በመጋቢት 5 ቀን 1520 አነስተኛ የስፔናውያን ጦር መርከቦች ከኩባ ደሴት ወደ ሜክሲኮ አመሩ፤ መርከቦቹ 900 የሚሆኑ የስፔን ወታደሮችን ከፈረሶች፣ ከጦር መሣሪያዎችና ጥቂት የአፍሪካ ባሮች ጋር ይዘው ነበር፤ ከባሮቹ አንዱ፣ ፍራንቼስኮ ድ ኤጋ፣ ከሁልጊዜውም የከፋ ጭነት በሰውነቱ ተሸክሞ ነበር፤ ምንም እንኳን ፍራንቼስኮ ባያውቀውም፣ በትሪሊዮን ከሚቆጠሩ ሕዋሶቹ መካከል የሆነ ባዮሎጂያዊ ቦምብ ተጠምዶ ጊዜውን እየቆጠረ ነበር – የፈንጣጣ ቫይረስ፤ ፍራንቼስኮ ወደ ሜክሲኮ ከገባ በኋላ ቫይረሱ በሰውነቱ ውስጥ እንደአሸን መራባት ጀመረ፤ በመጨረሻም በቆዳው ላይ ሁሉ እየፈነዳዳ ፈጦ ወጣ፤ በትኩሳት እየተቃጠለ የነበረው ፍራንቼስኮ ሴምፖአላን በምትባል አንድ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የቀደምት አሜሪካዊያን ቤተሰብ ውስጥ እንዲተኛ ተደረገ፤ እርሱ ወደዚህ ቤተሰብ በሽታውን ሲያስተላልፍ፣ እነርሱም ጎረቤቶቻቸውን ለከፉ፤ በአስር ቀናት ውስጥ ሴምፖአላን የመቃብር ስፍራ ሆነች፤ ስደተኞች በሽታውን ከሴምፖአላን ወደ ጎረቤት ከተሞች አስተላለፉት፤ ከከተማ ከተማ በወረርሽኙ እየተለከፉ በሄዱ ቁጥር፣ በሁኔታው የተሸበሩ ሰዎች ልክ እንደ መአበል ወደ ሜክሲኮና ከዛም ባሻገር በመሰደድ በሽታውን አዛመቱት፡፡
በዩካታን ባሕረ ገብ መሬት ውስጥ ይኖሩ የነበሩት ማያዎች ሦስት እርኩስ አማልክት – ኢክፔትዝ፣ ኡዛንካክ እና ሶጃካክ – በሌሊት መንደር ከመንደር እየዞሩ ሰዎችን በበሽታው እየለከፉ ነው ብለው አመኑ፤ አዝቴኮች በቴዝካትሊፖካ እና በሲፕቶቴክ አማልክት ላይ በምናልባት ደግሞ በነጭ ሰዎች ጥቁር አስማት ላይ አላከኩ፤ ካህናትና ሐኪሞች ምክር ተጠየቁ፤ እነርሱ ግን ጸልዩ፣ በቀዝቃዛ ገላችሁን ታጠቡ፣ ሰውነታችሁንም ቅጥራን(ሬንጅ) ቀቡ እንዲሁም ጥቁር ጢንዚዛ ዳምጣችሁ በቁስሉ ላይ ቀቡ አሉ፤ ምንም የረዳው ነገር ግን አልነበረም፤ ወደ እነሱ ለመቅረብ እና ለመቅበር የሚደፍር ማንም ባለመኖሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አስከሬኖች በጎዳናዎች ላይ በሰበሱ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ መላው ቤተሰቦች እንደዋዛ ተጠራርገው ጠፋ፣ ባለሥልጣናት ቤቶች በሙታኖች ላይ እንዲደረመሱ አዘዙ፤ በአንዳንድ ሰፈሮች ውስጥ ግማሽ ሕዝቡ አለቀ፡፡ በመስከረም 1520 መቅሰፍቱ ወደ ሜክሲኮ ሸለቆ ደረሰ፤ በጥቅምት ወር ደግሞ የአዝቴክ ዋና ከተማ ወደሆነችው እና እስከ 250,000 ሰዎች ወዳስጠለለችው አስደናቂ ከተማ – ቴኖችቲትላን ሰተት ብሎ ገባ፤ በሁለት ወራት ውስጥም የአዝቴክ ንጉሠ ነገሥት ኩዊትላዋክን ጨምሮ ቢያንስ ሢሶውን ፈጀ፤ በመጋቢት 1520፣ የስፔን መርከቦች ወደ አካባቢው ሲደርሱ፣ ሜክሲኮ 22 ሚለየን የሚሆኑ ነዋሪዎች የነበሯት ሲሆን፣ እስከ ታህሳስ ወር ድረስ 14 ሚሊየን ሰዎች ብቻ በሕይወት ነበሩ፤ ፈንጣጣ የመጀመሪያው ማዕበል ነበር፤ አዲሶቹ የስፔን ጌቶች ራሳቸውን በማበልጸግ እና የአገሪቱን ተወላጆች በመበዝበዝ ሥራ ላይ ተጠምደው እያሉ እስከ 1580 ድረስ ፍሉ፣ ኩፍኝና ሌሎች ተዛማች ገዳይ የበሽታ ማዕበሎች የሜክሲኮን ሕዝብ ቁጥር ከ2 ሚሊየን በታች አውርደውት ነበር፡፡ ከሁለት ምዕተ ዓመታት በኋላ፣ በጥር 1878፣ ብሪታንያዊው አሳሽ ካፒቴን ጄምስ ኩክ ሀዋይ ደረሰ፤ የሃዋይ ደሴቶች ተፋፍገው በሚኖሩ ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች የተሞሉ ነበሩ፤ እነኝህ ሕዝቦች ከአውሮፓ እና ከአሜሪካ ሙሉ በሙሉተነጥለው የሚኖሩ ነበሩ፤ እናም በዚህ ምክንያት ለአውሮፓ እና ለአሜሪካ በሽታዎች በጭራሽ ተጋልጠው አያውቁም፤ ካፒቴን ኩክ እና አብረውት የነበሩ ሰዎች የመጀመሪያውን የፍሉ፣ የሳንባ ነቀርሳ እና የቂጥኝ በሽታ አምጪ ተሕዋሲያንን ለሃዋይ አስተዋወቁ፤ ተከታይ የአውሮፓ ጎብኝዎች በዚህ ላይ ታይፎይድ እና ፈንጣጣን ጨመሩበት፤ በ1853 በሃዋይ ከመዐቱ የተረፉት 70000 ብቻ ነበሩ፡፡ እስከ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የበሽታ ወረርሽኝ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደሉን ቀጠለ፤ በጃንዋሪ 1918 በሰሜናዊ ፈረንሣይ ምሽጎች ውስጥ ወታደሮች በአንድ ልዩ በሆነ ለካፊ ቫይረስ – በቅጽል ስሙ የስፓኒሽ ፍሉ–በሺዎች መረፍረፍ ጀመሩ፤ ይህ የጦር ግንባር ዓለም ከዚያ ቀደም አይታ የማታውቀው ቀልጣፋ የዓለማቀፋዊ አቅርቦት መረብ መዳረሻ ነበር፤ ወንዶችና ወታደራዊ ቁሳቁሶች ከብሪታንያ፣ ከአሜሪካ፣ ከሕንድ እና አውስትራሊያ እንደጉድ ይፈሱ ነበር፤ ዘይት ከመካከለኛው ምስራቅ፣ እህልና ሥጋ ከአርጀንቲና፣ ጎማ ከማላያ እና መዳብ ከኮንጎ ይጓጓዝ ነበር፤ በምላሹ ሁሉም በስፓኒሽ ፍሉ ተለከፉ፤ በጥቂት ወራት ውስጥ ወደ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች – ከዓለም አንድ ሥስተኛው ህዝብ – በቫይረሱ ተያዘ፤ በሕንድ ከሕዝቡ 5 ከመቶ (15 ሚሊየን ሰዎች) የሚሆነው አለቀ፤ በታሂቲ ደሴት 14 ከመቶ የሚሆኑት ሞቱ፤ በሳሞአ 20 ከመቶ የሚሆኑት፣ በኮንጎ የመዳብ ማዕድን ማውጫዎች ውስጥ ደግሞ ከአምስት ሠራተኞች መካከል አንደኛው በዚሁ ቫይረስ ሞቱ፤ በአጠቃላይ ወረርሽኙ አንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ50 ሚሊዮን እስከ 100 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን ሕይወት አጠፋ፤ የአንደኛው ዓለም ጦርነት ከ1914 እስከ 1918 ድረስ 40 ሚሊዮን ሰዎችን ገድሏል፡፡ ቀሪዎቹን ወረርሽኞች በተመለከተ ሳምንት እንመለስበታለን፡፡
