ስነ ልቦና ማለት በሰው ውስጥ የሚኖር እንስሶች የሌላቸው ነፍስ ማለት ነው። ሰው እና እንስሳት አንድ የሚያደርጋቸው ሕይወታቸው ሲሆን እርሷም የምትጠፋ ናት። ስነ ልቦና ግን ከተፈጠርን ጀምሮ አብሮን የሚኖር ውስጣዊ እኛነታችን ነው።
የስነ ልቦና ጥንካሬን መፍጠሪያ ከሆኑ መንገዶች መካከል የአእምሮ ህመምን ማከም እንደሚያስፈልገው ሁሉ የአእምሮ ጤናን ማጎልበት፣ የሰዎች ድክመት ላይ ከማተኮር ይልቅ ጥንካሬያቸውን ደጋግመን መንገር፤ ጥሩ ያልሆኑትን ለማቅናት የሚሞከረውን ያህል ምርጥ የሆኑትም እንዲቀጥሉ ማገዝ የአዎንታዊ ስነልቦና መገንቢያ መንገዶች ናቸው፡፡
በተለይ የኮሮና ወረርሽኝ የአለም አገራትን ባጥለቀለቀበት ወቅት የሰዎች ስነ ልቦና በተለያዩ መንገዶች እየተጎዳ ነው። ዛሬ ላይ በበርካታ አገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ ሰዎች ከቤት እንዳይወጡ በተደጋጋሚ ይነገራል፤ ሁኔታውን አስገዳጅ ያረጉት አገራት እንዳሉ ሆኖ። ክስተቱ ለአንዳንዶች ምቾት የማይሰጥ ብሎም ስነ ልቦናዊ ጫናን የሚያሳድር ነው።
ኮሮና እቤት መዋልን ከማስገደዱ ባሻገር በበሽታው የሚወዱትን የቤተሰብ አባል ማጣትን፣ የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ መግባትን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ያካተተ የስነ ልቦና ጫናን ሊያደርስ ይችላል።
የስነ ልቦና የጉዳት መጠን ችግሩ ካለፈ በኋላም እንኳ ዜጎች አምራች እንዳይሆኑ ሊጎትታቸው የሚችል በመሆኑ በሽታውን ከመከላከል ስራ ጎን ለጎን የሰዎችንም ስነ ልቦና መገንባት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።
ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ ሲከሰት ከበድ ያለና ውሰብስብ የሚሆንበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ምክንያቱም ኑሯችን በጋራ ከመሆኑም በላይ ከዘመድ አዝማድ እንዲሁም ከጎረቤት ጋር በሀዘን፣ በደስታና በበዓል በድግስ ተጠራርቶ አብሮ ጊዜ የማሳለፉ ነገር ብዙ በመሆኑ ነው። በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስን ከመዋጋት ጋር በተያያዘ ይህ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ለማለት ባንደፍርም እንዲቋረጥ ግን በተለያዩ አካላት ግፊት እየተደረገ ነው።
በአሁኑ ወቅት ተማሪዎች እቤት ናቸው፡፡ አብዛኛው ወላጅም ከልጆቹ ጋር የመሆን እድልን አግኝቷል፤ ግን ደግሞ በስራ አልያም በሌሎች ምክንያቶች ውጪ መዋል የለመደ ሰው በአንድ ጊዜ ቤትህ ተቀመጥ ሲባል ሊፈጥር የሚችለው የስነ ልቦና ጫና ቀላል የማይባል ነው።
እኛም ሰዎች እቤት በመዋላቸው ምን ዓይነት የስነ ልቦና ጫና ይገጥማቸዋል? ከዚህ ሁኔታስ መውጣት የሚችሉት እንዴት ባለው መንገድ ነው ?ስንል የስነ ልቦና ባለሙያ ከሆኑት ከዶክተር በየነች ጸጋዬ ጋር ቆይታን አድርገናል።
አዲስ ዘመን፦ ስነ ልቦና ማለት ምን ማለት ነው?
