በ7 አህጉራት እና ከ212 በላይ ሀገራት የተዋቀረችው ዓለማችን ከ7.7 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ብዛት አላት። እ.አ.አ በ1804 ከክርስቶስ ውልደት በኋላ አንድ ቢሊዮን የደረሰው የዓለም ህዝብ ፈጣንና ወጥነት የሌለው ዕድገት አሳ ይቷል። ከ30 ዓመታት በኋላ ማለትም በ2050 እ.ኤ.አ. የዓለም የህዝብ ቁጥር 9.8 ቢሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይገመታል (ተ.መ.ድ. 2017 እ.አ.አ.)። ከዚህ ዕድገት ከፍተኛውን ድርሻ የኢሲያና የአፍሪካ ሀገራት ይወስዳሉ።
ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፈጣን የህዝብ ዕድገት ለተለያዩ ችግሮች ይዳርጋል። ከሚዳርጉ ችግሮች መካከል የኢኮኖሚ ማሻቀብ፣ የቁጠባ መጣኔ መቀነስ፣ የተፈጥሮ ሐብት መውደም፣ የአየር ንብረት መለ ወጥና የአካባቢ መበከል፣ የቆሻሻ ክምችት መጨመር፣ የአኗኗር ሁኔታ መዛ ባትና የኑሮ ውድነት መጨመር፣ ሥራ-አጥነት መብዛት፣ የነፍስ ወከፍ ገቢ መቀነስ እና የማህበራዊ መስተጋብር መዛባትና ማህበራዊ ችግሮች (ወንጀል፣ ስርቆት፣ ዝርፊያ፣ ግጭት፣ ጦርነት፣ ድርቅ እና ረሃብ) መበራከት ናቸው።
የህዝብ ብዛት መጨመር የመኖሪያ ቦታዎች መስፋፋትን ያመጣል። የመኖሪያ ቦታዎች መስፋፋት ለዱር አራዊት መኖሪያነት የሚያገለግሉ ቦታዎች በሰው ልጅ እንዲነጠቁ ያደርጋል። እነዚህ በሚነጠቁ ቦታዎች የሚኖሩ አራዊት ከሰው ልጅ ጋር ንክኪ ያደርጋሉ። ይህ ሁኔታም የሰው ልጅ እና የዱር እንስሳት ንክኪ እንዲፈጥሩ ያደርጋል። በንክኪው ከእንስሳት ወደ ሰው ያልታወቁና አዳዲስ የበሽታ አምጪ ተህዋሶች ይተላለፋሉ። እነዚህ በሽታ አምጪ ተህዋሶች የዘረ-መል ባህሪያቸውን ለውጠው የሰው በሽታ አምጪዎች ይሆኑና ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋሉ።
ካለፉት አሥርት ዓመታት ወዲህ ነበር በረሃማ አካባቢ ያሉ ደኖች እና ከሰው ልጅ ጋር ምንም ንክኪ ያልነበራቸው አካባቢዎች አዳዲስ ቫይረሶችና በሽታ አምጪ ተህዋሶዎች እንደ ኢቦላ፣ ኤችአይቪና ደንግዩ ያሉ በሽታዎች ተያያዥነት እንዳላቸው ጥናቶች ማሳየት የጀመሩት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተ ፈጥሮ ሐብት መውደም ከአዳዲስ ቫይረሶች መነሳት ጋር ሊያያዝ እንደሚ ችል ብዙ ተመራማሪዎች ማሰብ ጀምረዋል። በታህሳስ ወር በ2012 ቻይና ውስጥ ብቅ ያለው የኮቪድ-19 በሽታ አንዱ ምሳሌ ሊሆን ይችላል። የአካባቢ ሳይንቲስቶች የሰው ልጅ፣ የዱር እንስሳት እና ስነ-ምህዳር የሚፈጥሩት ግን ኙነት ለአዳዲስ በሽታዎች መነሳት ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገልፃሉ።
የሰው ልጅ የሚያከናውናቸው ተግባራት ማለትም፦ የመንገድ ግንባታ፣ የማዕድን ማውጣት ሥራ፣ የዱር አራዊት አደን እና የደን ጭፍጨፋ ስነ- ምህዳርን በማዛባት የኢቦላ ወረርሽኝ እንዲከሰት እንደረዳ በ1990ዎች የተ ደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ። የሰው ልጅ በረሃማ አካባቢዎች ያሉ ደኖችን በመጨፍጨፍ ያልታወቁ የዱር አራዊት መኖሪያዎ ችን ያወድማል። በዚህም ምክንያት ላልታወቁ የቫይረስ ዝር ያዎች ተጋላጭ ይሆናል። እኛ የሰው ልጆች ዛፎችን በመቁረጥ የተፈጥሮ ስነ-ምህዳሩን ስናዛባና በቦታው የሚኖሩ ቫይረሶችን ተፈጥሯዊ መኖሪያቸውን ስናጠፋ መኖሪያ ያጡና እኛ የሰው ልጆች መኖሪያቸው እንሆናለን።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት እንስሳት-ወለድና ተዛማጅ በሽታ ዎች ለምሳሌ ኢቦላ፣ ሳርስ፣ በርድ-ፍሉ እና ኮቪድ-19 አከሳሰታ ቸው ጨምሯል። በሽታ አምጪ ተህዋሶች ከእንስሳት ወደ ሰው እየተላለፉ እና ብዙዎች በፍጥነት ወደ አዳዲስ ቦታዎች እየተ ላለፉ ነው። እንደ የአሜሪካው ሲዲሲ ግምት ¾ኛ የሚሆኑ አዳዲስ በሽታዎች ከእንስሳት ተነስተው በመጀመሪያ ከተከሰ ቱበት አካባቢ አልፈው ሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችን ማጥቃት ችለዋል።
