አዲስ አበባ፡- የለውጡን ጉዞ ሁለተኛ ዓመት የምናከብረው በአንድ በኩል ፈተናና ስጋት፤ በሌላ በኩል የተስፋ ወጋገን ከፊታችን እየታየን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ትላንት
በሀገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት፤ ሀገራችን ባለፉት ሁለት ዓመታት በለውጥ ሂደት ያገኘቻቸውን ተስፋዎች ለማፍካት፣ ያጋጠሟትን ሳንካዎች ደግሞ ለማስተካከል እየጣረች ባለችበት ወሳኝ ወቅት መላው ዓለምን በጥቂት ወራት ውስጥ በቁጥጥሩ ስር ያዋለው የኮሮና ቫይረስ በእኛም አገር አሻራውን
አሳርፏል፡፡ ወረርሽኙ ወደ ሀገራችንም ገብቶ 29 ሰዎችን የቫይረሱ ተጠቂ አድርጓል፡፡ ነገ ምን ያህል ዜጎቻችንን እንደሚያጠቃ በእርግጠኝነት ባናውቅም ሁላችንም ተረባርበን በዝቅተኛ ጉዳት እንደምናስቆመው ግን ሙሉ እምነት አለን፡፡
ሀገራችን በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ስታልፍ ይኽ የመጀመሪያዋ አይደለም፤ የመጨረሻዋም ላይሆን ይችላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በለውጡ ጉዞ የመጀመሪያው ምዕራፍ ወቅት በሶማሌ ክልል የተነሳውና በመሳሪያም፣ በጭካኔም እስካፍንጫው ታጥቆ የነበረው ሀይል የለኮሰው እሳት የአፍሪካ ቀንድን እስከመረበሽ ሊደርስ ይችላል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ መፈጠሩ አይካድም ብለዋል። ያም ሆኖ የለውጡ ዓላማ ኢትዮጵያን በፍትሕ የላቀች፣ በዴሞክራሲ የዳበረች፣ በሰብአዊ መብት ጥበቃ የተመሰገነች፣ በኢኮኖሚ የበለጸገች፣ በሰላምና በደኅንነት የተረጋጋች ሀገር ማድረግ ነበርና ከፈተናው ጎን ለጎን በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ያ መጥፎ አጋጣሚ አልፎ እዚህ ደርሰናል ሲሉም አክለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለፁት፣ በተመሳሳይ የታጠቁ ኃይሎች በወለጋ እና በሌሎች የምእራብ ኦሮሚያ ክፍሎች ላይ የጥፋት በትራቸውን አሳርፈው ባንክ እየዘረፉ፣ ሰው እየገደሉ፣ ቤት እያቃጠሉ፣ መንገድ እየዘጉ፣ ትምህርት ቤት እየዘጉ ነዋሪውን እያማረሩ የነበረበት፤ ከገጠር ቀበሌዎች አልፎ እንደ ነቀምት፣ ጊምቢ እና ሻምቦ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ውስጥ መንግስታዊ መዋቅርን ለማፈራረስ የተንቀሳቀሰበት፤ የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎች ያለወታደራዊ አጀብ የሚያስቸግሩበት ጊዜያትን አስተናግደናል። የለውጥ ጉዞው ይሄንንም መጥፎ ጊዜ አልፎ አሁን የሕዳሴ ግድብ ግንባታችንን እያጣደፍን፣ ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶቻችንን በማጠናቀቅ ተስፋችንን ሳይሆን ሪቫን እየቆረጥን ዛሬ ካለንበት ደርሰናል።
በአንድ ቀን በአማራ ክልል ጠንካራ ጓዶቻችንን በግፍ አጥተን፤ በአዲስ አበባ ተወዳጅ የጦር መሪዎቻችን ተገድለው፤ ውጥረቱ ለድፍን ኢትዮጵያ ተርፎ የነበረበት ጊዜ አልፏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እዚህና እዚያ እሳት በተለኮሰ ቁጥር ጥፋተኛው ይህና ያኛው ቡድን ነው እየተባለ፤ በየአካባቢው ሀያና ሰላሳ የታጠቀ ጦር ሠራዊት ያለ እስኪመስል ድረስ በየቦታውና በየጊዜው ሰዎች እየተገደሉ፤ አንድ ሰው አልበቃ ብሎ መንደር በሙሉ በእሳት ይጋይ የነበረበት፤ እልቂቱ በአንድ አካባቢ ሳይወሰን፣ ሁለትና ሦስት ክልሎችን ያነካካበት፤ ዜጎች ኢትዮጵያ ልትበታተን ትችላለች በሚል ስጋት ውስጥ እንዲቆዩ የሆነበት አስጨናቂ ጊዜን ተረማምደናል ብለዋል።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ገለጻ፤ ኃላፊነት በማይሰማቸው ሰዎች ንግግር ወንድም እህቶቻችንን የተቀጠፉበት፤ በትንሽ በትልቁ የህግ የበላይነት ያበቃለት፣ ኢትዮጵያም ያከተመላት እንዲመስል ተደጋጋሚ የጥፋት ርምጃዎች የተካሄዱበት ወቅት አልፎ ከሞላ ጎደል ወደ ሰላማችን ተመልሰናል። የለውጥ ጉዞው በየጊዜው የሚገጥሙትን ጋሬጣዎች ከመሻገር ባለፈ የተለያዩ የሪፎርም ተግባራትን ለማከናወን የተንቀሳቀሰበት ወሳኝ ወቅትም ነበር።
“ቀጣዩ የለውጥ ዘመን ካሳለፍናቸው ሁለት የለውጥ ምዕራፎች የተሻለ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ሀገራችንን ወደሚገባት ምእራፍ እንደምናደርሳት አምናለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህ ደግሞ የሁላችን የሥራና ጸሎት ሕብረት ያስፈልጋታል ብለዋል።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ገለጻ፤ ተባበርን፣ ተደመርን፣ በአንድነት ወቅታዊ ፈተናችንን እንሻገራለን፤ የምንመኛትን፣ የምንጓጓላትን፣ የበለጸገች ኢትዮጵያን እንገነባለን። የተዘጉ ትምህርት ቤቶች፣ መስሪያ ቤቶችና ድንበሮች ይከፈታሉ፤ የተቀዛቀዘ ኢኮኖሚያችን ዳግም ያንሰራራል። ላልተወሰነ ጊዜ የምናደርገው መራራቅ በመቀራረብ ይተካል። እንቅስቃሴዎች ሁሉ ወደነበሩበት ይመለሳሉ። ሞትም በሕይወት ይሸነፋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 25/2012
በጋዜጣው ሪፖርተር
“የለውጡን ጉዞ ሁለተኛ ዓመት የምናከብረው በአንድ በኩል ፈተናና ስጋት፤ በሌላ በኩል የተስፋ ወጋገን ከፊታችን እየታየን ነው”