ዶክተር በየነች፦ ስነ ልቦና ወይም ሳይኮሎጂ ዘርፉ ብዙም እውቅና ያለው ባለመሆኑ ስንጠቀምበት አልቆየንም። አሁን አሁን እንዲያውም ከፍተኛ የሆኑ መሻሻሎች እየተስተዋሉ ነው።
ስነ ልቦና የሚያጠናው ስለ ሰው ልጆች ውስጣዊ ባህርይ ነው፤ ይህ ባህርይ ወይንም ደግሞ እንቅስቃሴ ከማንነት ጋር የተያያዘ ነው። በመሆኑም ሰዎች የሚያደርጉትን ነገር በማጥናትና በመረዳት ምን ዓይነት ባህርይ እንዳላቸው እንዲሁም በየትኛው ሁኔታ ተጎድተዋል የቱ ባህርያቸው ሊቀረፍ ወይም ደግሞ አብሯቸው ሊቀጥል ይገባል? የሚለውን በዝርዝር የሚያጠና ዘርፍ ነው።
አዲስ ዘመን፦ በኢትዮጵያ የስነ ልቦና ምንነትና አስፈላጊነቱን ተረድተነዋል ማለት ይቻላልን?
ዶክተር በየነች፦ አውቀን ሳይሆን ሳናውቅ እየተጠቀምንበት ነው፤ እንደ ሳይንስ ለብቻው ተወስዶና በስርዓተ ትምህርት ውስጥ ተካትቶ መሰጠት አልቻለም፤ ይህ ደግሞ የአገሪቱ የትምህርት ስርዓት ደካማነት መሆንን ያመለክታል፤ ስህተትም ነው።
ይህ ሁኔታ የሰውን ልጆች የሚጠቅም ባህርያቸውን የሚያንጽ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ብንጠቀመው እኛን ከዓለም ህዝብ ያቀራርበን ይሆናል እንጂ የተለየን
አያደርገንም፤ ሆኖም ሳይንስ መሆኑን ስላልተረዱትም ትተውት ኖረዋል። አሁን ላይ ግን ትንሽ ጅማሪዎች ስላሉ እነሱን ማስቀጠሉ ምናልባትም ወደፊት ከሳይንሱ ይበልጥ ተጠቃሚ ለመሆን ያስችለን ይሆናል።
አዲስ ዘመን፦ የሰዎችን ስነ ልቦና ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮች ምንድናቸው?
ዶክተር በየነች፦ የሰዎችን ስነ ልቦና ሊጎዱ የሚችሉ በርካታ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ያሉበት የኑሮ፣ የትምህርት ወይም ሌላ ሁኔታ ስነ ልቦናቸው ላይ ጫና ሊያሳድር ይችላል። ብዙ ሰዎችን አንድ ነገር በአንድ ጊዜ ሊጫናቸውና በስነ ልቦናቸውም ላይ ጫናን ሊያደርስ ይችላል።
አዲስ ዘመን ፦አንድ ነገር ብዙሀኑ ላይ የስነ ልቦና ጫና ሊያሳድር ይችላል ስንል ለምሳሌ የኮሮና ቫይረስ እያደረሰ እንዳለው ዓይነት ማለት ነው?
ዶክተር በየነች፦ አዎ ማለት ነው። በተለይም በቫይረሱ መስፋፋት ምክንያት የሰዎች እንቅስቃሴ ተገድቦ መቀመጡ ቀን ተቀን ከለመዱት አካሄድ የተለየ ስለሆነ በአንድ ቦታ ተወስነው የሚያደርጉት ነገር ሊጠፋቸው ይችላል። ይህ መሆኑ በራሱ የሚያስከትለው የስነ ልቦና ጫና ቀላል ነው ማለት አይቻልም።
በሌላ በኩል ደግሞ ልጆች ያላቸው ቤተሰቦች ብቻውን ከሚኖር ሰው በላይ የስነ ልቦና ጫናው ከፍ ሊልባቸው ይችላል።
አዲስ ዘመን፦ ለምንድን ነው ልጆች ያሏቸው ወላጆች ከሌላው በበለጠ ሁኔታ ለስነ ልቦና ቀውስ የተዳረጉ የሚሆኑት?
