እንደሚችል አመላካች ነው።
የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግና በማንቃት በኩል ላለው ክፍተት ግን ራሳቸውን ሴቶችን ጨምሮ የሁሉም አካላት ተጠያቂነት አለበት። በሴቶች በኩል በተለያየ አጋጣሚ እድሉን አግኝተው የተማሩ ሴቶች ሴት ልጆቻቸውን በጥሩ ሁኔታ ሊያሳድጉ፤ ሊንከባከቡም ይችላሉ።ነገር ግን ከዛ አልፈው ዘመድ አዝማድ ቤተሰብ አልያም ሰፈር ውስጥ በመድረስ ሴት ልጆችን ለማብቃት ሲሰሩ አይታይም። በግልባጩ ከዘመድም ሆነ ከገጠር የሚያመጧቸውን ሴት ልጆች እንደሰራተኛ ሳያስተምሩ በጫና ውስጥ ሲያስቀምጡ ይታያሉ። የሚያስተምሩ ቢኖሩም በስርአት እንዲያጠኑ ጊዜ ሰጥተው ሲያኖሯቸው አይታይም። አንዳንዶቹ እንዲያውም በሀገሪቱ ህግ አስራ አራት ዓመት ሳይሞላቸውን ልጆች ስራ መቅጠር የተከለከለ ቢሆንም ከዛ ያነሱትንም ሲያሰሩ ማየት የተለመደ ነው።
በህግ በኩልም ከፍተኛ ክፍት አለ ፖሊሶች ተደፍረው የመጡ ሴቶችን ሳይቀር በራስሽ ጥፋት ነው ሲሉና ሲያመናጭቁ ይታያል። ከዚህ አልፎ ጉዳያቸው ፍርድ ቤት የሚደርስላቸው ቢኖሩም በስርአት ምስክሮችና መረጃዎችን የሚያጠናቅርላቸው ባለመኖሩ ፍትህ ሳያገኙ የሚቀሩት በርካቶች ናቸው።
በመሆኑም በአንድ በኩል ህጎች ስለማይተገበሩ ንቅንቄ በማካሄድ በወረቀት የሰፈረው ህግ ወደ ተግባር እንዲገባ ስር ነቀል የሆነ ለውጥ በማምጣት መሰረታዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መንቀሳቀስ ይጠበቃል። ሴቶችን በተመለከተ እንደ ማህበረሰብም እንደ ግለሰብም
በሁሉም ረገድ በመስራት ውጤቱ ለዛሬው ባይሆንም ለመጪው ትውልድ እንደሚተርፍ በማመን ለዲሞክራሲ እንደምንታገለው አይነት የማያቋርጥ የትውልድ ቅብብሎሽ ያለበት ሂደት ይስፈልጋል። የዚህ አይነት አካሄድ በዲሞክራሲው ረገድ በህንድ ሀገር ብዙ ስራ ስለተሰራ ምንም የሌላቸው ድሃ የተባሉት ሳይቀር ጉዳያቸው ሆኖ በምርጫ ሲሳተፉ እናያለን። አሁን ለእኔ ምን ያደርግልኛል ኢኮኖሚዬ ሲዳብር እሳተፋለሁ አይሉም።በተመሳሳይ እዚህም ሁሉም ሴቶች መብታቸውን ለማወቅ ብሎም ለማስከበር የሚሰሩ መሆን አለባቸው።
በከተማ እስከ ወረዳ በገጠር እስከ ቀበሌና ጎጥ የሴቶችን ጉዳይ የሚመለከት ቢሮ ተቋቁሟል። በበቂ ሁኔታ የሴቶችን ጉዳይ እያዩ ግን አይደለም።የተዋቀሩት በፖለቲካ ፓርቲና አመለካካት ጋር በተያያዘ ነው። በዚህም የተነሳ የስነ ጾታ ትምህርት ያላቸውም ጥቂቶች ናቸው። በጀትና ከሚሰጣቸው ድጋፍ አልፈው የሚሰሩም ቢኖሩም አብዛኛዎቹ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ አይደለም። መዋቅሩ የመንግስት በመሆኑና የመንግስትን ሚና ተክቶ የሚሰራ ባለመኖሩ አዲሷ ሚኒስትር በሰጡት ተስፋ መሰረት ከመንግስት ብዙ መስራት ይጠበቃል።
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አፋጣኝ ጉዳዮች ሲገጥሙ የተለየ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ከመንግስትና ከሚመለከታቸው አካላት የሚጠበቅ ይሆናል። ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት ከኮቪድ 19 የኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ምንም እንኳ ለቫይረሱ ያለው ተጋላጭነት ለሁለቱም እኩል ቢሆንም የበለጠ ተጎጂ የሚሆኑት ግን ሴቶች ናቸው። በሀገራችንም ለመከላከል የሚሰራው ስራ አብዛኛው ለሴት የተውት የጽዳት ሰራ፤ ነርስነትና የመሳሰሉት ናቸው በቤት ውስጥም ሆነ በሆስፒታል በመንከባከብ ስራም የሚሳተፉት አብዛኛዎቹ ሴቶች ናቸው። በተጨማሪ በኢኮኖሚም ረገድ እንደ ቤተሰብ ካለው ገቢ ሲጎድል የሚመለከተው ሴቶችን ነው። በአንድ ወገን ስራ የሚሰሩም ከሆነ እንደፈለጉ ተሯሩጠው መስራት የሚችሉበት ሁኔታ የለም በሌላ በኩል የዋጋ ጭማሪም ሲኖር ብስፋት ምግብ ነክ ነገሮች ላይ በመሆኑ ችግሩ እነሱኑ የሚመለከት ይሆናል። በትምህርት ቤት ይመገቡ የነበሩ ልጆች ቤት በመዋላቸው ወላጆች ያንን ተማምነው እቅድም ስላለነበራቸው ለአንዳንዶች ሌላ ችግር ይሆንባቸዋል። በእርግጥ በመንግስት በኩል የተወሰዱት ከስራ ያለመባረርና ቤት ያለመልቀቅ ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ያለማድረግ ውሳኔዎችና የህብረተሰቡ የመረዳዳት ተግባር ለሴቶች እፎይታን የሚሰጡ በመሆናቸው ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መሰራት አለበት በማለት አሳስበዋል።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 23/2012
ራስወርቅ ሙሉጌታ
ተግባራዊ ለውጥ የሚሻው የሴቶች ተጠቃሚነት