በተለያዩ ብዙሃን መገናኛ እንደሚዘገበው በየአገራቱ በሚገኙ መንገዶች እንደወትሮ ሰዎች እንደልባቸው ሲንቀሳቀሱ አይታይም። ካፍቴሪያዎችና የገበያ ሥፍራዎች ባልተለመደ መልኩ እረጭ ብለዋል፤ ጉዞዎችም ታግደዋል። ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። ሥራና ሌሎችም እንቅስቃሴዎች ቆመዋል። ብዙኃኑ አካላዊ ርቀትን ለመፍጠር ቤቱ ከትሟል። ይህ አይበቃም በሚል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጣሉ አገራት እንዳሉም ተሰምቷል። ስፖርታዊ ልምምዶችና ውድድሮችም ተከልክለዋል።
አብዛኞቹ አገራት ሰርግና ቀብርን ጨምሮ ሰዎች የሚሰባሰቡባቸውን ክዋኔዎች ሁሉ አስቁመዋል። የእዚህ ሁሉ ምክንያቱ በቻይናዋ ሁዋን ከተማ ሁቤይ ግዛት ተቀስቅሶ ወደ ተለያዩ የዓለም አገራት በፍጥነት በመዛመት ላይ ያለው ኮሮና ቫይረስ ነው።
የመጀመሪያው የቫይረሱ ተጠቂ ሪፖርት ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ሶስት ወራትን ለመድፈን ጥቂት ቀናት የቀረው አደገኛው ወረርሽኝ በፍጥነት በርካታ አገራትን በማዳረስ ከጤና ችግርነት አልፎ የኢኮኖሚ ቀውስ ማስከተሉን ተያይዞታል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በዓለማችን በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 786 ሺ 973 ደርሷል። 37 ሺ 843 ሞት ሲመዘገብ ፤ 165 ሺ 932 የቫይረሱ ተጠቂዎች ማገገም ችለዋል።
በአሜሪካ የመጀመሪያው በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ሪፖርት የተደረገው እ.አ.አ ጥር 20 ቀን 2020 ነበር። ሶስት ወራት እንኳን ሳይደፍን በቫይረሱ ትናንት በተመዘገበው መረጃ መሰረት 164 ሺ 266 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁባት ሶስት ሺ 170 ሰዎችን በሞት አጥታለች። ትናንት ብቻ 422 ዜጎቿ በቫይረሱ ሲያዙ ፤ 14 በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል።
በኮሮና ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የኢኮኖሚ ቀውስ ግምት ውስጥ በማስገባት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሁለት ነጥብ ሁለት ትሪልዮን ዶላር የኢኮኖሚ ማረጋጊያ ፈርመዋል። በርካታ አሜሪካውያን ቤታቸው በመቆየት በማህበራዊ ፈቀቅታ ውስጥ ሆነው ሁኔታዎችን እየተከታተሉ ቢገኙም፤ አሁንም የቫይረሱን ስርጭት ማቆም አልተቻለም።
ሌላዋ በቫይረሱ እጅግ ከፍተኛ የሚባለውን አደጋ በመጋፈጥ ላይ ያለችው ጣሊያን በድምሩ 101 ሺ 739 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘውባታል። በቫይረሱ የተጠቁት ሰዎች በአሜሪካ ከሚገኙት በቁጥር ቢያንሱም በሞት ከፍተኛውን ቁጥር በማስመዝገብ ጣሊያን ከአሜሪካ ትልቃለች። እስከ ትናንት 11 ሺ 591 ሰዎችን በቫይረሱ ምክንያት አጥታለች። 14 ሺ 620 ሰዎች ማገገማቸው ተነግሯል። በጣሊያን በኮሮና ቫይረስ የተያዘ የመጀመሪያው
ሰው ሪፖርት የተደረገው እ.አ.አ ጥር 29 ቀን 2020 እንደነበር ይታወሳል።
እ.አ.አ ጥር 29 ቀን 2020 ለመጀመሪያ ጊዜ ቫይረሱ የተገኘበትን ሰው የመዘገበችው ስፔን እስከ ትናንት ድረስ በተመዘገበ መረጃ 87 ሺ 956 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘውባታል። ከእዚህ ውስጥ ሰባት ሺ 716 ዜጎቿን ሞት ነጥቋታል። 16 ሺ 780 የሚደርሱ ሰዎች ማገገማቸውም ተመልክቷል።
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው የተመዘገበው እ.አ.አ መጋቢት 12 ቀን 2020 ነበር።
የመጀመሪያው ሰው ሪፖርት ከተደረገ ከ19 ቀናት በኋላ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በአጠቃላይ 1013 የላቦራቶሪ ምርመራ አድርጓል። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 66 የላብራቶሪ ምርመራ አካሂዶ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች በአጠቃላይ 25 ሰዎች የቫይረሱ ተጠቂ ሆነዋል። ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አራት ሰዎች ማገገማቸውም ተመላክቷል።
ኮቪድ-19 በመባል የሚታወቀው ይህ ወረርሽኝ የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ ነው። መጀመሪያ ትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ከሳምንት በኋላ ደግሞ የትንፋሽ ማጠርን ያስከትላል።
ቫይረሱ ዓለምን ማስጨነቁን ፣ ለብዙዎች የጤና እክል ምክንያት መሆኑንና የብዙዎችን ህይወት መቅጠፉን ቀጥሏል። የዓለም ሳይንቲስቶች መድኃኒቱን ለማግኘት ጥድፊያ ላይ ናቸው። ይፈውሳል የሚሉት ግኝት ላይ እስኪደርሱ አሁን ባለው የተጨበጠ መረጃ መሰረት የኮሮና በሽታ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ መከላከል የሚቻለው ርቀትንና ንጽህናን በመጠበቅ ነው። በመሆኑም በጤና ሚኒስትርና በዓለም የጤና ድርጅት የሚተላለፉ ማሳሰቢያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 23/2012
ዘላለም ግዛው
ስለ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ቁጥሮቹ ምን ይናገራሉ?