አዲስ አበባ:- ህመምተኞች በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ ህክምና ለማግኘት ቢያቀኑም ተቋሙ ከቀኑ 10 ሰዓት በኋላ ታካሚዎችን አያስተናግድም በመባሉ ህክምና ማግኘት እንዳልቻሉ ገለጹ።
ህክምና ለማግኘት ወደ ጤና ጣቢያው አቅንተው እረፍዷል በሚል ህክምና መከልከላቸውን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የገለጹት ጠና ባይለየኝ፤ ሀሙስ መጋቢት 18 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ህክምና ለማግኘት ወደ ጤና ጣቢያው ቢያቀኑም፤ ተቋሙ ከቀኑ 10 ሰዓት በኋላ ህመምተኞችን አያስተናግድም በሚል ህክምና ከልክሏቸዋል።
አንድ ህመምተኛ በመንግሥት የሥራ ሰዓትም ሆነ ከሥራ ሰዓት ውጪ ድንገተኛ ህክምና ካስፈለገው ህክምና የማግኘት መብት እንዳለው አቶ ጠና ጠቁመው፤ በመንግሥት የሥራ ሰዓት ህክምና ሊከለከሉ ስለማይገባ ህክምና እንዲሰጣቸው ባለሙያዎችን በትህትና ቢጠይቁም፤ በባለሙያዎች መገፍተርና መመናጨቅ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።
በአገሪቱ የተከሰተውን የኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታትና ቫይረሱ በማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድረውን የጤና ቀውስ ለመቀነስ ማንኛውም ሰው ህመም ሲሰማው በአቅራቢያው ወደሚገኙ የህክምና ተቋማት መሄድ እንዳለበት ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ምክር እየሰጡ በሚገኝበት ወቅት በሥራ ሰዓት ታማሚ አትስተናገዱም ብሎ መመለስ ተገቢ አለመሆኑን
አመልክተዋል ።
በዚህ ሁኔታ ድንገት በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ወደ ጤና ጣቢያው ቢመጣ ተገቢውን አገልግሎት ስለማያገኝ በቶሎ ወደ ማግለያ ክፍል ገብቶ አስፈላጊውን ህክምና አግኝቶ እራሱን ከከፋ የጤና ችግር እንዲሁም ሌሎችን በቫይረሱ እንዳይያዙ ለማድረግና ከእርሱ ጋር ማህበራዊ ንክኪ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍል ተጋላጭነት ለመቀነስ እንደሚያስቸግር ገልጸዋል።
የጤና ጣቢያው አገልግሎት አሰጣጥ ይሻሻል ዘንድ የሚመለከተው አካል ጉዳዩን አጣርቶ ተገቢውን እርምጃ ካልወሰደ ህመምተኞች በወቅቱ ህክምና አለማግኘታቸውን ተከትሎ ቫይረሱ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ አገራዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል፤ መንግሥት የሥራ ሰዓታቸውን በአግባቡ አክብረው በሥራ ላይ በማይገኙ የጤና ተቋማት ላይ እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል ብለዋል።
ሌላኛዋ የወረዳው ነዋሪ ወይዘሮ ኢክራም ናስር በበኩላቸው፤ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ልጃቸው መጠነኛ የሰውነት ሙቀት የነበረውና እየቆየ ሲሄድም አጣዳፊ ተቅማጥና ማስመለስ በመከሰቱ ከቀኑ አስር ሰዓት በጤና ጣቢያው ቢገኙም የጤና ጣቢያው በር ተዘግቶ እንዳገኙት ጠቁመው፤ ህክምና ለማግኘት መረጃ ቢጠይቁም ሰዓት አልፏል ከ10 ሰዓት በኋላ ህክምና አይሰጥም የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው፤ ልጃቸው በድንገተኛ ህክምና እንዲያገኝ ቢጠይቁም፤ ነገ ይዘሽው ነይ በማለት በዕለቱ ልጃቸው ህክምና መከልከሉን ተናግረዋል።
የልጃቸውን የክትባት ካርድ ለመውሰድ ለአንድ
ሳምንት ያህል ወደ ጤና ጣቢያው ቢመላለሱም የሚያስተናግዳቸው ማጣታቸውን የሚናገሩት ሌላኛዋ ባለቅሬታ ወይዘሮ አዲስ ጸጋው በበኩላቸው ፤ ያለልደት የምስክር ወረቀት ልጃቸው በመጪው ዓመት ወደ ትምህርት ገበታ መግባት ስለማይችልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በመዲናዋ የተወለዱ ህጻናት በሁለት ወር ውስጥ የልደት የምስክር ወረቀት መያዝ እንዳለባቸው አቅጣጫ በማስቀመጡ፤ የልደት ካርድ ከጤና ጣቢያው ለመውሰድ ከሳምንት በላይ ቢመላለሱም መልስ የሚሰጣቸው ማጣታቸውን ተናግረዋል።
በጤና ጣቢያው የሥራ አስተባባሪ አቶ ዳኜ ዘነበ ስለጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፤ በጤና ጣቢያው የሚያስተናግደው የማህበረሰብ ክፍል ሰፊ በመሆኑ ከፍተኛ ማህበራዊ ንክኪ በተቋሙ መኖሩን ገልጸው፤ ማህበረሰቡ ህክምና ለማግኘት ወደ ተቋሙ በሚመጣበት ወቅት ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆን፤ ታካሚው ህመሙ ድንገተኛ ህክምና የማያስፈልገውና ህመምተኛውን ለከፋ ጉዳት የማያደርሰው ከሆነ በተቋሙ ያለውን ማህበራዊ ንክኪ ለመቀነስ ሲባል በቤቱ እንዲያገግም ምክር በመስጠት እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል።
ባለሙያዎች እራሳቸውን ከቫይረሱ የሚከላከሉበት የመከላከያ መሳሪያዎች ሳይሟላላቸው እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው፤ በሽተኞች ለህክምና ወደ ተቋሙ በሚመጡበት ወቅት ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ የታካሚዎችን ቁጥር መገደብ ግድ በመሆኑ፤ ታካሚዎቹ ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ሲባል ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ብለዋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 23/2012
ሶሎሞን በየነ
ጤና ጣቢያው ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑ ተገለጸ