‹‹በአሁኑ ወቅት የገጠመን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እጅጉን ከባድና ፈታኝ ቢሆንም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ከመገንባት አያግደንም፤ እንዲያውም የግድቡ ግንባታ በተቻለ መጠን ተጠናክሮ መቀጠለ አለበት፤›› በማለት ሀሳቧን የምትገልጸው ወይዘሮ የኔነሽ ማሞ፤ ነዋሪነቷ በደብረብርሃን ከተማ ሲሆን የ ‹‹የኔ ጋርመንትስራ›› አስኪያጅ እና ባለቤት ናት።
አሁን ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዓለምን እያስጨነቀ ያለው የኖቭል ኮሮና ቫይረስ
ወረርሽኝ በተለይም ‹‹ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ከባድ ፈተና ቢሆንም ፈተናውን ተሻግረን በጋራ የጀመርነውንና የእያንዳንዳችን ግዴታ የሆነውን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን እናጠናቅቃለን። ይህን ለማድረግ ደግሞ በቅድሚያ መንግሥትና የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡንን ምክር በመተግበር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኙ እንዳይዛመት መከላከል ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል፤›› ብላለች፡፡
ሁሉም ሰው የበኩሉን መወጣት ከቻለ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ለአፍታም ቢሆን ሳይዘነጋ ይቀጥላል የምትለው የኔነሽ በአሁኑ ወቅትም ህብረተሰቡ ከፍተኛ የሆነ ተሳትፎ እያደረገ ያለበትና ሥራው ተጠናክሮ የቀጠለበት ሁኔታ መኖሩን አምናለሁ ስትል ሀሳቧን አጋርታናለች፡፡ “እውነት ለመናገር እኔ በግሌ ከዚህ ቀደም በአባይ ግድብ ዙሪያ የነበረኝ አመለካከት አሁን ካለኝ በጣም ይለያል። ብዙም ተሳትፎ አድርጌያለሁ ለማለት አልችልም። በአሁኑ ወቅት ግን የአባይ ግድብ ጉዳይ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በመረዳቴ ከሰራተኞቼ ጋር በመሆን የተሻለ ተሳትፎ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነን” ትላለች።
ህብረተሰቡ በአሁኑ ወቅት በአባይ ግድብ ዙሪያ ያለው ንቃተ ሕሊና ያደገ በመሆኑ ተነሳሽነቱ ጨምሯል። በመሆኑም በቤተሰብ፣ በጓደኛና በሥራ ቦታዎች ላይ ህብረተሰቡ ስለ አባይ ግድብ ይወያያል። ከመወያየት ባለፈም የበኩሉን በመወጣት ግድቡን ለማጠናቀቅ ያለውን ዝግጁነት በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገልፅ ይታያል የምትለው የኔነሽ፤ እርሷም በበኩሏ የሞባይል ካርድ በሞላች ቁጥር በ8100A የገንዘብ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቃለች፡፡
‹‹ይህ ብቻ በቂ አይደለም እንደ ድርጅትና መስሪያ ቤት ብዙ ይጠበቅብኛል። በተለይም እንደ ቤተሰብ ልጆች ያሉኝ በመሆኑ ለልጆቼ የማወርሰው ታሪክ ሊኖረኝ ይገባል። ይህ ታሪክ ደግሞ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ነው። ስለዚህ ለግድቡ ግንባታ አስፈላጊ በሆነው ሁሉ ተሳትፎዬን አጠናክሬ በመቀጠል ታሪክ ለመስራት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መዘጋጀቷን በመግለፅ ሀሳቧን ቋጭታለች።
መቆም የለበትም ለጊዜው ሥራ ስለቆመ ነው እንጂ በአቅማችን ለመርዳት እየተዘጋጀን ነው፤ ሁሉም ሰው የራሱን ድርሻ መወጣት አለበት ሊያስቆመን የሚችል ሀይል የለም እኔ ለምሳሌ ብዙም ግንዛቤ አልነበረኝም
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአገራችን ኢትዮጵያ ከመከሰቱ አስቀድሞ ህብረተሰቡ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን አንድ ደረጃ ለማድረስ ከፍተኛ የሆነ መነሳሳት ፈጥሮ የተንቀሳቀሰበት ሁኔታ ነበር፤ ህብረተሰቡ በሕዳሴ ግድቡ ላይ የነበረው መነቃቃት ጥሩ መንፈስ ፈጥሮ እንደነበር የሚናገሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህሩ ዶክተር ወልደአብ ተሾመ ናቸው።
‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ በህብረተሰቡ ላይ የተፈጠረው መነቃቃት ጥሩ ነው›› የሚሉት ዶክተር ወልደአብ፤ ይህም ማለት ኢትዮጵያን ጨምሮ ሶስቱ አገራት ሲደራደሩ አሜሪካ ከአደራዳሪነት ወደ ወሳኝነት በመሄዷ በህብረተሰቡ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ቁጭት ተፈጥሯል። ከዚህም ባለፈ አሜሪካን የኢትዮጵያን እጅ ጠምዝዛ ለግብፅ ሁኔታዎችን ማመቻቸቷ ኢትዮጵያውያኑን እጅግ በማስቆጣት መነቃቃት ውስጥ አስገብቷል። በዚህም ህብረተሰቡ ልዩነቶቹን ወደ ጎን በመተው አንድነቱን አጠናክሮ ግድቡን ማጠናቀቅ እንዲችል አቅም እየሆነው ነው፤››፡፡
ይሁንና በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ጨምሮ ዓለምን እያስጨነቀ የመጣው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ህብረተሰቡ ቅድሚያ እየሰጠ ያለውና መስጠትም ያለበት ለደህንነቱ ነው። በመሆኑም በአሁኑ ወቅት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ አይደለም። ምክንያቱም አሁን ላይ ህብረተሰቡን አስጨንቆ የያዘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በህብረተሰቡ ላይ የጤና፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያሳርፍ እና ከዚህም በላይ የሰው ልጅን ሕይወት ሊያጠፋ የተዘጋጀ መሆኑን ያብራራሉ።
በመሆኑም አሁን ያጋጠመን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በጊዜ መገታት ካልቻለ በማህበረሰቡ ላይ የሚያስከትለው ተፅዕኖ የሚታየው ከአንድ እና ከሁለት ወራት በኋላ ነው። ስለዚህ አሁን ላይ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው የሰዎች ደህንነት ላይ በመሆኑ መከላከሉ ላይ አበክረን መስራት አለብን። ምክንያቱም በግለሰብም ይሁን በማህበረሰብ ደረጃ አሁን ላይ ልናስብ የሚገባን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በፍጥነት ወጥተን ወደ ሰላማዊ ህይወት የመመለስና ያለመመለስ ጥያቄ መሆኑን የገለፁት ዶክተር ወልደአብ፤
እርግጥ ነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 72 በመቶ የደረሰ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እንዲሁም አሜሪካን ባደረገችው ያልተገባ እጅ ጥምዘዛ ህብረተሰቡ ተነሳሽነቱ የጨመረበትና የግድቡን ግንባታ ዳር ለማድረስ ቆርጦ የተነሳበት በጣም ጥሩ ጊዜ እንደነበር እና ነገር ግን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ደግሞ እንቅፋት እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከተበሰረበት ጊዜ ጀምሮ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተቋርጦ የማያውቅና እስካሁን ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴም እየተደረገ መሆኑን የገለፁት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሃም ናቸው።
በአሁኑ ወቅት የገጠመን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሰዎችን እንቅስቃሴ የሚገድብ ከመሆኑም በላይ በጤና፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ሕይወት ላይ የሚያሳድረው ጫና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፤ ይሁንና ህብረተሰቡ በአሁኑ ወቅት እቤቱ ተቀምጦ በ8100A እየተሳተፈ መሆኑን እና የተለያዩ ባለሀብቶች በስጦታ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ህብረተሰቡ በጋራ ወጥቶ የቦንድ ግዥ ለመፈፀም የተቀዛቀዘ ቢመስልም በኢትዮጵያ ልማት ባንክና በንግድ ባንኮች የቦንድ ሳምንት መኖሩን ገልፀው፤ ዘንድሮ የቦንድ ሳምንትን ለየት የሚያደርገው የግራንት እና የቦንድ አካውንት ይፋ መደረጉ ሲሆን፤ ህብረተሰቡ በእነዚህ አካውንቶች ከንክኪ ነፃ በሆነ መንገድ ቤታቸው ተቀምጠው በግራንት አካውንት 1000291929609 ስጦታ ማበርከት የሚችሉ ሲሆን፤ የቦንድ ግዥ ለመፈፀም ደግሞ 1000291927738ን መጠቀም እንደሚችሉ አብራርተዋል።
በመጨረሻም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በየዓመቱ ግድቡ በሚገነባበት ጉባ ላይ ሲከበር የቆየ መሆኑን አስታውሰው፤ ባጋጠመን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ለዘጠነኛ ጊዜ የሚከበረው በዓል አጠቃላይ ግድቡን አስመልክቶ በየቤቱ የሚደርሰው ሚዲያ እንደመሆኑ ስለግድቡ የተለያዩ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በዓሉን በደማቅ ሁኔታ እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 24/2012
ፍሬህይወት አወቀ
የኮሮና ቫይረስ ያልገደበው የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