የማሸማቀቅ ትንኮሳ በአካለ-ሰውነት አነስተኛ፣ አቅመ-ደካማ፣ በዕድሜ በጣም ወጣት፣ አይናፋር፣ ደጋፊ የሌላቸው፣ አካል ጉዳተኛ ወይም ተጋላጭ የሆኑ ሌሎች ሰዎችን አቅዶ የመጉዳትና የማሰቃየት ተግባር ነው። የማሸማቀቅ ትንኮሳ እንዲሁ የሚደረግ ተግባር ሳይሆን ታቅዶና በተደጋጋሚ አቅመ-ደካማ የሆኑ ሌሎች ሰዎችን ለመጉዳት የሚደረግ ተግባር ነው። ይህን ተግባር የሚፈፅም ሰው አሸማቃቂ ሲባል የሚፈፀምበት ሰው ደግሞ ተሸማቃቂ ይባላሉ።
አሸማቃቂዎች በጉልበትና አቅም ከፍ ያሉ ናቸው። የሚተነኮሰው ግለሰብ ደግሞ በጉልበትና አቅም ዝቅ ያለ ነው። ተንኳሽነት በተፈጥሮ የሚመጣ ባህሪ አይደለም። የመተንኮስ ልምድ ገና በልጅነት ከሁለት ዓመት ጀምሮ ሊጀምር ይችላል። የማሸማቀቅ ትንኮሳ በቀላሉ የማይቆምና ረጅም ጊዜ የሚቆይ ባህሪ ነው። የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የማሸማቀቅ ትንኮሳ በዓለም ደረጃ በተለያየ መልኩ ይከናወናል። ይህ ተግባር በተለያዩ ሀገራት በተለያየ መጠን ይገኛል። ባላደጉ ሀገራት ከግንዛቤ አለማደግ ጋር ተያይዞ መጠኑና ዓይነቱ የጎላ ነው።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ ተማሪዎች ትንኮሳው እንደደረሰባቸው ሪፖርት አድርገዋል። የማሸማቀቅ ትንኮሳ የተለያዩ ዕውነታዎች አሉት። ትንኮሳው ፆታ አይለይም። አሸማቃቂዎች የሚያለቅሱ፣ የሚናደዱና ዕልህ ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ላይ በይበልጥ ያተኩራሉ። ሦስት ዓይነት የማሸማቀቅ ትንኮሳዎች አሉ። የአካል፣ የቃል እና ማህበራዊ ትንኮሳዎች ይባላሉ። የአካል ትንኮሳ፦ መምታት፣ መደብደብ፣ መግፋትና ማነቅ ያካትታል። የቃል ትንኮሳ፦ ዛቻ፣ ማስፈራራት፣ የጥላቻ ንግግር፣ መሳደብ፣ መጠቋቆም፣ መሳለቅና ማንቋሸሽ ያካትታል።
ማህበራዊ ትንኮሳ ደግሞ ማግለልና ሐሜት በማውራት ተቀባይነትን ማሳጣት ያካትታል። የማሸማቀቅ ትንኮሳ ከባለፉት አሥርት ዓመታት ጀምሮ በአዲስ መልክ በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች መከሰት ጀምሯል። ይህም በአካል ከሚደረገው እየከፋ ሄዷል። በእጅ የሚያዙ ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች መኖራቸው ትንኮሳውን በማቅለሉ ለመፈፀም አመቺ ሆኗል።
ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ኢሞ፣ ኢ-ሜይል፣ ኢንስታግራም እና ቲዊተር መተንኮሻ መሣሪያዎች ናቸው። የማሸማቀቅ ትንኮሳ በትምህርት ቤት፣ በመጓጓዣ ተሽከርካሪዎች ላይ፣ በሥራ ቦታ፣ በመኖሪያ አካባቢ፣ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን፣ በመዝናኛ ቦታዎችና በተለያዩ ቦታዎች ሊከሰት ይችላል። ተንኳሽና ተተንኳሽ ሰዎች በሚገናኙበት ቦታ ሁሉ ሊከሰት ይችላል። የማሸማቀቅ ትንኮሳ በአንድ ግለሰብ ወይም በቡድን በጋራ የሚተባበሩ ሰዎች ሊደረግ ይችላል። በአንድ ግለሰብ ሲከወን ጉዳቱ ከቡድን ከሚደረገው ያነሰ ይሆናል።