ዶክተር በየነች፦ አዎ በእነዚህ ሰዎች ላይ ጫና ከፍ ይላል። ምክንያቱም እነዚህ ወላጆች ምናልባት የሚኖሩበት ቤት ጠባብ ሊሆን ይችላል፤ በዚህ ላይ ልጆች ካሉ አሁን ላይ እንደ ልባቸው ወጣ ብለው መጫወት ካለመቻላቸው ጋር በተያያዘ በጣም አስቸጋሪ ይሆናል።
ልጆች በጣም እንቅስቃሴ የሚወዱ ናቸው፤ የሚማሩት የሚያድጉትም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው፤ ይህ ሁኔታ ሲገደብባቸው ይጨናነቃሉ በአንጻሩ ደግሞ ወላጆች ለምን ወጥተው መጫወት እንደማይችሉ ሲያስረዱዋቸውና እንዳይወጡ ሲከለክሉዋቸው የጭቅጭቅ መንስኤ ሊሆን ይችላል። ይህ ሁኔታ እንደምንም ተብሎ ለተወሰነ ጊዜ ማድረግ ይቻል ይሆናል ግን ደግሞ ረዘም ላለ ጊዜ ሲሆን በጣም ከባድ ነው የሚሆነው።
አሁን ላይ ልጆች ቤት መሆን አለባቸው፤ ይህ ደግሞ እንቅስቃሴያቸውን ይገድበዋል በዚህ ጊዜ ምቾት አይሰማቸውም ወላጆችም ግራ ይጋባሉ፤ ቀንም ማታም አብረው ነው የሚውሉት፤ ይህ ያልተለመደ ሂደት በመሆኑ ያለመስማማት ከፍ ሊል ይችላል።
አዲስ ዘመን ፦ ይህንን አብሮ የመቆየት ሁኔታን ወደ መልካም አጋጣሚ መቀየር አይቻልምን ? የሚቀይሩስ ካሉ እነርሱ ምን ዓይነት የስነ ልቦና ጥንካሬ ያላቸው ናቸው ማለት እንችላለን?
ዶክተር በየነች፦ አንዳንዱ ሰው ይህንን ጊዜ እንደ ወርቃማ እደል ተገንዝቦት ከልጆቹ ጋር ጥሩ ጊዜን ያሳልፋል። ሁልጊዜ ጠዋት ወጥቶ ማታ የሚገባ ወላጅ ምናልባት አሁን ለልጆቹ መጽሐፍ ለማንበብ እድል ያገኛል። ልጆቹንም ለማወቅ ሊጠቀምበት ይችላል።
ባልና ሚስትም ያላቸው ግንኙነት ጠለቅ ያለ እንዲሆን እድል ያገኛሉ። በመሆኑም አንዱ እድሉን
ሲጠቀምበት ሌላው ደግሞ ጭንቀቱን ከፍ የሚያደርግበት ሊሆን ይችላል። ይህም እንግዲህ ጉዳዩ አንድ ሆኖ የሰዎች ባህርይና ነገሮችን የሚረዱበት ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ ልዩነት ያለው በመሆኑ ነገሮቹንም የሚቀበሉት እንደ አመለካከታቸውና እንደ ባህርያቸው ስለሆነ ነው።
አዲስ ዘመን፦ እነዚህ ሁኔታው የሚያስጨንቃቸው ከልጆቻቸው ጋር ቆንጆ ጊዜን ማሳለፍ የሚያቅታቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በተቃራኒያቸው እንዳሉት ሰዎች ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
ዶክተር በየነች፦ ለምሳሌ ለብዙ ጊዜ በውጥን ይዘውት በሚቀጥለው ወር፣ በሚቀጥለው የእረፍት ጊዜዬ እሰራዋለሁ እያሉ ያስቀመጡት ነገር ሊኖር ይችላል፤ ይህንን ማከናወን ምናልባትም በቤት ውስጥ ሲቀመጡ ስራ እንዳያጡ ብሎም እንዳይጨነቁ ሊያደርጋቸው ይችላል።
