መገናኛ ብዙሃን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ላይ እያደረሰ ስላለው ጉዳትና ዜጎች ማድረግ ሥላለባቸው ቅድመ ጥንቃቄ መረጃ በመስጠት ላይ ትኩረት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ ለኢትዮጵያ ደግሞ በዚህ ወቅት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የምስረታ በዓልና ግብጽ አጋጣሚዎችን በመጠቀም የግድቡን ግንባታ ለማስተጓጎል የምታደርገው እንቅስቃሴ ሌላው ትልቅ አጀንዳ ነው፡፡ መገናኛ ብዙኃን እነዚህን ሁለት ትላልቅ ጉዳዮች እንዴት አጣጥመው እያቀረቡ ይሆን? ካነጋገርናቸው የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት አብዛኞቹ የግድቡን ጉዳይ በዘገባቸው እንዳልዘነጉት ይናገራሉ፡፡ የሰው ህይወትን ለማዳን በሚደረገው ርብርብም የማይተካ ሚናቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡
የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ አማረ አረጋዊ ምንም እንኳን ወቅታዊ በሆነው ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ አግባብ ቢሆንም ሀገራዊ
ጉዳዮችን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ሽፋን መስጠት መዘንጋት የለበትም ይላሉ፡፡ ሁለቱም ጉዳይ ለኢትዮጵያ በእኩል ደረጃ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለውም ያምናሉ፡፡ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጾታ፣ ዕድሜ፣ብሄር፤ኃይማኖት፣ቀለም በአጠቃላይ የሰው ፍጡርን ሳይለይ የሚጎዳ በመሆኑ በሽታውን ለመከላከል የጋራ ትብብርን እንደሚጠይቅ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብም እንዲሁ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በጋራ ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ተቋማቸው ሁለቱንም ትላልቅ ጉዳዮች ሽፋን እየሰጡ ያለበትን ሁኔታ አስታውቀዋል፡፡
ድርጅታቸው በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች በሚያሳትመው ጋዜጦቹ በዜና እና በተለያዩ አምዶች ያስተናግዳል፡፡ ኢትዮጵያ የተፋሰሱን ሀገራት ጥቅም በማይነካ መልኩ ግድቡን እየገነባች መሆኑንና በግብጽ በኩል የግድቡን ሥራ ለማስተጓጎል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ቦታ እንደሌላቸው ጭምር የተለያዩ አካላትን በማነጋገር በማቅረብ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ እንደሆነ
አስረድተዋል፡፡ ‹‹በበሽታው ምክንያት የዕለት ፍጆታዎች ዋጋቸው እየናረ ነው፡፡ከአቅርቦት ጋር በተያያዘም ህገወጥነት እየተስተዋለ ነው፡፡ይህ ሁሉ ችግር እያለ ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጉዳይ መነሳት የለበትም አይባልም፤›› ይላሉ፡፡
ተቋማቸው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አደገኛነት ግምት ውስጥ ባስገባ ሀገራዊ ጉዳይንም በንቃት በመከታተል፣ የተፈጠረው በሽታም በቀጣይ ሊያስከትል የሚችለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በማመላከትና መወሰድ ስላለበት እርምጃ ከአንድ የመገናኛ ብዙኃን የሚጠበቀውን ተግባር እንደሚወጣም ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት የአዲስ አበባ ዜና ዴስክ ምክትል ዋና አዘጋጅ አቶ አብይ ጌታሁን በበኩላቸው በተቋሙ የውስጥ አሰራር (በኤዲቶሪያል) ኢትዮጵያ የበሽታውን ወረርሽኝ ፈተና ለመወጣት የምታደርገውን ጥረት በማሳየት ውስጥ ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮችም የዜና ሽፋን ማግኘት እንዳለባቸው አቅጣጫ በማስቀመጥ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የዜና ሽፋናቸው በአብዛኛው በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ላይ ቢያተኩርም በታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ መረጃ ለህዝቡ ተደራሽ በማድረግ በኩልም ከሌሎች የዜና ሽፋኖች በተለየ ተንቀሳቅሷል፡፡
