ጋምቤላ (ኢዜአ)፡- የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለ14 ቀናት ተፈፃሚ የሚሆኑ የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉን አስታወቀ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ትናንት ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ውሳኔዎቹ የተላለፉት የክልሉ መንግሥት ካቢኔ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ ሲሆን ተግባራዊ የሚሆኑትም ከመጋቢት 23/ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ነው።
በውሳኔው መሰረትም ከመሃል ሀገርና ከአጎራባች ክልሎች ወደ ክልሉ የሚገቡና የሚወጡ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል።
ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሚኒባሶች ሙሉ ለሙሉ ሥራቸውን እንዲያቆሙ እንዲሁም የሞተር ተሽከርካሪዎችም ከአንድ ሰው ሌላ እንዳይጭኑ መወሰኑን አስታውቀዋል።
ከክልል ወደ ዞኖችና ወረዳዎች የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ቀደም ሲል ሲጭኑ ከነበረው የሰው ቁጥር በግማሽ እንዲቀንሱ ገደብ ተጥሎባቸዋል።
የሺሻ፣ ጫት፣ ጭፈራና መጠጥ ቤቶች ለቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው በመሆኑ እንዲዘጉ መወሰኑንም ገልጸዋል።
ጫት ከአጎራባች አካባቢዎች ወደ ክልሉ እንዳይገባ መከልከሉንም አመልክተዋል።
ከፍተኛ የሰራተኛ ቁጥር ባለባቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች በእድሜ የገፉ፣ ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች ሥራቸውን በቤታቸው እንዲያከናወኑም ተወስኗል።
“በክልሉ የሚገኙ ስደተኞች እንደ ሀገር በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ከአሁን በፊት ከነበራቸው ልቅ እንቅስቃሴ የሚገደቡ ይሆናል” ብለዋል።
ከበሽታው ጋር በተያያዘ የንግድ ማህበረሰብ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርግ ክትትሉ እንዲጠናከር መወሰኑንም አቶ ኡሞድ ተናግረዋል።
በክልሉ መንግሥት የተላለፉት ውሳኔዎች ተፈፃሚ እንዲሆኑ ለጸጥታ አካላት መመሪያ መተላለፉንም ርዕሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።
መንግሥት ላስተላለፋቸው ውሳኔዎች ተፈፃሚነት ሁሉም ዜጋ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም መልዕክታቸውን በማስተላለፍ፤ ውሳኔው ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት እንደሚቆይም ተገልጿል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 24/2012
የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ኮሮናን ለመከላከል ውሳኔዎችን አሳለፈ