በቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ የተፈቀደላቸው የመንግሥት ሠራተኞች ቤተሰባቸውንና ማህበረሰቡን ከኮሮናቫይረስ እንዲከላከል በማገዝ የማህበራዊና ሰብአዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቀርባለሁ ።
መንግሥት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የፌዴራል የመንግሥት ተቋማት ሠራተኞቻቸው ሥራቸውን እቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ፣ በቢሮ ሆነው የሚሰሩት ደግሞ ከአካላዊ ንኪኪ እንዲርቁ ውሳኔ አስተላልፏል።
በቤት እንዲሰሩ ከተፈቀደላቸው ሠራተኞች ጋር እንዴት እንደሚገናኙና በቢሮ የሚሰሩ ሠራተኞች በምን ሁኔታ እየሰሩ እንደሆነ ለማወቅ በአካል፣ በስልክና በኢሜል እየተከታተልን ነው ።
በዚህ መሰረት ተቋማት የቫይረሱን ስርጭት በመከላከል ሂደት ላይ የሚታዩባቸው ክፍተቶች እንዲሻሻሉ ግንዛቤ እየሰጠን ነው ።
የካይዘን ኢንስቲትዩትን በጎበኙበት ወቅት ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ተቋማቱ ቫይረሱን ለመከላከል በመንግሥት የወጡ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ጥሩ አፈፃፀም እያሳዩ ነው።
ይሁን እንጂ ሰራተኞቹ ከአካላዊ ንክኪዎች ራሳቸውን ከማራቅና በቤታቸው በመወሰን ቫይረሱን በመከላከል ረገድ ሙሉ በሙሉ ውጤታማ እንዲሆን ተከታታይ ግንዛቤና ቁጥጥር ይጠይቃል ።
በቤታቸው እንዲቆዩ የተደረጉ የመንግሥት ሠራተኞች ከሚሰሩት የቢሮ ኃላፊነት በተጨማሪ ቤተሰባቸውንና የአካባቢያቸውና ማህበረሰብ ከቫይረሱ እንዲከላከሉ ድጋፍ በማድረግ የዜግነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።
በተለይም ከትምህርት ቤት የቀሩ ልጆች እንዳይሰላቹ በማድረግ ከቤት እንዳይወጡ በመከላከል የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል መስራት ለአገር ውለታ እንደመዋል የሚቆጠር ነው ።
አዲስ ዘመን መጋቢት 24/2012
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በዛብህ ገብረየስ መልዕክት