ምናልባትም እኮ ጊዜ ያጡት የቤተሰቡን ፎቶግራፎች በሚገባቸው መልኩ አዘጋጅቶ ማስቀመጥ ሊሆን ይችላል፤ ይህ ጊዜ ሊወስድ የሚችል ስራ በመሆኑ አሁን ላይ ቁጭ ሲሉ ይህንን ቢሰሩት ትኩረታቸውን በስራ መጥመድና ቀኑንም ስጦታ እንደተሰጣቸው አድርገው በማሰብ ራሳቸውን በማዝናናት ሊያሳልፉት ይችላሉ።
በሌላ በኩልም በግላቸው እስከ አሁን ለማንበብ ጊዜ አጥተው ከነበረ የመጽሐፍ ማንበቢያ ጊዜ ሊያደርጉት ይችላሉ፤ ለልጆቻቸው ጥሩ የጨዋታና የተረት ፕሮግራም በማዘጋጀት ከእነርሱ ጋር የማይሰለች ጊዜን ለማሳለፍ ይችላሉ።
እድሉ ያላቸው በኢኮኖሚም ጥሩ ከሆኑ ደግሞ በተለያዩ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች (ቻናሎች) የሚተላለፉ ዶክመንታሪ ፊልሞችን በማየትም ማሳለፍ ከጭንቀትና ድብርት ከማውጣቱም በላይ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ጥሩና የማይረሳ ጊዜን እንዲያሳልፉ እድል ይፈጥራል።
እዚህ ላይ እኮ ቤታቸው ትንሽም ይሁን ትልቅ የእቃዎቹን አቀማመጥ በመቀየር፣ ቀለም በመቀባት፣ ባላቸው ቦታ መሬት አልያም እቃ ላይ አትክልቶችን በመትከል ለራስ አዲስ ስራን መፍጠርና መዝናናት ይቻላል።
አዲስ ዘመን፦ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ቦታ ከምንሰጠው ነገር መካከል በዓል በግንባር ቀደምትነት ይነሳል፤ በዓልን ተከትሎ የሚመጡ የዘመድ ጥየቃዎች በተለይም ትንሳኤ ሲሆን ይሰፋሉ፤ አሁን ደግሞ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እነዚህ ነገሮች አይከናወኑምና እንደው በህብረተሰቡ ላይ ሊያደርስ የሚችለው ስነ ልቦናዊ ጫናን እንዴት ማለፍ ይቻላል?
ዶክተር በየነች፦ ገበያው ካለ ሄዶ ራስን ጠብቆ መግዛት ይቻላል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ የበዓሉን ድምቀት የሚያጓድል ነገር አይኖርም፤ ምክንያቱም በተለይም በዚህ መሰሉ የጭንቀት ወቅት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ወደ አምላክ የምትጮህበት ጊዜ ነው፤ ይህንን ዋና ስንቅ አድርጎ መያዙ ከምንም በላይ የስነ ልቦና ጫናው እንዳይኖር ያደርጋል።
የትንሳዔ በዓል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል እንደመሆኑ ክርስቶስም የሰውን ልጆች ለማዳን ብሎ የሞተበት በመሆኑ ለበዓል የሚያስገፈልጉ ግብዓቶችን መሸመት እንኳን ባይቻል የክርስቶስን ፍቅር እያሰቡ በዓሉን በደስታ ማሳለፍ የሚችሉበትን ሁኔታ ለራሳቸው መፍጠር ይገባቸዋል። ካልሆነ ግን ላላስፈላጊ ስነ ልቦናዊ ጉዳትም መዳረግ ሊከሰት ይችላል።
አዲስ ዘመን፦ በበሽታው ተጠርጥረው በኳራንታይን ውስጥ ያሉ በርካታ ወገኖቻችን አሉና እነሱስ ይህንን ቀን በጽናት እንዲያልፉት ሊያደርጉት ይገባል የሚሉት የስነ ልቦና መንገድ ምንድን ነው?
