በኩታገጠም የአስተራረስ ዘዴ የተመረተው የስንዴ ምርት አሽቶ መሬቱን ሸፍኖታል፡፡ የስንዴው ቡቃያ ጎንበስ ቀና እያለ ምቾቱን በተሸከመው ፍሬ አስመስክሯል፡፡ ቀዝቃዛ አየር የሚወደው ይህ ሰብል ፍሬ ተሸክሞ በነፋስ እየተወዛወዘ አካባቢውን አስውቦታል፡፡ ነፋሻማው አየር የስንዴውን ዛላ ሲያወዛውዘው የሚያሰማው ድምጽ ቅዝቃዜውን ያስረሳል፡፡ይሄ ትዕይንት ከትናንት በስቲያ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ የአርሶ አደር በዓል በተከበረበት ወቅት ያስተዋልኩት ነበር፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ ገርባ ቀበሌ ነዋሪው አርሶ አደር ሀይሉ መኬ፤ ያለፉት ሶስት ዓመታት በስንዴ ክላስተር የብዙዎችን ማሳ በማገናኘት (በኩታገጠም)፣ በባለሙያዎች በመታገዝ ማምረታቸው ውጤታማ እንዳደረጋቸው ይገልጻሉ፡፡
አርሶ አደር ኃይሉ ባለፈው ዓመት ከአንድ ሄክታር 53 ኩንታል ማምረታቸውን በመጠቆም፤ አንዱን ኩንታል 1ሺ150 ብር ለገበያ ማቅረባቸውንም ይገልጻሉ፡፡ ዘንድሮ ከአንድ ሄክታር 58 ኩንታል አገኛለሁ ብለው ተስፋ አድርገዋል፡፡
አርሶ አደር ሙሉ ማሞ በበኩላቸው፤ በክላስተር መታቀፋቸው ቴክኖሎጂን ለማሳደግና ንጹህ ዘር ለማግኘት እንደረዳቸው ይናገራሉ፡፡ ዘንድሮ ተባይ ቢከሰትም በኬሚካል መከላከል ችለዋል፡፡ የዋግ በሽታ እንዳስቸገራቸውና ኬሚካሉም ውድ መሆኑን በመግለጽ፤ ለቀጣይ የምርት ጊዜ ዋግን የሚቋቋም የተለየ ዘር ለመጠቀም አስበዋል፡፡
የሞረትና ጅሩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ወንድምኩን እንደሚሉት፤ በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘይቤ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ማሳደግ መቻሉን ይጠቅሳሉ። በስንዴ አመራረት የተገኘውን ውጤታማ ስራ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ትግበራው የአርሶ አደሩን የምርት ተጠቃሚነት፣ የገበያ ትስስር ችግር የሚፈታበትን ሥርዓት ለማጠናከር መቻሉንም ይገልጻሉ፡፡ የአርሶ አደሩ የማምረት አቅም እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው፤ ከልማዳዊ አሰራር እንዲላቀቅ የሚቻለው ጥረት እንደሚደረግም ነው አቶ መብራቴ የሚገልጹት፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድም አገኘሁ በበኩላቸው፤ በዞኑ ካሉት 22 የገጠር ወረዳና አምስት የከተማ አስተዳደር ውስጥ 19 ወረዳዎች በስንዴ ክላስተር የታቀፉ መሆናቸውን ይጠቁማሉ፡፡ 46 ሺ605 ሄክታር መሬት መሸፈኑንና ሞረትና ጅሩ፣ ሲያደብርና ዋዩ፣ እንሳሮና ምንጃር ሸንኮራ ምርቱ በዋናነት የሚተገበርባቸው መሆኑንም ይጠቁማሉ፡፡
ሰሜን ሸዋ ዞን የተለያዩ ሰብሎች እንደሚመረቱበት የጠቆሙት አቶ ተፈራ፤ ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲና ከምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር የአካባቢውን ፀጋ ለማስተዋወቅ ጥረት መደረጉንም ተናግረዋል፡፡ በእስካሁን ትግበራ ከተገኙ ስድስት የግብርና ምርቶች የንግድ ምልክት ማግኘታቸውን ከእነዚህ መካከልም፤ የጅሩ ሰንጋ፣ ምንጃር ነጭ ጤፍና የአረርቲ ሽምብራ ይገኝበታል፡፡ የግብዓት አቅርቦት እጥረት፣ በሽታን ሊቋቋሙ የሚችሉ በምርታማነታቸው የታወቁ ዝርያዎችና ማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት፣ እሴት ጨምረው የሚያመርቱ ፋብሪካዎች በቅርበት አለመኖር በችግር የሚነሱ መሆናቸውንም ይጠቁማሉ፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሁሴን፤ የኩታ ገጠም ልማት ትግበራ በአጭር ጊዜ ውጤታማ ያደረገ መሆኑን ያነሳሉ፡፡ በአገር አቀፍ ከሚታረሰው 14 ሚሊዮን ሄክታር በሁሉም ሰብሎች ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺ ሄክታር ደግሞ በወሳኝ ሰብሎች መሸፈናቸውንም ይናገራሉ፡፡ በእጥረት የሚነሱትን የምርጥ ዘር አቅርቦት፣ የማዳበሪያና ሌሎች የግብአት አቅርቦቶች በወቅቱ አለመድረስን ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ፣ የግብይት ችግርን ለመፍታትም እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡
ዘላለም ግዛው
Your writing style is so engaging and easy to follow I find myself reading through each post without even realizing I’ve reached the end
Wonderful beat ! I wish to apprentice while you amend your web site, how could i subscribe for a blog web site? The account aided me a acceptable deal. I had been a little bit acquainted of this your broadcast provided bright clear idea
Hi my family member! I want to say that this post is awesome, nice written and come with approximately all significant infos. I would like to peer extra posts like this.