አዲስ አበባ፡- በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ባላቸው አካላት የተጀመረው የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ።
ትላንት የተጀመረውን በኪነጥበብ ባለሙያዎች የሚሰጥ የግንዛቤ ማስጨ በጫ አስመልክቶ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት ሰሞኑን በሚኒስትሮች፤ በከንቲባዎችና በከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ሲደረግ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። እስካሁን በተሰሩት ስራዎች በእጅ መታጠብና መጨባበጥ ላይ የታዩ አበረታች ለውጦች ቢኖሩም አካላዊ ፈቀቅታ ላይ ግን ብዙ የሚቀር በመሆኑ ግንዛቤ የመፍጠሩ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ሀያ አርቲስ ቶችን ያካተተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሰራ ሲሆን እስከ እሁድ ሁሉ በስራ መውጫ ሰዓት ለህብረተሰቡ የጥንቃቄ መልእክቶችን እያስተላለፉ መሆናቸውን አርቲስት ሰራዊት ገልጿል። በተጨማሪም አስራ ሶስት አርቲስቶች ተሰባስበው የሰሩት የግንዛቤ መፍጠሪያ ማስታወቂያ መዘጋጀቱንና ከሁለት ቀን በኋላ የሚለቀቅ መሆኑን በመግለጽ በድምጻውያንም በኩል በርካታ ስራዎች እየተዘጋጁ መሆ ኑን ጠቁመዋል።
አካላዊ ፈቀቅታን ለመተግበር ከኢትዮጵያውያን ባህልና አኗኗር አንጻር አስቸጋሪ ቢሆንም በተደጋጋሚ ግንዛቤ በመፍጠር መተግበር እንዳለበትና አጠቃላይ በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮሮናን ቫይረስ ስርጭት የመከላከል ስራ በክልሎችም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበት አርቲስት ሰራዊት አሳስበዋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 25/2012
ራስወርቅ ሙሉጌታ
ግንዛቤ ፈጠራው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