ዶክተር በየነች፦ ይህ በጣም ሊተኮርበት የሚገባ ነገር ነው። ሰዎችም ከባድ ጊዜን እንደሚያሳልፉ እገምታለሁ። ይህም ቢሆን ግን ኳራንታይን እንዲገቡ ያደረገው አካል ለእነሱ ስነ ልቦና ጠቃሚ የሆኑ አገልግሎቶችን ማቅረብ ይገባዋል።
አዲስ ዘመን ፦ እንደ ባለሙያ እዚህ ቦታ ላይ የገቡ ሰዎች እራሳቸውን በምን መልኩ ነው ማጠንከርና ነገም ሌላ ቀን እንደሆነ እንዲሰማቸው ማድረግ የሚችሉት?
ዶክተር በየነች፦ አዎ እንግዲህ ሊገነዘቡት የሚገባው ነገር ቢኖር ቦታው በእድሜያቸው አንዴ የተሰጣቸውና ራሳቸውን ለማጠንከር የተመቻቸላቸው መልካም እድል እንደሆነ ነው፤ ከራሳቸው፣ ከአምላካቸው ጋር የመገናኛ ትልቅ እድል እንደሆነና በሽታውም እንደሌለባቸው ነገ ጥሩ ዜና እንደሚሰሙ በማሰብ እራሳቸውን ከጭንቀት ነጻ አድርገው መቆየት ይገባቸዋል።
ሌላው ደግሞ ወረቀትና እስክሪፕቶ የሚቀርብላቸው ከሆነ ሀሳባቸውን መጻፍ ቢጀምሩ፤ እስከ አሁን ግጥም ጽፈው የማያውቁ ከሆነ ቢሞክሩ፣ ይህችን ኳራንታይን የሆኑባትን ጊዜ ባህርያቸውን ቀርጸው ቢወጡ በጣም ጥሩ ይሆንላቸዋል።
ይህም ኳራንታይን ሳይመጣ በፊትም እኮ ሰዎች በተወሰነ ጊዜ ልዩነት ከፈጣሪያቸው ጋር ለመገናኘት ብቻቸውን የሚሆኑበት ቦታ አለ፤ በሀይማኖት አጠራሩ “ሱባኤ” ይይዛሉ። በዚህም የተወሰነ ሳምንታት ቆይተው ይመለሳሉ። ኳራንታይንንም ለእንደዚህ አይነት እድል መጠቀምና ቦታውን እንደ እምነታቸው ከፈጣሪያቸው ጋር መገናኛ ሊያደርጉት ይገባል። ይህንን በማድረግ
ቦታው ላይ ጥሩ ትውስታንም ይዘው ለመሄድ ይችላሉ።
አዲስ ዘመን፦ አንድ ሰው በስነ ልቦናው ጠንካራ ነው ሲባል ምን ምንም ባህርያት አሉት?