በቡድን የሚደረገው ትንኮሳ በቃላትም ሆነ በአካል የብዙ ሰዎች የጋራ ጥቃት ስለሚሆን የከፋ ጉዳት ያመጣል። የማሸማቀቅ ትንኮሳ በሀገራችን ሰፊ ትኩረት አልተሰጠውም። የባለፉት 150 ዓመታት የፖለቲካ ቀውሶች የማሸማቀቅ ትንኮሳን መሠረት ያደረጉ ናቸው። የብሔር እኩልነት ተብሎ ሲጠራ የቆየው ከማሸማቀቅ ትንኮሳ ጋር በቀጥታ ይገናኛል። ለብሔሮች የተለያዩ ስያሜዎች ሲሰጡ ነበሩ።
ነፍጠኛ፣ ፂላ፣ ጋላ፣ ባሪያ፣ ወላሞ፣ ትምህክተኛ፣ ጠባብና ዘላን የሚባሉ ስያሜዎች ለብሔሮች የተሰየሙ ናቸው። እነዚህ ስያሜዎች አንድን ብሔር/ግለሰብ ለማሸማቀቅ ታቅዶ የሚደረግ ትንኮሳ ነው። ተንኳሹ በጊዜው የሥልጣን ባለቤት በነበረበትና ተተንኳሹ ደግሞ ተገዢ በሆነበት ጊዜ ነበር። ይህም ሁናቴ ሀገራችንን ለብዙ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውሶች ዳርጓት ቆይቷል። ትንኮሳ ከፖለቲካው ውጪ በማህበራዊው ሕይወትም በሰፊው ይታያል። የማህበረሰብ ልዩነትን የማቻቻል ልማድ ስለሌለን የማሸማቀቅ ትንኮሳ የተለመደ እንዲሆን ረድቷል። ለዚህም ትንኮሳ ሦስት ሀገራዊ አጋጣሚዎችን አነሳለሁ። በመጀመሪያው አጋጣሚ የአንዲት የስምንተኛ ክፍል ተማሪ የደረሰባትን አጋጣሚ አነሳለሁ።
አጋጣሚው የተከሰተው የዛሬ 20 ዓመት ገደማ ነበር። ባለታሪኳ ሥሟ አስቴር ይባላል። አስቴር ስምንተኛ ክፍል ስትማር ሳለ የመጀመሪያ የወር አበባዋን ታያለች። ከወላጅ እናቷ ጋር በግልፅ ፆታዊ ጉዳዮች ባለመወያየቷ ስለወር አበባ በቂ ግንዛቤ አልነበራትም። አስቴር በወቅቱ ነጭ ቀሚስ ለብሳ ነበር። በትምህርት ቤት ሳለች የወር አበባው ልብሷ ላይ መፍሰሱን የክፍል ተማሪዎቿ በማየታቸው በቡድን ሆነው እየተሳቀቁ ተሳልቀውባት ነበር። አስቴር የክፍል ተማሪዎች መሳለቃቸው በከፍተኛ ስላሸማቀቃት ተመልሳ ወደ ትምህርት ቤቱና ወደ ተሳለቁባት የክፍል ጓደኞች ላለመሄድ ወሰነች። በዚህም ምክንያት ለሁለት ዓመታት ትምህርቷን አቋረጠች።
በሁለተኛ አጋጣሚ አንዲት በጂንካ ከተማ የሚኖር እጅግ በጣም በቁመት አጭር የሆነን ሰው ታሪክ አነሳለሁ። ይህ ሰው ታመነ ይባላል። በቁመቱ ማጠር ምክንያት በደረሰበት ጫና ታመነ ትምህርቱን 9ኛ ክፍል ላይ ለማቆም ተገድዷል። የቁመቱን ማጠር የክፍል ጓዶቹ፣ የመንደር ጎረቤቶችና በየመንገዱ የሚያዩት ሰዎች ሁሉ ደጋግመው በማየት ይሳለቁበታል። ያሸማቅቁታል። አንዳንድ ሰዎች አጠገቡጋ ተጠግተው የቁመት ልኬት እያደረጉ ምን ያህል ከእነሱ እንደሚያጥር ያሳዩት ነበር። ታመነም ከሰዎች ለምን እንዲህ አጥሮ እንደተፈጠረ በህሊናው እራሱን ይወቅሳል። ይበሳጫል። አምርሮ ቁጭት ውስጥ ይገባል።
