በአሁኑ ወቅት ዓለም ከፍተኛ ፈተና ከፊቷ ተጋርጧል። በዓለም የስልጣኔ ማማ ላይ ያሉ አገራት ሳይቀር በኮሮና ቫይረስ እየታመሱ ነው። 45ሺ የሚጠጉ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውንና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ተጠቂ ያደረገውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት የተለያዩ ጥረቶችን እያደረጉ ይገኛሉ። ከእነዚህ ዘዴዎች መካከል እንቅስቃሴን መገደብና ሰዎች በቤት ውስጥ እንዲቀመጡ ማድረግ አንዱ ነው።
በኢትዮጵያም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሲባል የመንግስት ሰራተኞች ቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ
በመንግስት ውሳኔ ተላልፏል። ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎችም በጊዜያዊነት ተዘግተዋል። ይህን ተከትሎ ሰዎች ቤታቸው ሲያሳልፉ ለጭንቀት እንዳይዳረጉ ማከናወን በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የስነ ልቦና ሳይንስ ምሁራን ምክር ይለግሳሉ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስነ ልቦና መምህር የሆኑት ዶክተር ትግስት ውሄብ እንደሚሉት፤ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት መፍትሄ ናቸው ከሚባሉት መካካል ዋናው ቤት መቀመጥ ነው። በኢትዮጵያም የቫይረሱ ስርጭት ለመከላከል መንግስት የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን ቤት ሆነው እንዲሰሩ ውሳኔ አስተላልፎአል። ይህን ተከትሎ ሰዎች ቤት መዋልን ያለመዱትና ያልተዘጋጁበት በመሆኑ ጭንቀት ሊፈጥርባቸው ይችላል። በተለይ የጭንቀት ችግር ያለባቸው ሰዎች “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንደሚባለው የበለጠ የሚጠበቁበትና ያለ ስራ ቁጭ ሲሉ ደግሞ የጭንቀቱ መጠን ይጨምራል ይላሉ።
ሰዎች ሲቀመጡ በጥቅሉ ውጤታማ በሚያደርጉ ተግባራት ላይ ቢያሳልፉ በሽታውን ከመከላከል በሻገር ለወደፊት ህይወታቸውም ሆነ እውቀታቸው ያተርፉበታል የሚሉት ዶክተር ትዕግስት፤ ወላጆች ከቤት ውስጥ ሲቆዩ ልጆቻቸውን በማስተማር፣ በማጫወትና በውይይት ማሳለፍ ይኖርባቸዋል ይላሉ። ፍቅረኞችም ስለቀጣይ
ከ 1ኛው ገጽ የዞረ
የሕይወታቸው ምዕራፍ በማቀድና በመዘጋጀት እንዲሁም ጊዜን በንባብ፣ ፊልም በማየትና ሌሎች የሰዎችን ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ ስራዎችን በማከናወን ማሳለፍ ከጭንቀት እንደሚገላግልና ለቀጣይ ህይወታቸው ውጤታማ እንደሚያደርግ ዶክተር ትዕግስት ይመክራሉ።