ዶክተር በየነች፦ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ሲሆኑ ወይንም መጥፎ አስተሳሰብ የሌላቸውና ነገሮችን ጥሩ ለማድረግ የሚጥሩ ሲሆኑ፤ በተለይም በዚህ ወቅት የመጣብን ችግር በጣም ከባድ ነው ግን ደግሞ ለመላው አለም ነው፤ ለእኛ ብቻ አይደለም የመጣው ሁኔታው ከባድ ቢሆንም ያልፋል ማለት የሚችሉ ሲሆኑ ነው።
በሌላ በኩልም ጭንቀትን ለማራገፍ የሚረዱ የአተነፋፈስ ስርዓቶችን መከተለም እረፍትን የሚሰጥና ዘና ያለ ስሜትን ውስጣችን እንዲፈጠር የሚያደርጉም ናቸው።
ስሜታቸውን ዘና ለማድረግም ጡንቻዎቻቸውን በማሳሳብና ለቀቅ በማድረግ ያለው ጭንቀት እንዲቃለል ያደርጋሉ፤ በዚህም ዝም ብሎ ከሚሰማ የህመም ስሜት ከመዛልና ከመድከም በመውጣት ጥሩ ስሜት እንዲፈጠር ማድረግ ይችላሉ።
በመሆኑም ህብረተሰቡ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከመጣበት ጭንቀትና ውጥረት ለመውጣት ልክ “ሳክስፎን” ተጫዋቾች መሳሪያው ድምጽ እንዲያወጣ ለማድረግ ከውስጣቸው አየር እንደሚስቡት ሁሉ፤ ሁሉም ሰው እንደዛ አየርን በመውሰድ እና ወደ ውጭ በማውጣት እጆችን፣ ፊትን፣ ማጅራትን፣ ትከሻን ከዛም ደረትና ሆድ በመጨረሻም እግርንና መቀመጫን ተራ በተራ በማንቀሳቀስ ልዩነቱን እየተረዱ በመሄድ ጭንቀትን ማባረር ይቻላል። ይህንን ቀለል ያለ የጭንቀት ማባረሪያ መንገድ ደግሞ በቀን ለሶስት ጊዜ ያህል፤ ማለትም ጠዋት ከመኝታቸው ሲነሱ፣ ከምሳ በኋላና ማታ ወደ መኝታ ከመሄድ በፊት ቢሰሩ ውጤቱ የሚታይ ይሆናል።
አዲስ ዘመን፦ አሁን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ጭንቀት ውስጥ ያለበት ጊዜ ነው፤ ከላይ ከጠቀሱልኝ ጭንቀት ማባረሪያ መንገዶች ሌላ እንዴት እናልፈዋለን ይላሉ?
ዶክተር በየነች፦ ይህ ከባድ ጊዜ ይታለፋል፤ ታሪክም እንደሚነግረን እንደዚህ የሚያስጨንቁ ጊዜያት ታልፈዋል፤ ይህንንም እናልፈዋለን። በዓለም ላይ ያሉ ሳይንቲስቶችና ተመራማሪዎች እየሰሩ ነው፤ ከዚህ አንጻር ጊዜው ሁኔታው ከባድ ቢሆንም ውጤት ይመጣል፤ እናልፈዋለን።
አሁን ደግሞ ወቅቱም ክርስቶስ እኛን ለማዳን የሞተበት ነውና ይህንንም በማሰብ እርሱም ይረዳናል በማለት እምነትን አጠናክሮ መሄድ ያስፈልጋል። በነገራችን ላይ ሞት ማንንም አያልፍም፤ ሁላችንም እንሞታለን አንዳንዶቻችን ደግሞ ቀናችን ከሆነ እንቅፋትም ለመሞት ምክንያት ይሆናልና ያን ያህል መጨነቅ ሳይሆን እናልፈዋለን ብሎ በማሰብ መጠንቀቅ ነው የሚሻለው።
አዲስ ዘመን፦ ለነበረን ጊዜ በጣም አመሰግናለሁ።
ዶክተር በየነች፦ እኔም አመሰግናለሁ።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21/2012
እፀገነት አክሊሉ
“ይህንን ወቅት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከቤተሰብ ጋር ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ ይቻላል” ዶክተር በየነች ፀጋዬ የስነ ልቦና ባለሙያ