ምንጭ፡ሆሞ ዲዮስ (የመጪው ዘመን አጭር ታሪክ)
የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19)
የኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ሲሆን ሲጀምር በትኩሳት ሲሆን በማስከተልም ደረቅ ሳል ይኖረዋል። ከሳምንት በኋላ ደግሞ የትንፋሽ ማጠርን ያስከትላል፤ በዚህ ሳቢያም አንዳንድ በበሽታው የተያዙ ሰዎች የህክምና እርዳታ ሊያስፈልጋቸው ይችላል። የእነዚህ ምልክቶች መታየት ግን በበሽታው የመያዝ ምልክት ላይሆን ይችላል። ምክንያቱም ምልክቶቹ ከተለመዱት የጉንፋንና የኢንፍሉዌንዛ ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ ነው።
ኮሮና ቫይረስ የከፋ በሚሆንበት ጊዜ ኒሞኒያን፣ ሳርስን፣ የውስጥ አካላት ሥራ ማቆምን እንዲሁም ሞትን ሊያስከትል ይችላል። በዕድሜ የገፉና አስም፣ የስኳር በሽታ፣ የልብ ህመምን የመሳሰሉ ቀደም ሲል የነበሩ የጤና ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች በበሽታው ሲያዙ በጠና የመታመም ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ሰዎች በበሽታው ከተያዙ በኋላ ምልክቶችን እስከሚያሳዩ ድረስ እስከ 14 ቀናትን ሊወስድ እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ገልጿል። ነገር ግን አንዳንድ አጥኚዎች ምልክት የማየቱ ነገር እስከ 24 ቀናት ድረስ ሊቆይ እንደሚችል ጠቁመዋል።
የኮሮና ቫይረስ ብቸኛው መከላከያ
ለኮሮና ቫይረስ እስካሁን የተገኘ ክትባትም ሆነ መድሃኒት ስለሌለ ዋነኛው የመከላከያ መንገድ የግል ንጽህናን መጠበቅ፤ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅና ከሚያስሉናከሚያስነጥሱ ሰዎች ሁለት ሜትር ያህል መራቅ ይገባል፡፡ የጤና ተቋማት እንደሚሉት በሽታውን ለመከላከል እጅን በመደበኝነት በደንብ መታጠብ እጅግ ጠቃሚ ነው። እስካሁን በሽታው እንዴት እንደሚተላለፍ በእርግጠኝነት የሚታወቅ ነገር የለም።
ነገር ግን የኮሮና አይነት ቫይረሶች ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፉት በበሽታው የተያዙ ሰዎች በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ወቅት በሚያወጧቸው ጥቃቅን ጠብታዎች አማካይነት ነው። ስለዚህም ስናስልና ስናስነጥስ አፍንጫና አፋችንን በሶፍት ወይም በክርናችን እንሸፍን፤ ፊታችንን እጃችንን ሳንታጠብ አንንካ። በተጨማሪም ከታመሙ ሰዎች ጋር የቀረበ ንክኪ ከማድረግ መቆጠብ በሽታውን ለመከላከል ያግዛል። የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች የሚፈለገውን ያህል በሽታውን ለመከላከል አያስችሉም።
የኮሮናቫይረስ አለብኝ ‘ብለው ከጠረጠሩ
በበሽታው ተይዣለሁ ብለው የሚያስቡ ሰዎች አስፈላጊውን ምክርና የህክምና ድጋፍ ለማግኘት ለሚመለከታቸው የጤና ተቋማት ማሳወቅ አለባቸው። በበሽታው ተይዞ ይሆናል ተብሎ ከሚታሰብ ሰው ጋር የቀረበ ንክኪ ከነበረዎት፤ እራስዎን ለተወሰነ ጊዜ ከሌሎች ሰዎች አግልለው እንዲቆዩ ሊነገርዎት ይችላል።
ስለዚህ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር የሚኖርን የቀረበ ንክኪ ማስወገድ ይኖርብዎታል። በሽታው ከተከሰተባቸውና ከሌሎች አገራት የተመለሱ ከሆነ ምናልባትም ለተወሰነ ጊዜ እራስዎን አግልለው መቆየት ሊያስፈልግዎት ይችላል። ኮሮና ቫይረስ ምንያህል አደገኛ ነው? ሊድንስ ይችላል? የዓለም ጤና ድርጅት ከ56 ህሙማን ላይ በሰበሰበው መረጃ መሰረት በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ አምስት ሰዎች መካከል አራቱ ቀለል ያሉ የበሽታውን ምልክቶች ብቻ ያሳያሉ።
በዚህም መሰረት፡
• 80 በመቶው ቀለል ያሉ ምልክቶችን ያሳያሉ
• 14 በመቶው ከባድ ምልክቶችን ያሳያሉ
• 6% በመቶው ክፉኛ ይታመማሉ ምንም እንኳን አሃዞቹ አስተማማኝ ባይሆኑም በበሽታው ከተያዙት መካከል የሚሞቱት ሰዎች ብዛት ዝቅተኛ እንደሆነ ተስተውሏል፤ ይህም ማለት በበሽታው ከተያዙ ሰዎች መካከል ከመቶው አንድ ወይም ሁለቱ ብቻ የሚሆኑት ናቸው ለሞት የሚዳረጉት። በአሁኑ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩት በህክምና ላይ ያሉ ሲሆን ሊሞቱ ይችላሉ። በዚህም ሳቢያ የሞት መጠኑ በመቶኛ ከፍ ሊል ይችላል።
ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ስልካችንን እንዴት እናጽዳ?
የዓለም ጤና ድርጅት ኮሮና ቫይረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ እንደሆነ ገልጿል። ድርጅቱ ይህ ወረርሽኝ ራሳችን ልንከላከለው የምንችለው መሆኑንም አስታውቋል። ይህንንም ለማድረግ እጃችንን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ ፊታችንን በተደጋጋሚ አለመነካካት፣ በምናስነጥስበት አልያም በምናስልበት ወቅት አፍና አፍንጫችንን በሶፍት አልያም በክርናችን መሸፈን የሚጠቀሱ መከላከያዎች ናቸው።
በቤታችንም ሆነ በምንሰራበት ስፍራ በተደጋጋሚ የእጅ ንክኪ የሚበዛባቸው ስፍራዎችን ማጽዳት ከመከላከያ መንገዶቹ መካከል አንዱ ነው። ነገር ግን ስልካችንን በየደቂቃው የምንጠቀም እንደመ ሆናችን እንዴት ማጽዳት እንዳለብን እስካሁን ካላሰብን ቀጣዩ ጠቃሚ ነጥብ ይሆናል።
