በሀገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ታሪክ አንድ ምእተ አመት አይሞላውም። የመጀመሪያው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (የያኔው UCAA) በ1950 (እኤአ) ከመከፈቱ በፊት በዚህ ደረጃ የሚጠቀሱ ምንም አይነት ተቋማት አልነበሩም።
የመጀመሪያው ትውልድ የሆነውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተከትሎ አገራችን የበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ባለቤት የሆነች ሲሆን አሁን የአራተኛው ትውልድ አባል የሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ባለቤት ለመሆን በቅታለች።
እንደሚታወቀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አላማ በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ ባለሙያ ምሁራንን ማፍራት ነው። ከኮሌጆች ጀምሮ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ የሚሰጡ ተቋማትና ልዩ ስልጠናን የሚያቀርቡ የማህረሰብ ኮሌጆች (Community college) ድረስ ያሉ አላማቸው ይኸው ሲሆን በጥናትና ምርምር አገርንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ማገልገልም የዚሁ አካልና ተነጥሎ የማይታይ ነው።
ይህን መነሻ ይዘን በእነዚህ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምን ምን አይነት የጥናት መስኮችና የሙያ ዘርፎች ይስተናገዱባቸዋል? የሚል ጥያቄን ብናነሳ የሚቀየም የለም። በመሆኑም ጥያቄውን አንስተን መልሱን “ስንገምት” ሊሆን የሚችለው የትምህርትም ሆኑ የጥናት መስኮች ሲከፈቱ የመጀመሪያው ትኩረታቸው አገርና ተቋሙ የተከፈተበት አካባቢ መሆኑን ነው። በመሆኑም አለም አቀፍ ሁኔታዎችን ስንፈትሽም ባብዛኛው የምናገኘው ይህንኑ ነው።
አገራት የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይኑሯቸው እንጂ የሚያስፈልጓቸው የሙያ መስኮች ሁሉ አሏቸው፤ የሚፈልጓቸው ምሁራን ሁሉ የሚፈልቁባቸው ናቸው ማለት ግን አይደለም። ለምሳሌ በአገራችን ወደ 50 የሚጠጉ (ኮሌጆችንና በመገንባት ላይ ያሉትን ዩኒቨርሲቲዎች ሳይጨምር) የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አሉ። ከነችግሮቻቸውም ቢሆን የግሎቹም ቁጥር ቀላል አይደለም። የሁሉም ተደምሮ እንደ አገር ሲታዩ ቁጥሮቻቸው ይብዙ እንጂ ከተፈላጊ ጥናት መስኮች አኳያ የላቁ ናቸው ለማለት አያስደፍሩም። እንቅስቃሴዎቻቸው ሁሉ የፉክክር፤ ተግባራቸው ሁሉ ተደጋጋፊ ሳይሆን ተደጋጋሚ ሆኖ ነው የሚታየው። ከህንፃ አሰራራቸው ጀምሮ ተመሳሳይ፤ ከዲፓርትመንት አከፋፈታቸው ጀምሮ አንድ አይነት፤ ከትኩረት አንፃርም አንድ አቅጣጫ ሆነው ነው የሚታዩት። ይህ ደግሞ በየትኛውም ዘመናዊ መስፈርትና መመዘኛ ቢታይ ስህተት እንጂ አዋጭ ሆኖ አይገኝም። ለማለት
የፈለግነው ለአገሪቷ የሚያስፈልጓት የጥናት መስኮች ሁሉ ይሰጡባቸዋል፤ የሚያስፈልጓት ባለሙያዎች ሁሉ ይፈልቁባቸዋል ማለት አይቻልም ነው። ለዚህ ደግሞ ማሳያችን በርእሳችን የጠቀስነው፤ በ1971 በኤ.ጄ. ዌበርማን የተፈጠረው፤ በ1885 የተቋቋመውን ዩኒቨርሲቲ ኦፍ አሪዞናን የተቀላቀለው “ጋርቦሎጂ” ነው። ለመሆኑ “ጋርቦሎጂ” ምንድን ነው??
