‹‹የሰው ልጅ ህልውናው ቀጣይ የሚሆነው የኑሮው ዘይቤ በግብርናው ላይ የተመሰረተ ሲሆን ብቻ ነው ! ›› የሚል ጠንካራ አስተሳሰብ ይዞ ለሚነሳ ብዙም ተከራካሪ ይኖረዋል የሚል እምነት የለንም።ምክንያቱን ደግሞ በአንድ ምሳሌ ማሳየት ይቻላል።በ1977 ዓ.ም. ምድር ጠብታ ዝናብ እንኳ ናፍቃ ፣ ወንዞች ደርቀው፣ እንስሳትና የሰው ልጆች የሚቀምሱት አጥተው አካላቸው አልቆና ጠውልጎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍጡራን መርገፋቸው ሁሌም በሰቀቀን የሚታወስ መጥፎ ሀገራዊ ትዝታ ነው፡፡
ያንን ክፉ ወቅት በህይወት ኖሮ የታዘበም ፤ በታሪክ ያደመጥ ሆነ ያነበበ ሰማይ በዝናብ ይሞላ፤ ወንዞች እስካፋቸው ሞልተው ሲገማሸሩ ይታዩ፤ ምድር በሰብልና በአረንጓዴ ተክሎች ትጥለቅለቅ ብሎ የማይመኝ ማን ይሆን ያሰኛል።መቼም ቢሆን የዓለም የአየር ንብረት ተለዋዋጭ ነውና በአንድ ወቅት ያስደሰተው ልምላሜ በሌላ ወቅት ለሀዘን መዳረጉ ከቀደመው ክስተት የሚታወቅ ነው፡፡
ይሁንና ደስታን የሚያጎናጽፈን ጉዳይ ግን የእርሻ መሬቶች በምርት ተሞልተው ከአየር ጠባይ መዛባትና ከሰብል አጥፊ አረሞች እንዲሁም ከበሽታዎች ሲጠበቁና በቂ ምርት ተገኝቶ የሰው ልጅ በልቶና ጠግቦ ሲያድር ማየት ነው።በአገራችን የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ በግብርና ሚኒስቴር በኩል በርካታ ሥራዎች ተሰርተው ተስፋ ሠጪ ውጤቶችም እየተመዘገቡ ይገኛሉ ፡፡
ባለፉት ዓመታት መንግሥት ለግብርናው ዘርፍ ትልቅ ትኩረት በመስጠት የገበሬውን ህይወት ሊለውጡ የሚችሉ፤ በርግጥም የተጠበ ቀውን ያህል ባይሆንም መለወጥ የቻሉ ተግባራት ተከናውነዋል። የተገኙ ውጤቶች መንግሥት ለግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ቢሰራ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ሀገሪቱ በምግብ እህል አቅርቦት እራሷን እንደምትችል ያመላከቱ ጭምር ናቸው ።
የፌዴራል መንግሥት ከክልልና ፌዴራል የግብርና ተቋማት ጋር በመሆን ግንዛቤ መፍጠሪያ የምክክር መድረኮችን በማካሄድ በአርሶ አደር፣ በግል ባለሃብትና በመንግሥት ይዞታ ስር የሚገኙ እርሻ መሬቶችን በመለየት፣ የመስኖ መሰረተ ልማቶችን በማስፋት የጀመራቸውን ሥራዎች አጠናክሮ በመቀጠል ከቻለ ሩቅ የሚመስለውን በምግብ እህል ራስን የመቻል ጥረት ሊያቀርበው ይችላል ።
በቅርቡም የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ለግብርና ግብአት የሚውሉ አንድ ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የጸረ ተባይ አረምና ዋግ ኬሚካሎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቱ ማስታወቁ ፤ ለግዥው የዋለውን ገንዘብ የኦሮሚያ ክልሉ መንግሥት በብድር መስጠቱ ብሎም ከዚህ የእርሻ ትራክተሮችንና ውሃ መሳቢያ ፓምፖችን ለአርሶ አደሩ ማቅረቡ ደግሞ የክልል መንግሥታት የቱን ያህል አርሶ አደሩን ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ።
ይህን የክልሉን መንግሥት ተግባር ሁሉም ክልሎች እንደ ጠንካራ ተሞክሮ ወስደው ሊጋሩት የሚገባ ነው።በዚህ በአስቸጋሪ ወቅት የኮሮና ቫይረስ የግብርናውን ዘርፍ አደጋ ውስጥ ይከተዋል በሚባልበት ሰዓት የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ለአርሶ አደሩ ያሳየው አጋርነት የሚደነቅ ነው ።
ይህ ተግባር በሀገር አቀፍ ደረጃ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግና የምግብ እጥረትን ታሪክ በማድረግ ለጀመርነው የብልጽግና ጉዞ እርሾ ሊሆን የሚችልም ነው ፡፡
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21/2012
ለግብርናው የሚሰጠው ትኩረት ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል!