አዲስ አበባ፡- በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና በአባይ ወንዝ ዙሪያ ኢትዮጵያ የምታከናውናቸው የዲፕሎማሲ ሥራዎች በዋናነት የተፋሰሱን ሀገራት ማዕከል ያደረጉ መሆን እንዳለባቸው የዘርፉ ምሁራንና ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ ሀገራዊ አንድነት ማጠናከርም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና በአባይ ወንዝ ዙሪያ ለአዲስ ዘመን አስተያየታቸውን የሰጡት የስራቴጂክ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ጉዳዮች ጥናት ክፍል ኃላፊ አቶ ልዑልሰገድ ግርማ እንደተናገሩት፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ እና በአባይ ወንዝ ዙሪያ ኢትዮጵያ የምታከናውናቸው የዲፕሎማሲ ሥራዎች በዋናነት የተፋሰሱን ሀገራት ማዕከል ያደረጉ ሊሆን ይገባል፡፡
በግድቡ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን መካከል የተደረጉ የሶስትዮሽ ውይይቶችና ድርድሮች አሁንም መቀጠል አለበት ያሉት አቶ ልዑልሰገድ፤ ከሶስትዮሽ ውይይቶች፣ ድርድሮችና ውይይቶች ጎን ለጎን ኢትዮጵያ የምታከናውናቸው የዲፕሎማሲ ሥራዎች በዋናነት የተፋሰሱን ሀገራት ማቀፍ አለባቸው:: በተለይም በወንዙ ዙሪያ የሚካሄዱ ውይይቶችና ድርድሮችም ሁሉንም የተፋሰሱን ሀገራት ሊያካትቱ ይገባል ብለዋል፡፡
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮችንና ውይይቶችን ግብጽ በመለጠጥ የውሃ ክፍፍል ሀሳብ እያነሳች መሆኑን ያነሱት አቶ ልዑልሰገድ፤ በተለይም የውሃ ክፍፍል ዙሪያ ሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት በሌሉበት ሁኔታ ውይይትም ሆነ ድርድር ሊካሄድ አይገባም ብለዋል፡፡ እንደ ልዑልሰገድ ማብራሪያ፤ የተፋሰሱን ሀገራት ከኢትዮጵያ ጎን በማሰለፍ የተፋሰሱ ሀገራት ተመሳሳይ አቋም እንዲይዙ ማድረግ ኢትዮጵያን ውጤታማ ያደርጋታል፡፡ የተፋሰሱን ሀገራት ከጎን የማሰለፍ ሥራ ከተሰራ በኋላ ኢጋድአባል ሀገራት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ስለ ግድቡ እና ወንዙ እውነተኛ መረጃ እንዲኖረው በትኩረት ሊሰራ ይገባል::
የተፋሰሱ ሀገራት ተመሳሳይ አቅም እንዲይዙ ከተደረገ በኋላ ኃያላን ሀገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የኢትዮጵያን ሁኔታና በወንዙ የመጠቀም መብቷ በተሳሳተ መንገድ እንዳይረዱትና የተሳሳተ ግንዛቤያቸው እየሰፋ እንዳይሄድ ዲፕሎማሲ ወሳኝ ሚና እንዳለውም አብራርተዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ ባለቤት መሆኗንና የመጠቀም መብት እንዳላት ለሌሎች ሀገራት ለማሳወቅ የጀመረቻቸው መልካም ሥራዎች መኖራቸውን ያነሱት አቶ ልዑልሰገድ ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብለዋል፡፡ ለብዙ ዓመታት በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የሲቪክስ፣ ፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት እንዲሁም ፍልስፍና ሲያስተምሩ የቆዩት አቶ ግዴይ ደገፉም የአቶ ልዑል ሰገድን ሀሳብ ያጠናክራሉ፡፡ የአባይ ተፋሰስ ሀገራት በግድቡ እና በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም እንዲይዙ ማድረግ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ይናገራሉ፡፡ሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት ስለ ወንዙ አጠቃቀም ተመሳሳይ አቋም ከያዙ ግብጽ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የምታደርገው ጥረት ፍሬ አልባ ይሆናልም ብለዋል፡፡እንደ አቶ ግደይ ማብራሪያ ኢትዮጵያ የተፋሰሱን ሀገራት ከጎኗ ከማሰለፍ ባሻገር ቋሚ ወዳጆቿን ከጎኗ ማሰለፍ አለባት፡፡ ኢትዮጵያ በችግሯ ጊዜ ከጎኗ ሲቆሙ የነበሩ ወዳጅ ሀገሮች አሏት፡፡ ሁል ጊዜ ስለኢትዮጵያ የማይዋዥቅ አቋም ያላቸው ሀገራትን ለይታ ከጎኗ እንዲቆሙ ልታደርግ ይገባል::በስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ኢንስትቲዩት የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ጉዳዮች ጥናት ክፍል ኃላፊ አቶ ልዑልሰገድ ግርማ አክለውም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከዲፕሎማሲው በላይ የኢትዮጵያዊያን አንድነት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ የፖለቲካ ርዕዮት አለም፣ የሃይማኖት፣ የብሄር፣ የቋንቋ ልዩነት ወደ ጎን በመተው ሁሉም በግድቡ እና በወንዙ ጉዳይ ተመሳሳይ አቋም ሊኖረው ይገባል፡፡ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በማድረግ አንድነታቸውን ማጠንከር የሀገሪቱን የመደራደር አቅሟንም ያጠናክራልም ብለዋል አቶ ልዑልሰገድ፡፡የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የፍልስፍና ምሁሩ ግዴይ ደገፉ በበኩላቸው ግብጾች ከዚህ ቀደምም በኢትዮጵያውያን መካከል ያሉ ልዩነቶችን ተጠቅመው ሀብታቸውን እንዳይጠቀሙ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ አሁንም በአንዳንድ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ያሉ ልዩነቶች ለግብጾች ሌላ እድል እንዳይከፍት ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡ የፖለቲካ ኃይሎች ልዩነቶቻቸውን በማጥበብ ተቀራርበው ሊሰሩ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡አዲስ ዘመን መጋቢት 24/2012መላኩ ኤሮሴ
የአባይ ዲፕሎማሲ የተፋሰሱን ሀገራት ማዕከል ማድረግ አለበት •የውስጥ አንድነትን ማጠናከር አለበት