የቦንድ ሽያጭ ሳምንትን አስመልክቶ በተሰጠ የዜና ሽፋን ዜጎች ለግድቡ ግንባታ የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ እንደሚያጠናክሩ መረጃ መሰብሰቡን አቶ አብይ ተናግረዋል፡፡ ግብጽ እያነሳች ባለው ጉዳይ ላይም ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ምን መሆን እንዳለበት ምሁራንን በማነጋገርና በተለያየ መልኩ ዘገባዎችን በማቅረብ የግድቡ ጉዳይ እንዳይዘነጋ፣ዜጎችም ጉዳያችን ነው ብለው የሚጠበቅባቸውን እንዲያበረክቱ ተቋሙ በዘገባው ያልተቆጠበ ጥረቱን እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክተር ሞላልኝ ከሰተብርሃን ናቸው::
እርሳቸው እንዳሉት ተቋማቸው ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሽፋን ቢሰጥም ከዘጠኝ አመት በፊት ግንባታው የተጀመረው ግድብም ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ተስፋ እንደሆነ ግምት ውስጥ ባስገባ የተለያዩ አጀንዳዎችን በመቅረጽ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የአሀዱ ሬዲዮ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥበቡ በለጠ ኢትዮጵያ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችዋ ከአባይ ጋር የተሳሰረ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ሬዲዮ ጣቢያቸውም ይህንኑ ግምት ውስጥ በማስገባት ስሙን እንደሰየመና በወንዞች ዙሪያ ታሪክን በማጣቀስ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በማስተሳሰር ዘገባዎችን የሚያቀርብበት በሳምንት ሁለት ጊዜ ቋሚ ፕሮግራም እንዳለው ተናግረዋል:: ፕሮግራሙ በኮሮና ቫይረስ በሽታ አለመቋረጡንም ተናግረዋል፡፡
የግሉ የሬዲዮ ጣቢያ ከመዝናኛ ዓለሙ ወጣ ባለ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሚና እንዲኖራቸው መደረግ አለበት የሚሉት አቶ ጥበቡ የሬዲዮ ጣቢያዎች ፈቃድ የሚያገኙት መዝናኛ በሚለው ተገድበው እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ እንደግብጽ ያሉ ሀገራት ህዝባቸውን የሚያነቁበት አንዱ መሳሪያቸው የሬዲዮ መገናኛ ብዙሃን እንደሆነ መዘንጋት እንደሌለበት አስታውሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የግሉ የሬዲዮ ጣቢያዎች ሀገር ችግር ውስጥ ስትገባ ከዚያ በሚያወጣ መልኩ ለመንቀሳቀስ አቅም ያላቸው ሆነው እንዲወጡ ባለመደረጉ የሚፈለገውን ያህል ተንቀሳቅሰዋል ብለው አያምኑም፡፡ መንግሥት በዚህ በኩል ማሰብ እንዳለበት ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡
‹‹ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ለማውራት ሰው በህይወት መኖር አለበት›› ያሉን ደግሞ የድሬ ቲዩብ ኦንላይን ዋና አዘጋጅ አቶ ፍሬው አበበ ናቸው፡፡ ‹‹የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ሳይቀሩ አጀንዳቸውን ያደረጉት የኮሮና ወረርሽኝ በሽታ ጉዳይ ላይ ነው፡፡ የእኛ ተቋምም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡›› ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል:: ስለሌላ ጉዳይ መረጃ መስጠት በሽታውን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ያደበዝዘዋል፡፡ በህዝብም ተቀባይነት አይኖረውም ብለው ያምናሉ፡፡
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ የሚተላለፉ መረጃዎች ሚዛን የደፋ ቢሆንም ተቋማቸው ትኩረት ከሰጣቸው አምስት አቅጣጫዎች አንዱ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ የሚሰጠው ሽፋን እንደሆነ የገለጹልን ደግሞ የዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት የዜና እና ወቅታዊ ፕሮግራም ክፍል
አዲስ ዘመን መጋቢት 24/2012
ለምለም መንግሥቱ
የሀገር ህልውናን ለማስቀደም ያላመነቱት መገናኛ ብዙሀን