አዲስ አበባ፡- የብልጽግና ጉዞው እውን እንዲሆን እያንዳንዱ ዜጋ ጤናውን እንዲጠብቅና ግድቡንም ለማጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቀረቡ። የፕሮጀክቱ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት ዘጠነኛ አመትን ምክንያት በማድረግ ትላንት በውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አዳራሽ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ እንደሚሉት፤ የግድቡ የሲቪልና የኤሌክትሮ መካኒካል ስራዎች ግንባታ በመፋጠን ላይ ይገኛሉ። በዚህም መሰረት በአሁኑ ወቅት የዋናው ግድብ ኮንክሪት ሙሌት 82 በመቶ፣ የሃይል ማመንጫዎች ግንባታም የቀኙ 71 በመቶ፣ የግራው 86 የደረሰ ሲሆን፤ የጎርፍ ማስተንፈሻው 86 በመቶ እና የኮርቻ ግድቡ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል። አሁን እየተሰራ ያለው የማስተካከያ ስራ ነው። ይሄ አጠቃላይ የሲቪል ስራውን ወደ 86 ነጥብ 6 በመቶ አድርሶታል።
እንደ ኢንጂነር ክፍሌ ገለጻ፤ የግድቡ ስራ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ፈጥሮ የነበረው የብረታብረት ስራን ችግር ከመፍታት አኳያ ሰፊ የእርምት እርምጃ ተወስዷል። ዛሬ ላይ በዚህም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራውን በሚመለከትም ከ44 በመቶ በላይ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ዘጠኝ ተርባይንና ጄኔረተሮችም ተፈብርከው የተከላ ሂደት ላይ ናቸው። ለቅድመ ኃይል ማመንጫ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሁለት ተርባይንና ጄኔሬተሮችን በተመለከተም መገጣጠም የተጀመረ ሲሆን፤ ማስተላለፊያ አሸንዳው ተጠናቅቆ ኮንክሪት ሙሌት ተጀምሯል። እንደ አጠቃላይ ሲታይም የግድቡ ስራ አፈጻጸም 72ነጥብ4 በመቶ ላይ ደርሷል። ለዚህ ደግሞ የግድቡ ስራተኞች ትጋትና የህዝቡ ተሳትፎ ትልቅ አቅም የፈጠረ ሲሆን፤ ይሄው ድጋፍ ሊቀጥል ይገባል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ፕሮጀክቱ ሲጀመር ሶስት የማዕዘን ድንጋዮች አሉት። አንደኛው፣ ዛሬ ዘጠነኛ ዓመቱን የያዘውን ፕሮጀክት የማስጀምር ስራ ሲሆን፤ ሁለተኛው ጉዳይ በመጀመሪያው የውል ስምምነት መሰረት ከአራት ዓመት በኋላ የመጀመሪያውን ኃይል ማመንጨት፤ እንዲሁም እኤአ በ2017 ፕሮጀክቱን ማጠናቀቅ ሶስተኛው የማዕዘን ድንጋይ ነው። ይሁን እንጂ የፕሮጀክቱ ውል ሲፈጸም በነበሩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በታሰበው ጊዜ ውሃ መያዝና ስራውን ማጠናቀቅ አልተቻለም። ሆኖም በዚህ ሁለት ዓመት በተወሰደው የእርምት እርምጃ ችግሩን ማቃለልና አቅም ያላቸውን ተቋራጮች በማስገባት ስራው እንዲፋጠን እየተሰራ ነው።
በዚህም ከወራት በኋላ ውሃ ለመያዝ የሚያስችል ስራ
እየተሰራ ሲሆን፤ አሁን ላይ ተሆኖ ሲታይም ተግባሩ በታሰበው መሰረት ውሃ መያዝም ሆነ የቅድመ ኃይል ማመንጨት እቅዱ በታሰበው መሰረት እንደሚከናወን ይታመናል። ለዚህም ከማስተካከያና ጥገና ስራ ጀምሮ የሚከናወኑ ተግባራት በጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እየተከናወኑ ይገኛል። ምክንያቱም በታሰበው ወቅት ውሃ መያዝ ካልተቻለ ሂደቱን ለአንድ ዓመት የሚያራዝመው ከመሆኑም ባለፈ፤ በአንድ ዓመት ውስጥ ግድቡ የሚያመነጨውን ወደ አንድ ቢሊዮን የሚገመት ኃይል ያሳጣል፤ ለኮንትራክተሮችም ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፈል ያደርጋል። በመሆኑም ስራው ይሄንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እየተከናወነ ያለ ነው።