እንደ ሬቢስ እና ፕላግ ያሉ በሽታዎች ከእንስሳት ወደ ሰዎች ከ100 ዓመታት በፊት የተላለፉ ናቸው። ሌሎች ለምሳሌ ማርበርግ (ከሌሊት ወፍ እንደሚተላለፍ የሚታመን) አሁን ላይም አልፎ አልፎ አለ። ዘንድሮ በታህሳስ ወር በውሃን ቻይና የተነሳው ኮቪድ-19 ለሰው ልጅ አዲስና በዓለም-አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ ያለ ወረርሽኝ ነው። ሌሎች በሽታዎች ለምሳሌ ላዛ ፌቨር በናይጄሪያ እ.አ.አ 1969 ነበር የታወቀው፤ ኒፓህ በማ ሌዥያ፤ ሳርስ በቻይና፤ ዚካና ዌስት ናይል-ቫይረስ በአፍሪካ ተነስተው ዘረ-መላቸውን ለውጠው ቋሚ በሽታዎች ሆነዋል።
በከተሞች አካባቢ ያለው የህዝብ ጥግግት ለወረርሽኝ በሽ ታዎች በፍጥነት መስፋፋት አመቺ ነው። የሰው መኖሪያ ቤቶች የተጠጋጉና የተያያዙ በመሆናቸው ከአንድ መኖሪያ ቤት ወደ ሌላው ቤት ለመስፋፋት አመቺ ነው። በአንድ ውስን ስፍራ ብዙ ሰዎች መኖራቸው ከሰው ወደ ሰው በሽታዎች ለመተላ ለፍ ያመቻል። በተጨማሪም በሽታ አምጪ ተህዋሶች መመሸ ጊያ እንደ ደን ያለ ስፍራ አለመኖሩ በከተማ የሚኖረው የሰው ልጅ ማረፊያው ይሆናል።
እነዚህ እንደ አዲስ የሚነሱት እንስሳት-ወለድና ተዛማጅ በሽታዎች የዓለም የጤና ሁኔታ፣ ድህነት እና ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ሥጋት ይፈጥራሉ። ይህ ሁናቴም ለብዙ ሰዎች መታ መምና መሞት፣ ሰላምና ደህንነት መናጋት እና የኢኮኖሚ ግሽበት ይዳርጋል። ከወረርሽኝ መከሰት ጋር ተያይዞ የሚፈ ጠረው አደጋ የዓለም ኢኮኖሚን በሰፊው ያናጋል። የትራን ስፖርት መቆምና የንግድ እንቅስቃሴዎች መገታት የዓለም ኢኮኖሚ ይጎዳና የኢኮኖሚ ማሻቀብ ያመጣል። የኢኮኖሚ ማሻቀብ ረሃብና ድርቅ ያመጣል። ማህበራዊ ችግሮች ይበረ ከቱና ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ይወድቃል። ብዙ ከጤና ጋር በቀጥታ ተያያዥ ያልሆኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ይበረክታሉ።
የዱር አራዊት መኖሪያዎችን መንካት ከበሽታዎች አልፎ ለአካል ጥቃትም ይዳርጋል። ለምሳሌ የእባቦች መኖሪያ ቦታ ሰዎች ቢሄዱ በእባቦች ይነደፋሉ። አዞና ጉማሬ ያለባቸው ሐይ ቆችም ለዋናና ዓሣ ለማስገር ሰዎች ሲሞክሩ ጥቃት ይደርስባቸ ዋል። የአራዊት መኖሪያ ቦታዎች መንካት ለጥቃት ለበሽታዎች በተጨማሪ ይዳርጋል።
ከላይ በዝርዝር ለማብራራት እንደሞከርኩት የህዝብ መብዛት የከተማ መስፋፋትና የደን ሥፍራዎች መከበብና መራቆት ስለሚያመጣ የተፈጥሮ ሐብት እንዲወድም ያደር ግና የዱር አራዊት መኖሪያ ቦታዎች በሰው ልጅ ይነጠቃሉ። ይህ አጋጣሚ የደን ስፍራዎች የሚኖሩ የዱር አራዊት ከሰው ልጅ ጋር ንክኪ ይፈጥሩና የእንስሳት-ወለድና ተዛማጅ በሽታ ዎች ከአራዊት ወደ ሰው ይተላለፋሉ። ከአራዊት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች የዘረ-መል ባህሪያቸውን ይለዋውጡና የሰው ልጅ በሽታዎች ሆነው ይቀራሉ። ስለዚህ የህዝብ ዕድ ገትን መግታት፣ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ መሥራት፣ የማህበረሰብ ግንዛቤን ማሳደግ፣ የዱር አራዊት መኖሪያ ቦታ ዎችን መጠበቅ እና የሰው ልጅ ከዱር አራዊት ጋር ያለውን ንክኪ መቆጣጠር ሊሠሩ የሚገባቸው የመፍትሄ አቅጣጫዎች ናቸው። አበቃሁ።
(የአሜሪካው ሲዲሲ፣ የዓለም ጤና ድርጅት እና ተ.መ.ድ. – የመረጃ ምንጮች ናቸው)
አዲስ ዘመን መጋቢት 26/2012
በላይ ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