አገራችን በአንድ በኩል ለአመታት በተለያዩ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ወዲህና ወዲያ ሲናጥ የቆየ የፖለቲካ ስርዓት፣ በሌላ በኩል ደግሞ በዓለም አደባባይ ስማችንን ያጎደፈና በርካታ ዜጎችን ለጎስቋላ ኑሮ የዳረገ ድህነትና ኋላቀርነት ውስጥ ስትዳክር ቆይታለች።ባለፉት ሁለት ዓመታትም እነዚህን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በመፍታት ዘላቂና አስተማማኝ የፖለቲካ ስርዓት ለመፍጠር በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል።በተለይ በፖለቲካው መስክ የታየው ለውጥ ትልቅ እመርታ የታየበት እንደነበር ብዙዎች ይመሰክራሉ።
ይህንን ለውጥ ከዳር ለማድረስም በመጪው ነሐሴ እውነተኛና በህዝቦች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ በማካሄድ ዴሞክራሲያዊ ስርኣትን ለመገንባት መንግስት ቁርጠኛ አቋም በመያዝ ቀን ቆርጦ በመጠባበቅ ላይ እንደነበር ይታወቃል።ይሁን እንጂ “ሰው ያስባል፤ ፈጣሪ ይፈፅማል” እንደሚባለው የኮሮና ወረርሽኝ ይህንን እቅድ አሰናክሏል።
የኮሮና ወረርሽኝ የአገራችንን የምርጫ ሂደት ብቻ ሳይሆን መላው ዓለም ባሰበበት እንዳይውል ያደረገ ትልቅ የዘመኑ ክስተት ነው።ይህ ክስተት ምርጫን ቀርቶ የሰው ልጆች የእለት ተዕለት ህይወታቸውን በአግባቡ ለመምራት የሚያከናውኗቸውን እንቅስቃሴዎች በመገደብ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የፈጠረ አስከፊ የዘመኑ ስጋት ነው።ከዚህ አንጻር አሁን ያለው መሰረታዊ ጥያቄ ህዝባችን የከፋ ጉዳት ሳይደርስበት ይህንን ችግር እንዴት ልንሻገረው እንችላለን? የሚለው ነው።
ዛሬ ከዚህ አስከፊ ደዌ ለመሻገር ሁሉም እንደ አንድ ዜጋ ማሰብ የሚጠበቅበት ወቅት ነው።ይህን ጊዜ ለመሻገር አእምሮን በሌላ ጉዳይ ማዋከብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል።ይህ ወቅት የእለት ጉርሳቸውን እንደቀደመው የሰው ልጅ በየእለቱ እየሰሩ ከእጅ ወደአፍ የሚኖሩ ዜጎች ነገን እንዲያዩ ርብርብ ማድረግን ይጠይቃል።ዛሬ ወደነገ ለመሻገር የሚያስችሉ ጥንቃቄዎችን ከልብ በመስራት መተግበርን ይጠይቃል።ዛሬ የደከመው ኢኮኖሚያችን ይበልጥ ተዳክሞና ሞቶ ከበሽታው በላይ ሌላ አስከፊ የሞት ጥላ እንዳያንዣብብን ስልት መቀየስን ይሻል።በዚህ ወቅት እነዚህና መሰል አስተሳሰቦች ናቸው ወደ ነገ የሚያሻግሩን፡፡
በሌላ በኩል መንግስት ከምርጫ ጋር ተያይዞ የገጠመው ፈተናም ቀላል አይደለም።በተለይ አገሪቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት በለውጥ ሂደት ላይ የቆየች መሆኑና ይህንን ለውጥም በሰለጠነ መንገድ ምርጫ በማካሄድ በኢትዮጵያ የህዝብ
ተአማኒነት ያለው መንግስት ለመመስረት ደፋ ቀና በሚልበት ወቅት ኮሮና ያስከተለው ቀውስ እቅዱን ሙሉ ለሙሉ አናግቶታል።ያም ሆኖ ግን መንግስት በለውጥ ሂደቱ ያሳየው ከፍተኛ ቁርጠኝነትና አመራር አሁንም ከዚህ ችግር ለመውጣት የሚያስችለው እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል።
መንግስትም ይህ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ሌት ተቀን ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።በአንድ በኩል ህብረተሰቡ ስለኮሮና ቫይረስ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረውና በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ መንገዶችን እንዲከተል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ችግሩ የሚራዘም ከሆነ ከዚህ የበለጠ ሰብኣዊ ቀውስ እንዳያስከትል የሚያስችሉ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እርምጃዎችን በመውሰድ ክትትሉን አጠናክሮ ቀጥሏል።ነገር ግን የበሽታው ቀጣይ ሁኔታ ስለማይታወቅ ዛሬም የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።ዛሬን በመዘናጋት የሚከሰት ቀውስ የሚያስከትለው አደጋ የከፋ ከመሆኑም በላይ አገርን ትልቅ የህልውና አደጋ ውስጥ የሚከት ነው፡፡
ይህን ታሳቢ በማድረግም መንግስት ኮሮና ቫይረስ ከመከላከሉ ጎን ለጎን አጠቃላይ ፖለቲካዊ ችግሮችንም በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ውይይት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አካሂዷል።ትላንት ደግሞ የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረበውን የምርጫ ማራዘሚያ የውሳኔ ሃሳብ ከመረመረ በኋላ ያፀደቀው ሲሆን የመፍትሄ ሃሳብ እንዲቀርብም ለህግ፤ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።
ይህ ውሳኔ በቀጣይ መንግስትም ሆነ መላው ህዝብ ዋነኛ ትኩረቱን በሽታውን በመከላከሉ ላይ እንዲያውል ያግዛል።ከዚህም በሻገር መንግስት በቀጣይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ይረዳል።ምርጫው በቀጣይ ከበሽታው በኋላ መከናወን የሚችል ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ዜጋም ድምጹ ሳይባክን የሚፈልገውን የፖለቲካ ድርጅት እንዲመርጥና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታው በተጀመረው አቅጣጫ እንዲቀጥል ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ትልቅ ውሳኔ ነው።
ምርጫ የሚኖረው ህዝብ ሲኖር ነው።ህዝብ እንዲኖር ደግሞ ዛሬ ላይ ኮሮና ቫይረስን መከላከል እና በዚህም ሰበብ ሊከሰት የሚችለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተገንዝቦ ከወዲሁ መፍታት ይጠይቃል።ይህ ሳይሆን ቀርቶ መንግስትና የፖለቲካ ድርጅቶች ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ በምርጫ የሚያባክኑ ከሆኑ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል!
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 23/2012
ህይወትን መታደግ ከምርጫም በላይ ነው!