ስልክዎን በኪስዎ፣ በቦርሳዎ አንዳንዴም ወደ መፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ይዘውት ይሄዳሉ። ምን ያህል ጀርም ስልክዎ ብቻ ተሸክሞ እንደሚገኝ አስበውታል? ኮሮናንስ ስላለመያዙ ምን ያህል እርግጠኛ ነዎት? የአሜሪካን የጤና ስርዓት በበላይነት የሚቆጣጠረው ሲዲሲ በምናስነጥስበት አልያም በምናስልበት ወቅት ከሰውነታችን የሚወጣው ጀርም በሚረጭበት ስፍራ ላይ ለሰዓታት በሕይወት ይቆያል ብሏል።
ስለዚህ ቆሽሸው የሚታዩን ነገሮችን በአጠቃላይ እንድናፀዳ ይመክራል። በማጽዳትና ከቫይረሱ ነጻ በማድረግ ረገድ ልዩነት እንዳለም ተቋሙ ያሳስባል። መጀመሪያ ቆሻሻውን ማጽዳት ቀጥሎም ከቫይረሱ ነፃ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ያስገነዝባል። ስልካችንን ለማጽዳት 70 በመቶ አልኮል ያለው ዋይፐር መጠቀም የሚቻል ሲሆን በረኪና ግን አይመከርም። ቀላል ሳሙናና ውሃም ለማጽዳት እንደሚያገለግልም ባለሙያዎች ይመክራሉ። ዶ/ር ሌና ሲሪክ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለንደን ማይክሮባ ዮሎጂስት ናቸው። እርሳቸው እንደሚመክሩት ከሆነ ስልክዎን ለማጽዳት ከቻርጀሩ መንቀል፣ መሸፈኛ ካለው ማውለቅ ቅድሚያ ልትወስዷቸው የሚገባው ተግባር ነው። ዋና ዋና የሚባሉት የስልክ አምራቾች ስልካችንን ለማጽዳት ኬሚካሎች፣ ለእጃችን ማፅጃነት የምንጠቀምባቸው ሌሎች እንዲሁም ሸካራ ነገርን ለማጽዳት የሚያገለግሉ ዋይፐሮችን መጠቀምን አይመክሩም። ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው የስልክዎን ስክሪን መከላከያ ይጎዳሉ አልያም ያወድማሉ የሚል ነው።
ስለዚህ ይላሉ ዶ/ር ሌና፣ በቀላሉ በውሃና በሳሙና በተነከረ ጥጥ ወይም ከጥጥ በተመረተ ጨርቅ ማጽዳት በቂ ነው። በጥጥ ወይም በጨርቁ የስልክዎን ስክሪንም ሆነ ጀርባ እንዲሁም ጎኖች ማጽዳት ይችላሉ። በዚህ ወቅት ግን የሚያጸዱበት ፈሳሽ በስልኮቹ ክፍተቶች በኩል እንዳይገባ ጥንቃቄ ያድርጉ። በርግጥ አንዳንድ ውሃን የሚቋቋሙ ስልኮች ቢኖሩም ከጊዜ በኋላ ግን ይህንን ብቃታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በአግባቡ ከወለወሉ በኋላ በለስላሳ ጨርቅ ማድረቅ አይርሱ።
ዶ/ር ሌና እንደሚሉት በሳሙናና ውሃ ስልክዎን ማጽዳት ቫይረሶችንና ጀርሞችን ከስልክዎት ላይ ያፀዳል። አይፎንን ስልኮችን የሚጠቀሙ ከሆነ፣ አፕል ስልክዎን በአግባቡ 70 በመቶ አይሶፕሮፔል አልኮል ባላቸው ዋይፐሮች ማጽዳት እንደሚችሉ ይመክራል። እነዚህን ዋይፐሮች ከኮምፒውተር መለዋወጫዎች መሸጫ ሊያገኟቸው ይችላሉ። በዚህ ሁሉ ስልክዎን ካፀዱ በኋላ ባልታጠበ እጅዎ ከሆነ የሚጠቀሙት መልሶ ስልክዎ በጀርሞች ይሞላል። ስለዚህ እጅዎን በየጊዜው መታጠብ አይርሱ!
ምንጭ -የዓለም ጤና ድርጅት እና ቢቢሲ
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 3/2012
አስከፊ ወረርሽኞች በታሪክ ውስጥ