ጋርቦሎጂ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስከሶስተኛ ዲግሪ ድረስ የሚሰጥ አንድ የትምህርት አይነት/ጥናት መስክ ሲሆን፤ የስነ-ምድር ቁፋሮ ማካሄድ (archaeological excavation of landfills)፣ አዳዲስ የቆሻሻ ክምችቶችን ማጥናትና የሚያስከትሉት አደጋ ወይም የሚያስገኙት ጥቅም መኖር አለመኖሩን መፈተሽ፣ የከርሰ ምድር ውሀንና ሌሎች የውሀና አካላትን (ውቅያኖሶችን) መለየትና መከላከል፣ ብክለቱ ድርቅና ረሃብ ስለ ማስከተልና አለማስከተሉ፣ የቆሻሻን መጠንን ማወቅና ማስተዳደር፤ በማዳበሪያንት መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል፣ ከአንድ አካባቢ ከሚገኙ ነዋሪዎች ስለሚመነጩ ቆሻሻዎች፣ ከቆሻሻው ክምር መንጭቶ ወደ መሬት የሚገባው ፈሳሽ (leachate) መርዛማ መሆንና አለመሆኑን መለየት፣ የህብረተሰቡን ባህል (በተለይ) ከቅድመና ድህረ ዘመናዊነት የአኗኗር ዘይቤ አኳያ ማጥናት፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ስለቆሻሻዎቹ ስላለው ግንዛቤና መሰረታዊ እውቀት፣ በአካባቢው ያሉ ሀላፊዎች/ባለ ስልጣናት ስለጉዳዩ ያላቸውን ግንዛቤ በተመለከተና ስለሚያሳልፏቸው ውሳኔዎች መለየት ወዘተ ነው። በተገኘው ውጤት መሰረትም መፍትሄዎችን በማፈላለግ ተግባራዊ ማድረግና ችግሮች እንዳይከሰቱ ከወዲሁ መከላከል መቻል ነው።
በመዲናችን አአ በተለምዶ “ቆሼ ሰፈር” የደረሰብን አደጋ የእነዚህ ሁሉና ሌሎች ክምችቶች መሆኑ በወቅቱ የተነገረ ሲሆን ጉዳዩን ለመረዳት እንኳን አገራችን ካላት የአቅምና የተማረ የሰው ሀይል ማነስ ምክንያት ምን ያህል ከባድ፤ ተገቢ የሆኑትን ካልሆኑት ለይቶ እርምጃዎችን እንኳን ለመውሰድ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደነበር ይታወሳል። ምን ላይ እንደደረሰ ባይታወቅም አአ ዩኒቨርሲቲም ጉዳዩን ሊመረምር ሀላፊነቱን መውሰዱ (ለመሆኑ እሱ ራሱ የ”Garbology” የትምህርት ዘርፍን ይሰጣል?) ይታወሳል።
ይህንን ተግባራዊ በማድረግና ውጤታማ በመሆን በኩል የበርካታ አገራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተጠቃሾች ሲሆኑ በWilliam Rathje ሲመራ የነበረው የአሪዞና ዩኒቨርሲቲው (Tucson) የ1973ቱ እና 1987ቱ “Garbage Project” በቀዳሚ ምሳሌነት ተጠቃሽ ሲሆን፤ በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት ተመስርቶ ወደ ስራ በመግባት ውጤታማ የሆነው፤ በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዋሺንግተን ተማሪዎች የተጀመረውና በስነ-ምድር ምርምር ጥናት (archaeology)፣ ዘመናዊ ባህል (mod¬ern culture) እና ቆሻሻ (waste ) መካከል ያለውን ማእከላዊ ቦታ (intersections) ከቆሻሻ አመራር ( waste management) አኳያ ማስገንዘብ ላይ አተኩሮ የሰራው “The UW Garbology Project (UWGP)” ነው።
ከላይ የጠቀስነው የ”ቆሼ ሰፈር” አደጋና ያስከተለው እልቂት የተከሰተበት ስፍራ ከዋናው ከተማ እምብርት ያለው እርቀትና በወቅቱ የነበረውን የሕዝብ ብዛት ግምት ውስጥ በማስገባት ከ50 ዓመት በፊት ለቆሻሻ መቅበሪያነት (landfill) ተመርጦ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን፤ ዛሬ ከግማሽ ምዕተ ዓመት አገልግሎት በኋላ በስፍራው የተከማቸው ቆሻሻ 36 ሄክታር ስፋት ያለውን ቦታ ሸፍኖ 13 ሜትር ያህል ተቆልሎ፤ (ከክምሩ ስር 40 ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ ውስጥ ተቀብሮ ያለውን ቆሻሻ ሳይጨምር)፤ በየዓመት 300ሺህ ቶን የሚጠጋ ቆሻሻ እየተደፋበት ከግማሽ ምእተ አመት በላይ አስቆጥሮ ይሄው ከሶስት አመት በፊት በድንገት ለመደርመስና በነዋሪዎች ህይወትና ንብረት ላይ አደጋን አድርሶ ሄደ። አሁን የዚህ ፅሁፍ ጥያቄ ይህ አደጋ ተመልሶ እንዳይመጣ ምን ይደረግ? የሚለው ሲሆን መልሱንም እዚሁ “ሳይውል ሳያድር የ’Garbology’ ጥናት መስክ ያስፈልገናል” በማለት መልሱን ይሰጣል። በተለይ በ2011 ዓ/ም የተገኘው መረጃ በአዲስ አበባችን ብቻ በአመት 18ሺህ 680 ቶን (አንድ ቶን 1000 ኪሎ ግራም ነው) ቆሻሻ ባናቷ እንደሚደፋባት ስናስብ የጥናት መስኩና መስኩ ያፈራቸው ባለሙያዎች (Garbagists እና Garbage anthropologists) አስፈላጊነት ብዥታን የሚፈጥር አይደለም። በአሁኑ ሰአት ሰውን እንደ ቅጠል እያረገፈ ያለውን ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ንም ለመቋቋም ዋናው ንፅህናን መጠበቅ መሆኑን ስናክልበት ደግሞ ጉዳዩን ያንረዋል።
በአለም ተጨባጭ ሁኔታ ስናጠቃልለው፤ አንድ ሰው (የEdward Humes “Garbology: Our Dirty Love Affair with Trash” መጽሐፍ እንደሚነግረን) በህይወት ዘመኑ 102 ቶን በአመት፤ በቀን 7.1 ፓውንድ (pounds) ቆሻሻን የሚጥል ሲሆን፤ ይህንንም ጥናቱ “የምንጥላቸው ፕላስቲክ ቆሻሻዎች ብቻ ከአሜሪካው ባህር ሀይል አጠቃላይ ክብደት የሚልቅ ሲሆን ይህም በመቶ ቢሊዮን ዶላሮች ወጪን እያስወጣን ይገኛል” ሲል አቻውን ያስቀምጥለታል። እውነቱ ይህ ከሆነ የጋርቦሎጂ አስፈላጊነት ጥያቄ እዚህ ግባ የሚባል አይደለምና በዚሁ እንለያይ።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 23/2012
ግርማ መንግሥቴ
ፍላጎቶቻችንና የጥናት መስኮቻችን አቅጣጫ