ዛሬ በዓለም ላይ በህክምና አገልግሎት አሰጣጣቸው ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ የበለጸጉ አገራትን ጭምር የሚፈታተን አደጋ እያጋጠመ ነው፡፡ የኮሮና ቫይረስ በህክምና ዘርፉ ብቻ ሳይሆን በማህበረሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴም ላይ ትልቅ ፈተና መደቀኑንም ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህጻናትና የአጠቃላይ ቀዶ ህክምና ከፍተኛ ስፔሻሊስትና የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አመዘነ ታደሰ እንደሚሉት የኮሮና ቫይረስ ድንበር የማይወስነው በመሆኑ ኢትዮጵያም የችግሩ ተጠቂ ሁናለች፡፡ የኢትዮጵያ የሕክምና ባለሙያዎችም ማህበርም ይህ የሕክምና ፈተናን ለመቋቋም ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡
የኮሮና ቫይረስ በህብረተሰቡ ብቻ ሳይሆን በህክምና ባለሙያዎችም ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና የሚያደርስ ነው የሚሉት ዶክተር አመዘነ፣ ስለ ቫይረሱ በእውቀትና በጥንቃቄ ላይ የተመሰረተ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ማህበሩ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በበሽታው መከላከልና ሕክምና ዙሪያ ባለሙያዎችን የማሰልጠንና አስፈላጊውን ቁሳቁስ ለማሟላት ጥረት በመደረግ ላይ ነው ብለዋል፡፡ ለአብነትም ባለፉት ሁለት ሳምንታትም 400 ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል ብለዋል፡፡
እንደ ዶክተር አመዘነ ገለጻ፤በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታትም በሁሉም ክልል ለሚገኙ የጤናና የህክምና ባለሙያዎች ኮሮናን በመከላከልና በህክምናው ዙሪያ በህክምና የትምህርት ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡ እነዚህ ሰልጣኞች ደግሞ ሌሎቹን የጤና ባለሙያዎች የሚያሰለጥኑ ይሆናል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ የውይይት መድረኮችን በመክፈት በቫይረሱ የተጠቁ እንደ ቻይናና የአሜሪካ የጤና ባለሙያዎችን ተሞክሮ የማካፈል ስራ እየተሰራ ነው፡፡
በአገሪቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ህብረተሰቡ በቫይረሱ ዙሪያ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ካሉ ምላሽ የሚሰጡ 300 በላይ የጤና ባለሙያ በጎ ፈቃደኛ ተመዝግበው አገልግሎቱን ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙም ገልጸውልናል፡፡
“በሽታው መድኃኒትም ሆነ ክትባት የለውም፣ በቅርብ ይገኛል ተብሎ አይጠበቅም” ያሉት ዶክተር አመዘነ፤ ያለው ብቸኛው አማራጭ ጥንቃቄ ማድረግና አስቀድሞ መከላከል ቢሆንም በኢትዮጵያ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሲባል በመንግስት የተወሰዱ ውሳኔዎችና የጤና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን ምክሮች ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ክፍተቶች ይታያሉ፤መዘናጋቱ እንደ አገር ዋጋ ስለሚያስከፍል መንግስትም ሆነ ህብረተሰቡ ተገቢውን እርምጃና ጥንቃቄ የማድረግ ጉዳይ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
የህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስን ስርጭት አስቀድሞ ለመከላከል ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጫበጫ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል የሚሉት ደግሞ በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ኢብሳ ሙሳ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፤ የጤና ባለሙያዎች ዘንድ መጀመሪያ አካባቢ በቂ የህክምና መከላከያ ቁሳቁሶች ባለመሟላታቸው መደናገጥ ተፈጥሮ ነበር፡፡ በአሁን ጊዜ ለጤና ባለሙያዎች የሚሆኑ የመከላከያ የህክምና ቁሳቁሶችን ለማሟላት ዩኒቨርሲቲው ግዥ ፈጸሞ ከቻይና ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እነዚህ ነገሮች ከተሟሉም ሁሉም የጤና ባለሙያዎች የዘመኑ ወታደር ስለሆንን የስነ ልቦና ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ከኮሮና ለከፋው በኢቦላ ቫይረስ የተጠቁ አገራትን ለመደገፍ ወደ ውጭ አገር መሄዳቸውን አውስተው “እኛ የጤና ባለሙያዎች ከኮሮና ቫይረስ ህዝባችንን ለመታደግ ሙያዊ ስነ ምግባር በጠበቀ መልኩ ህይወት የማዳን ስራችንን በቁርጠኝትን ለማከናወን ዝግጁ መሆን አለብን” ብለዋል፡፡
ሆስፒታሉ ቫይረሱ የሚጠቁ ሰዎች ካሉ ደግሞ ከወዲሁ የዝግጅት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ ለአብነትም በአሁኑ ጊዜ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ባስገነባው ሆስፒታል ለታካሚዎች የሚሆን 100 አልጋዎች ዝግጁ ማድረጉንና አልጋዎቹንም ወደ 300 ለማሳደግ ግዥ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ እየታየ የፖሊስና መከላከያ ሆስፒታሎችን እንዲሁም ዩኒቨርስቲዎችና ጤና ጣቢያዎች ለመጠቀም አማራጭ ዕቅድ መኖሩንም ጠቁመዋል፡፡
ድሬዳዋ ከተማ አንድ ከአውስትራሊያ የመጣ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ስለመያዙ ጥርጣሬ አድሮበት ራሱን በሆቴሉ ለይቶ አቆይቶ እንደነበር አውስተው ይህ ሰው በአሁኑ ጊዜ በቫይረሱ መያዙ በምርመራ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡ የተገናኛቸው ሰዎች እየተለዩ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ እየተደረጉ መሆኑንም በመግለጽ በአካባቢው አስፈላጊውን ጥንቃቄ መደረግ እንደሚኖርበትም መክረዋል፡፡
“አሁን በጣም ጥንቃቄ የምናደርግበት ጊዜ ላይ ነን” ያሉት ዶክተር ኢብሳ “ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” እንደሚባለው ኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋ ከመጣ መቆጣጠር አዳጋች ስለሚሆን ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ምክረ ሀሳባቸውን ለግሰዋል፡፡
ህብረተሰቡ የመንግስት ውሳኔዎችንና የጤና ባለሙያዎችን ሙያዊ ምክር ማለትም ከቤት ያለመውጣትን፣ከአካላዊ ንክኪ መራቅን፣ ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች አለመገኘትን፣እጅን በሳሙና መታጠብን፤ ሳኒታይዘር መጠቀምንና አፍንጫን፣ዐይንና አፍን በእጅ አለመንካትን እንዲሁም የህመም ምልክት የሚታይበት ጊዜ ሰው ቶሎ ወደ ህክምና ተቋማት መሄድን ልክ እንደ “ፈጣሪ ቃል ሳይሸራርፉ በመተግበር” ራስን፣ቤተሰብንና ህዝብን ከቫይረሱ መከላከል ተገቢ ይሆናል” ብለዋል፡፡
አዲስ ዘመን መጋቢት 25/2012
ጌትነት ምህረቴ
የዘመኑ ወታደሮች ዝግጁነት