“በአንጻሩ ሰዎች የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ሲባል ቤት ሆነው እንዲያሳልፉ ሲደረግ ከአዎንታዊ ይልቅ በአሉታዊ ምላሾች የሚሰጡ መኖራቸውንም አውስተዋል። የተወሰኑ ሰዎች ጭንቀቱን ለመርሳትም ጫት ቤት፣መጠጥ ቤትና ሺሻ ቤቶች የማሳለፉ ሁኔታ ሊስተዋል ይችላል።ይህ ተግባር ግን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። ጦሱ ከራሳቸው አልፎ ለቤተሰብም ይተርፋል። እውነተኛ መረጃ ላይ ተመርኩዞ ቀጥተኛ የሆነ ምላሽና መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ችግሩ እኛ አገር አልተፈጠረም፤ አይመጣም ብሎ እውነታን መካድ ተገቢም ትክክልም አይደለም። በተለይ ይበልጥ ለችግሩ ተጋላጭ የሚያደርጉ የመጠጥ ቤቶች፣ጫት ቤቶችና ሌሎች ለሱስ አጋላጭ በሆኑ ቦታዎች መገኘት ተገቢ አይደለም” ይላሉ ዶክተር ትዕግስት።
ዶክተር ትዕግስት እንደሚሉት በሌላ በኩል በስሜት የመመራት ሁኔታ ደግሞ ለራስም ሆነ አብሮ ካለው ሰው ጋር የተግባቦትና የሀሳብ ያለመጣጠም ሁኔታ ሊያመጣ ይችላል። ይህ ደግሞ ቅራኔ ሊፈጥር ይችላል። ለዚህ መፍትሄው ቤት መቀመጥ በስነ ልቦና ያለውን የጭንቀት ጫና ለመቀንስ ስለ ኮሮና ቫይረስ የሚተላለፉ የተጋነኑ በተለይ የማህበራዊ ሚዲያ ዜናዎችን አለመከታተል እንደሆነ ይመክራሉ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስነ ልቦና(ሳይኮሎጂ) የትምህርት ክፍል የማህበራዊ ስነ ልቦና መምህር ፕሮፌሰር ሀብታሙ ወንድሙ በበኩላቸው ሰዎች የተለመደ ተግባራቸው በድንገት ሲቆም መጨነቃቸው አይቀርም። ከመጨነቅ ይልቅ ቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎችና ራሳቸውን ቤት ውስጥ ሆነው በሚሰሩ ስራዎች ማሳለፍ ይኖርባቸዋል። ከብዙ ሰዎች ጋር የሚገናኝና ማህበራዊ ትስስሩ ጠንካራ የነበረ ሰው ቤት መቀመጡ ሊከብድ ቢችልም አማራጭ መፍትሄዎችን መፈለግ ይገባል ይላሉ።
ለምሳሌ” እኔ የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ።አሁን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሲባል መንግስት ዩኒቨርስቲዎች እንዲዘጉ በወሰነው ውሳኔ ቤት ነው የምውለው። ዩኒቨርሲቲ ዝግ ነው ብዬ ቁጭ አላልኩም። እውቀቴን ለማስፋት አነባለሁ፣ስለ ኮሮና ቫይረስ ስርጭትና ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች መረጃም እከታተላለሁ፤ ቴሊቪዥንም እከታተላለሁ፤ ሌሎችም ተመሳሳይ ተግባሮችን አከናውናለሁ” ሲሉ የራሳቸውን ተሞክሮ ነግረውናል።
ሰዎችም ጊዜያቸውን ቤት ሲያሳልፉ የተለያዩና የኃይማኖት መጽሐፎችን ቢያነቡ፤ቢጸልዩና የመዝናኛ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን በመከተል ቢያሳልፉ የራሳቸውንም ሆነ የቤተሰባቸውን ከኮሮና ቫይረስ ከመከላከል ባሻገር በህይወታቸውና በስራቸው ውጤታማ ይሆናሉ። የንባብ ባህል የሌላቸው ሰዎች ደግሞ አትክልቶችን በመንከባከብ፣በአካባቢ ጽዳትና በሌሎች ስራዎች ቢጠመዱ ራሳቸውን ከጭንቀት መከላከል ይቻላል። በአንጻሩ በመጠጥ ጊዜ ለማሳለፍ መሞክር ለኮሮና ቫይረስ ከመጋለጥ አልፎ የጤና ጉዳት ያስከትላል።ሌላውንም ሆነ ራስንና ቤተሰብን ከመጎዳት የተወሰነ ጊዜ ራስን ከእንቅስቃሴ መገደብና በቤተሰብ ስራዎች መጠመድ የተሻለና ተመራጭ ነው። በአጠቃላይ ጥቅምና ጎዳቱን አመዛዝኖ የተሻለውን መምረጥና ከጭንቀት መዳን መፍትሄ እንደሆነ ጠቁመዋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 25/2012
ጌትነት ምህረቴ
በኮሮና ዘመን ቤት ውስጥ እንዴት ያሳልፋሉ?