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ በበኩላቸው እንደሚሉት፤ ህዝቡ ግድቡ “የፋይናንስ ምንጩም፣ መሃንዲሱም እኛው” ተብሎ ሲጀመር ከመንግስት ጎን ሆነው ሲደግፉና ሲያበረታቱ ነበር። አሁንም ሙሉ ድጋፍ እያደረጉ ነው። ለምሳሌ፣ የግብጽን ኢሞራላዊና ኢፍትሃዊ ጫና ተገንዝቦ እና የአሜሪካንንም ያልተገባ ውሳኔና ጫና ተቃውሞ መሆን የለበትም ብሎ ቁጣውን ገልጿል። አሁንም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሆነው የግድቡን ጉዳይ አብይ አጀንዳቸው አድርገው በቁጭት እየሰሩ ነው። ምሑራንም ሆኑ መላው ህዝብ በገንዘብ፣ በእውቀት፣ በጉልበትና ዲፕሎማሲ ዘርፉ የማይተካ ሚና እየተጫወቱ ይገኛል።
እንደ ወይዘሮ ሮማን ገለጻ፤ የተፈጠረውን ችግር መሰረት አድርጎ የታየውን መቀዛቀዝ ምክንያት በማድረግ 180 መድረኮች፣ ከ300 በላይ ገጽ ለገጽ ውይይቶች፣ ከህጻን እስከ ወታደር፣ ከፖለቲካ ፓርቲ እስከ ሲቪል ተቋማት ውይይት ተደርጓል። ሁሉም ግድቡ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋሉ፤ ለዚህም በጉልበትም፣ በገንዘብም፣ በሙያም ጭምር የድርሻቸውን ለማበርከት አምነው እየሰሩ ይገኛል። በዚህ ዓመት እስካሁን ብቻ 405ነጥብ9 ሚሊዮን ከህብረተሰቡ በስጦታና በቦንድ ተገኝቷል። ከዚህ ውስጥ 17 ሚሊዮኑ ከውጭ ካሉ ኢትዮጵያውያን የተገኘ ነው። እስካሁን ባለው ሂደትም 13 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ከህዝቡ ሊገኝ ችሏል። ይህ ደግሞ ህዝቡ በገባው ቃል መሰረት እየሰራ መሆኑን ያሳያል።
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ለመልማት በምትሰራው ስራ ውስጥ አንዱና ትልቁ የህዳሴው ግድብ ነው። የዓባይ ወንዝ ገባር ወንዞች አስተዋጽዖ የሚያደርጉበት ወንዝ ነው። ግድቡም እነዚህ ወንዞች ሁሉ አስተዋጽኦዋቸውን ካበረከቱ በኋላ ያለው ቦታ ላይ የሚከናወን ትልቅ የኃይል ማመንጫ ግድብ ነው። ይህ ሲሆን ደግሞ ድንበር ተሻጋሪ ወንዝ ላይ እንደመሆኑ ጭቅጭቅ ማስነሳቱ የማይቀር ነው። ሆኖም ግብጽ የቀደመ የቅኝ ግዛት ተጠቃሚነትን የታሪክ ሁነት ፍላጎት ላይ ተመስርታ የምትንቀሳቀስ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ግን ሉዓላዊ መብቷን የመጠቀም፤ ነገር ግን ሌሎች ላይ የጎላ ጉዳት ያለማድረስ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ላይ ተመስርታ እየሰራች ነው። አሁን ያለው የድርድር ሂደትን ተከትሎ የውሃ ድርሻ ላይ ድርድር እየተደረገ ነው የሚለው ሀሰብ የተሳሳተና ከእውነት የራቀ ሲሆን፤ ድርድሩ የውሃ ክፍፍል ላይ ሳይሆን በግድቡ አጠቃላይ የቴክኒክ ጉዳይ ላይ ያተኮረ፤ የኢትዮጵያን ጥቅምም ባስከበረ መልኩ እየሄደ ያለ ነው።
ኃላፊዎቹ እንደገለፁት‹‹ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ እንዲሉ››፤ ዓለምን ያስጨነቀውና ኢትዮጵያም በስጋት ውስጥ ያለችበትን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ከመከላከል አኳያ ህዝቡ አስቀድሞ ሊጠነቀቅና ራሱን በመጠበቅ ቤተሰብና አገሩን ሊጠብቅ ይገባል። ለዚህ ደግሞ ችግሩን ከመከላከል አኳያ መንግስት የሚሰጠውም መመሪያ መከተል፤ ከተቻለም በቤት መቀመጥ፤ የግድ ካለም አካላዊ ርቀትን ጠብቆ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ይመክራሉ። እናም ህዝቡ ከምንም በበለጠ ጤናውን ሊጠብቅ፤ የብልጽግና ጉዞ መብራቱ የሆነውን ግድብም ሊጠብቅ ይገባል። ‹‹በጥረታችን ጤናችን ይጠበቃል፤ ግድባችንም ይጠናቀቃል፤›› በሚል መርህም ሁሉም ሊሰራ ይገባል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 25/2012
ወንድወሰን ሽመልስ
ጤናችን እንዲጠበቅና ግድባችንም እንዲጠናቀቅ እያንዳንዱ ዜጋ እንዲረባረብ ጥሪ ቀረበ