በዚህም ምክንያት ከሰዎች ጋር ማህበራዊ ግንኙነት ለመቀነስ ተገዶ ነበር። በሦስተኛ አጋጣሚ አንዲት የ28 ዓመት እንስት ከጋብቻ ጋር ተያይዞ ያጫወተችኝን አጋጣሚ አነሳለሁ። የዚህች ሴት ሥም ቤተልሄም ይባላል። ቤተልሄም በጣም ውብና ማራኪ ሴት ናት። ይሁን እንጂ አምስተኛ ዓመቷ ላይ ሳለች በተሳሳተ መርፌ ነርቯን በመጉዳቱ ግራ እግሯ እንዲያጥር፣ አንዲቀጥንና መራመድ እንዳትችል ዳረጋት።
ቤተልሄም እግሯ ላይ የብረት ድጋፍ ተደርጎላት እያነከሰች ነው የምትራመደው። በዚህም ምክንያት ቤተልሄም በውበቷ ተማርከው የሚቀርቧት ሰዎች የአካል ጉዳተኛ በመሆኗ መልሰው ይርቋት ነበር። በአንድ ወቅት አንድ ዕድሜው ገፋ ያለው ሰው ቀረባት። ሰውየው አድማሱ ይባላል። አድማሱ ለስድስት ዓመታት ያህል ከቤተልሄም ጋር በፍቅር ቆይቷል።
ነገር ግን ቤተልሄም አካል ጉዳተኛ ስለሆነች አቶ አድማሱ ሊያባት አልፈለገም። ቤተልሄም በዚህ ምክንያት ሞራሏ ተሰበረ። አካል ጉዳተኛ በመሆኗ ከሰዎች እኩል አይደለሁም የሚል የበታችነት ስሜት ተሰማት። ለረጅም ጊዜ በጭንቀት ውስጥ ሰምጣ ቀረች። ከፍተኛ መሸማቀቅ ደረሰባት። በሀገራችን ብዙ የማሸማቀቅ ትንኮሳዎች ይከሰታሉ። ልዩ ሰው መሆን ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል።
የቆዳ ቀለማቸው በጣም የጠቆረ ሰዎች፣ በጣም ረጅም ወይም አጭር የሆኑ ሰዎች፣ የድሃ ድሃ የሆኑ፣ መልካቸው የማያምሩ፣ አካለ-ሰውነታቸው ለየት ያሉ፣ ፆታዊ ማንነታቸው የተዛባ፣ አካል ጉዳተኞች፣ ማህበራዊ እክል የገጠማቸው ሰዎች፣ የባህልና አኗኗር ዘይቤያቸው የተለየ ሰዎች እና በቁጥር አናሳ የሆኑ ሰዎች የማሸማቀቅ ትንኮሳ በከፍተኛ ሁኔታ ሰለባ ናቸው። በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታ፣ በመኖሪያ አካባቢ፣ በትራንስፖርት፣ በመዝናኛ ቦታዎችና በየመንገዱ ልዩ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች የማሸማቀቅ ትንኮሳ ይደርስባቸዋል። የማሸማቀቅ ትንኮሳ ለአካላዊ፣ ለሥነ-ልቦናዊ፣ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ይዳርጋል። አካላዊ ጥቃት፣ ማደህየት፣ ማግለል፣ መድሎ እና የሥነ-አእምሮ ህመም ይዳርጋል። ከመደበኛ ሰዎች የበታች እንዲሆኑ ይፈረድባቸዋል። ከላይ በዝርዝር ለመግለፅ እንደሞከርኩት የማሸማቀቅ ትንኮሳ ለብዙ ቀውሶች እንደሚዳርግ ነው። ተተንኳሾች ከተንኳሾች በጉልበትና አቅም ያነሱ መሆናቸው መከላከል አይቻላቸውም። በዚህም ምክንያት ይህን ማህበራዊ ችግር ለመቅረፍ የሕግ ማዕቀፍ መቅረፅ፣ ስለማሸማቀቅና ትንኮሳ በተለያዩ መንገዶች ማህበረሰቡን ማስተማር፣ የተተንኳሾች ማህበር ማቋቋም እና ማህበራዊ ችግሮች ላይ በሰፊው መሥራት ያስፈልጋል እላለሁ። አበቃሁ።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 3/2012
በላይ አበራ ከአርባ ምንጭ ዮኒቨርሲት
ትንኮሳና ማሸማቀቅ በኢትዮጵያ